"Jehovah Jireh" (የሆዋ ይሬ) "እግዚአብሔር ያዘጋጃል" (The Lord Will Provide)። በዘፍጥረት ምዕራፍ 22 አብርሃም ልጁን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ በእግዚአብሔር በተፈተነበት ወቅት፣ ልጁን ለመሠዋት እጁን በዘረጋ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ጠርቶ ከለከለው። ከዚያም አብርሃም ቀና ብሎ ሲያይ ቀንዶቹ በዕንጨት ውስጥ የተያዙትን በግ አየና በልጁ ምትክ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። በዚህ ጊዜ አብርሃም እግዚአብሔር በፈተናውና በጭንቀቱ መሃል ያዘጋጀለትን መውጫ በማየት የዚያን ቦታ ስም "የሆዋ ይሬ" (እግዚአብሔር ያዘጋጃል) ብሎ ሰየመው። በሰው አቅም ምንም ተስፋ የሌለ በሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ እንኳን፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ መፍትሔውን እንደሚያዘጋጅ ያስታውሰናል። በአጠቃላይ ቃሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እና አቅራቢነት የሚያበስር ታላቅ ስም ነው። @Asaph1 sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
3July 10, 2026 105