የሚረዳችሁ ሰው የተገቸገረ ሠው ነው።
✍️ብዙ ጊዜ ሰዎች አይናቸውን ወደ ከፍታዎች ፣ ባለሥልጣን ፣ሀብታም እና የተማሩ ደግሞም ትልልቅ ብለው ወደሚያስቡ ሰዎች እንደሚያደርጉ እሙን ነው። ሰው ገንዘብ ስኖረው በመስጠት ፣እውቀት ስኖረው በምክር ፣ጥሩ ዘመድ ስኖረው አንዳች ጥሩ ነገር ማድረግ የገሃድ እውነት ነው። ሥጋ ለባሽን ተስፋ የሚያደርግ ግን ብዙ ጊዜ ጉዳት ፣ሐዘን ፣አላስፈላጊ መጎዳት ፣በመጨረሻ ለውስጥ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ይዳርገናል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው(ት. ኤርም 17:5 (NASV))። ብዙ ጊዜ የሚረዳንን ሰው ከእኛ ከፍ ካለ ቦታ መጠበቅ የተለመደ ነው። አንድ አንድ ጊዜ ግን የሚረዳን ሰው ከታች ሊሆን ይችላል።
✍️ዛሬ ከሥራ ቦታ ስመለስ አንድ ነገር ገጠመኝ። በአርባ ምንጭ ከተማ ከሴቻ ወደ ታች ቁልቁለት እየፈጠንኩ ስመጣ ፣አንድ በእድሜ ገፋ ያለ አባት ወደ ታች ፣ለጸሐይ ጀርባውን ሰጥቶ እየወረደ ነበር። ይዠው ብኸድስ ቢዬ ሞተሬን አቆምኩኝና አባ ወዴት ኖት ? የእኔ ልጅ ወደታች ነኝ ፣አሉና እኔጋ መጡ። ሞተር ላይ እንደተቀመጡ የእኔ ልጅ እግዚአብሔር ይባርክህ እያሉኝ ጀርባዬ ላይ ሳሙኝ። አሜን አሜን... እያልኩኝ አባ ከየት ኖት አልኩኝ ? ልጄ ከመሥሪያ ቤት ወጥቼ ወደቤተ እየኸድኩኝ ነው። እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ አሉኝና ፣ እየጸለይኩ ነበር አሉኝ። ምንድነው አባ የሚጸልዩት ? ልጄ መንቀሳቀሻ(Transport) ያስቸግረኛል ፣እግዚአብሔር ሆይ ወደ ቤት የሚያደርሰኝን ሰው ስጠኝ እያልኩ እየጸለይኩ ነበር አሉኝና ጌታ ይባርክኽ አሉኝ አሁንም። አባ እኔ አገልጋይ ኢሳይያስ እባላለሁ ስል እልልል እሰይ የእኔ ልጅ አሉና ፣ልጄ እኔ የሚሠራው ክልል ላይ ነው ፣የዛሬ ሶስት ዓመት ወደ አርባምንጭ መጥቻለሁ ፣ሐዋሳ ረጅም ዓመት ሰርቻለው ፣ከ2004 ጀምሮ ከትልልቅ አገልጋዮች ጋር እያገለገልኩኝ ቆይቼ አሁን ወደ አርባምንጭ መጥቻለሁ ፣አሉና እኔ ሚዲያ ላይ ብቻ የማውቃቸውን አገልጋዮች ፣እሳቸው አብሮአቸው አገልግለዋል። እየገረመኝ እየሰማው እኔ ወደ ቤቴ ከሚመለስ ፣እሳቸው ወደ ሚሄዱበት ቦታ ድረስ አደርሳቸዋለሁ አልኩና ለራሴ በውስጤ ወሰንኩኝ። ታዲያስ በዚህች አጋጣሚ በሚትመስል ግኑኝነት ውስጥ እኔ አንዳች ነገር አደርግልሃለሁ አሉኝና ፣ሁለት ነገር ከእኔ ወሰዱ። ራእዬና የሕይወቴ ግብ ከሆኑ ነገሮች መሐል አንዱን በቀላሉ አደርግልሃለሁ አሉና ስልክህን ሰጠኝ አሉኝ እየገረመኝ ፣ስልክ ተለዋውጠን አድርሻቸው ወደ ቤቴ ተመለስኩ።
እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቍራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፣ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።
ዳዊትም፣ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብፃዊ ስሆን፣ የአንድ አማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ። የከሊታውያንን ደቡብ፣ የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡብ ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።”ዳዊትም፣ “ታዲያ ወራሪው ሰራዊት ወዳለበት መርተህ ታደርሰኛለህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው(ሳሙ ቀዳማዊ 30:12-15 (NASV))።
✍️ዳዊትን ወደ ተማረኩ ሚስቶቹና ወደ ተወሰዱ ንብረቶች መርቶ ያደረሰው ሰው ፣በረሃብ ምክንያት መንገድ ላይ የወደቀ ፣በሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ ፣ጉልበት የሌለው ፣አቅሙም የከዳው ሰው ነበር። ዳዊት ይረዳኛል ብሎ አልነበረም ሰውየውን ከመንገድ አንስቶ ያበላውና ያጠጣው። ነገር ግን ዳዊትን ወደ ትክክለኛ ቦታ የሚመራ ኮምፓስ(Compas) ያ የወደቀው ሠው ነበር። ወዳጆቼ የምትረዱት ሰው መልሶ የሚረዳችሁ ሊሆን ይችላልና የወደቁ ሰዎችን አትለፉ። ከአጠገባችሁ ያሉ ፣ግን አሁን በጣም የተቸገሩ ፣እናንተ ካላችሁበት ችግር የሚያወጡ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ዝም ብላችሁ አስቡ እስኪ ሞተር ልፍት ሰጥቼ ፣ራዕዬን የሚደግፍ ሰው ሳገኝ። እግዚአብሔር አሠራሩ ግሩም ነው። ጌታችን ምንም ባልተማረ ሰው በኩል ምሁር የማያስምረውን ትምህርት ሊያስተምረን ይችላል ፣ጥቅት የረዳችሁት እርዳታ የብዙ ሚልዮን ብር በር ሊሆን ይችላል ፣አንዳች አቅም በሌለው ሰው በኩል ወደ ምንጫችን ሊመራን ይችላል።
"Prayer"
✍️እግዚአብሔር ሆይ ይኽንን ጽሑፍ ያነበቡ ሁሉ ፣ከመንገዳቸው አንዳች የሚረዳን ሰው የሚቀሰቅስ የሰማይ ኃይል ይለቀቅ። እግዚአብሔር መልካምነቱ ከፊታችሁ ያውጣ ፣የስሙን ጉልበት ይዘዝላችሁ። ጸለይኩኝ የልቦናችሁ አይኖች ይከፈቱ ፣መርዳት የምትችሉበትን አቅምም ኃይልም እግዚአብሔር ይስጣችሁ። መንገዳችሁ በቅቤ የታጠበ ይሁን። የእግዚአብሔር ቀኝ ይደግፋችሁ። እንደ አጋር ምንጫችሁን ማየት ይሁንላችሁ። አሜን በሆነው በታመነው ምስኪር በኢየሱስ ስም አሜን(7*)🙏።
✍️Abuna
@EsayasAbuna
@Gospelofchristjesus








