⭕️ ደሙን የሚያየው እግዚአብሔር ነው ‼️
💢 እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከመውጣታቸው በፊት አሥረኛውን መቅሠፍት እግዚአብሔር በግብፃውያን ሁሉ ላይ ሲያመጣ እስራኤላውያን በበራቸው መቃን እና ጉበን ላይ ደም እንዲቀቡ ታዘው ነበር ።
🔰 ደሙን አይቶ የሚያልፈው ማነው ?? የሞት መልአክ ?? የሞት መልአክ የሚል እራሱ ክፍሉ ላይ አለ ?? ደሙን የሚያየው እግዚአብሔር እራሱ ነው ።
📜 ዘጸአት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
¹³ ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።
🔰 በግብፅ አገር የሚያልፈው እግዚአብሔር ነው ፣ ደሙን የሚያየውም እግዚአብሔር ነው ፣ የግብፅን በኩር የሚገድለውም እግዚአብሔር ነው ።
📜 “እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፥ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም።”
— ዘጸአት 12፥23
ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ የሚያልፈው እግዚአብሔር ሲሆን ፤ "አጥፊው" የተባለው መቅፀፍቱ (ጥፋቱ እራሱ) ነው ፤ በሰውኛ ዘይቤ ተገልጿል ። [ “ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።” መዝ 91፥10 ]
📜 “ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ።”
— ዘጸአት 12፥27
🔰 ፋሲካ የሞት መልአክ ማለፍ ሳይሆን የእግዚአብሔር ማለፍ ነው ፤ ደሙን አይቶ ያለፋቸው እግዚአብሔር ነበር ።
📜 “እንዲህም ሆነ፤ እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በግዞት እስካሉት እስከ ምርኮኞቹ በኵር ድረስ፥ የግብፃውያንን በግብፅ ምድር የተገኘውን በኵር ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵሮች ሁሉ መታ።”
— ዘጸአት 12፥29
🔰 ይሄንን ታሪክ ከሆነ ፍጡር ጋር ማያያዝ ማቆም አለብን ፤ በራሱ በእግዚአብሔር የተፈፀመ ድርጊት ነው ።
ይሄንንም ድርጊት የፈፀመው በእስራኤል ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ነበር ። እርሱም ወልድ ነው ።
📜 “በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፥”
— ዘጸአት 14፥19
የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏



