@AsaphTube · 597 subscribers
Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/AsaphTubeIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created May 7, 2021per Telegram
We have been tracking it since August 22, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
አላደግንም ከፍ ባለ አንደበት ሙቀት ለመጎተት ዝም ባለ አንደበት ኋላ ለመተቸት ስታወራ ጻድቅ ዝም ስትል በደለኛ እኔ ነኝ አዋቅ እነው ያንተ ዳኛ አላደግን ገና እየጋትን ወተት ፈራጅ በዝቷልና መማር ቀሬ ከእውነት እኔ ያንተ አንተ ትብስ ሆኗል የኛ ኑሮ ሰውን ማየት ሆኖበታል ክርስቲያን ዘንድሮ እግር አውጭኝ ይላላ ከዝግታ አለም ቶሎ ሙቀት እንጅ የሰከነ የለም ጆሮ ዳባ ብለን ሥር ለሚገነባ ጆሮ ተክለን ሰማን ውስጥ ለማይገባ ቆንጆ ተረት ሳቅ ከደራበት ሙቀት እስከ ማታ ለአፍታ ካየለበት የመጣ ስመስለን ሰማይ ተጠግቶ ጎትት እንላለን ትርጉም ተዘንግቶ ሰማይ ርቆ አያቅም እኛ ርቀን እንጅ በደጃችን ቆመን አለን ሄደን ከእርሱ ደጅ sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
.....መለኮታዊ ምስጢር...... ሰሞኑን በዚህ ስነ-መለኮታዊ ትምህርት እንቃኛለን የማይመረመረው መለኮታዊ ምስጢር ካሉ ምስጢራት ሁሉ በላይ ረቂቅና በሰው ልጅ አእምሮ ተመራምሮ የማይደረስበት ታላቅ ምስጢር ቢኖር ምስጢረሥላሴ ነው። ሚስጢር መባሉም በአመክንዮ (Logic) ብቻ ሊፈታ ስለማይችልና በእምነት የሚቀበሉት የፈጣሪ መገለጥ በመሆኑ ነው። “ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት” የመሆናቸው ምስጢር መለኮታዊ ተፈጥሮአቸው ከፍጡራን አእምሮ በላይ መሆኑን ያሳያል። የሥላሴን ምስጢር ለየት የሚያደርገው በሰው ልጅ ልምድ ውስጥ የሚታይ አምሳያ የሌለው መሆኑ ነው። ለምሳሌ፦ አንደኛው የጊዜ አልባነት ምስጢር ነው አብ ከወልድ አይቀድምም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም። ሦስቱም የዘላለም ቀዳማውያን ናቸው። ሦስቱ አካላት ቢኖሩም መለኮት ግን አይከፈልም። አብ ባለበት ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ። ይህንንም በወንጌል ዮሐንስ በአጭሩ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?” (ዮሐ 14፡10) በማለት ገልጦታል። ምስጢረ ሥላሴ በሰው ልጅ ጥበብ የተደረሰበት ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው። ስነ-መለኮትን ስናጠና አመክንዮን (Reason) እንደ ረዳት መሣሪያ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም፣ ገደብ ሳናበጅለት የእውቀታችን ሁሉ ብቸኛ መለኪያ ካደረግነው፣ የማይመረመረውን የእግዚአብሔርን ምስጢር በአነስተኛ አእምሯችን ለመጠቅለል በመሞከር ወደ እምነት እጦት እና አእምሮን ጣኦት የማድረግ ስህተት ውስጥ እንወድቃለን፤ በመሆኑም አእምሮ ከእምነት በታች ሆኖ መለኮታዊውን እውነት የሚያደንቅ እንጂ እውነቱን የሚፈጥር ወይም የሚቆጣጠር ሊሆን አይገባም። እያንዳንዱ የእምነታችን መሠረት ሕያው ሆኖ የሚቀጥለው በሥላሴ ምስጢር ውስጥ ሲሰረጽ ነው። ስለዚህ፣ ይህን ጥልቅ ምስጢር እንደ መነሻ በማድረግ፣ 'ለማወቅ አምናለሁ' የሚለውን መርህ በመከተል ወደ በሳል መረዳት የሚያሸጋግር እምነት ሊኖረን ይገባል። "ሥላሴን ለመረዳት የምትሞክር ከሆነ አእምሮህን ታጣለህ፤ ሥላሴን ከካድክ ግን ነፍስህን ታጣለህ።" ቅዱስ አውግስጢኖስ "የሥላሴ ምስጢር በሰው ልጅ ምክንያታዊነት(Reason) ሊደረስበት የሚቻል የፍልስፍና ጥያቄ ሳይሆን፣ በእምነት ብቻ የሚገኝ መለኮታዊ መገለጥ ነው።" ቶማስ አኩዊናስ "ወደ ሥላሴ ምስጢር ስንቀርብ ጫማችንን አውልቀን ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም የምንቆምበት ስፍራ የተቀደሰ ነው። አእምሮአችን ሊረዳው ባይችልም፣ ልባችን ግን በፍቅር ሊያመልከው ይገባል።" ቻርለስ ስፐርጀን ይቀጥላል....... sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
Last part እግዚአብሔርን ቀዳሚ ማረግ አንድን ሰው ባወቅነው መጠን የበለጠ እንደምንወደው እና ያ ሰው የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ እንደምንተጋ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን በባህሪውና በማንነቱ ይበልጥ እያወቅነው ስንመጣ በህይወታችን የሚገባውን ቀዳሚነት እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔርን በህይወታችን ቀዳሚ ማድረግ ማለት ፦እራስን ለእርሱ ማስገዛት እና በእያንዳንዱ ሁኔታዎች ውሰጥ እንደ ሃሳቡ እና እንደ ፈቃዱ መኖር ማለት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ እና እንደ አባትነቱ ማወቅ ያስፈልጋል። እግዚአብሔርን ማወቅ እርሱን እንድናስቀድም እና እርሱን በመፍራት እንድንኖር ይረዳናል። እስራኤላውያን ነፃ ያወጣቸው ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሆነ ሳያስተውሉ በሙሴ አለመኖር ወደ ሃጢያት አዘነበሉ፡፡ መፅሐፍ እንደሚል “እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም….” ሮሜ 1፡ 21 (አመት)”። የመኖራችን ወይም ዛሬን የማየታችን ምክንያት በህይወታችን ቀዳሚ ያደረግናቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ ስራ፣ ትምህርት፣ ቤተሰብ፣ ትዳር፣ ጓደኛ፣ አገልገሎት ቢሆን ቀዳሚ ሊሆን የሚገባው እራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳንሆን የሚከለክሉን ከሆነ እና ለእርሱ የሚገባውን ጊዜ እንዳንሰጥ እንቅፋት ከሆኑ ለእነዚህ ነገሮች እየተገዛን ነው ማለት ነውና ንስሃ ገብተን ወደ እርሱ እንመለስ፤ እግዚአብሔር በህይወታችን ካሉት ነገሮችህ ይልቅ ቀዳሚ እና ዋነኛ እናድርገው።