.....መለኮታዊ ምስጢር...... ሰሞኑን በዚህ ስነ-መለኮታዊ ትምህርት እንቃኛለን የማይመረመረው መለኮታዊ ምስጢር ካሉ ምስጢራት ሁሉ በላይ ረቂቅና በሰው ልጅ አእምሮ ተመራምሮ የማይደረስበት ታላቅ ምስጢር ቢኖር ምስጢረሥላሴ ነው። ሚስጢር መባሉም በአመክንዮ (Logic) ብቻ ሊፈታ ስለማይችልና በእምነት የሚቀበሉት የፈጣሪ መገለጥ በመሆኑ ነው። “ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆኑ ሦስት” የመሆናቸው ምስጢር መለኮታዊ ተፈጥሮአቸው ከፍጡራን አእምሮ በላይ መሆኑን ያሳያል። የሥላሴን ምስጢር ለየት የሚያደርገው በሰው ልጅ ልምድ ውስጥ የሚታይ አምሳያ የሌለው መሆኑ ነው። ለምሳሌ፦ አንደኛው የጊዜ አልባነት ምስጢር ነው አብ ከወልድ አይቀድምም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም። ሦስቱም የዘላለም ቀዳማውያን ናቸው። ሦስቱ አካላት ቢኖሩም መለኮት ግን አይከፈልም። አብ ባለበት ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ። ይህንንም በወንጌል ዮሐንስ በአጭሩ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን?” (ዮሐ 14፡10) በማለት ገልጦታል። ምስጢረ ሥላሴ በሰው ልጅ ጥበብ የተደረሰበት ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው። ስነ-መለኮትን ስናጠና አመክንዮን (Reason) እንደ ረዳት መሣሪያ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም፣ ገደብ ሳናበጅለት የእውቀታችን ሁሉ ብቸኛ መለኪያ ካደረግነው፣ የማይመረመረውን የእግዚአብሔርን ምስጢር በአነስተኛ አእምሯችን ለመጠቅለል በመሞከር ወደ እምነት እጦት እና አእምሮን ጣኦት የማድረግ ስህተት ውስጥ እንወድቃለን፤ በመሆኑም አእምሮ ከእምነት በታች ሆኖ መለኮታዊውን እውነት የሚያደንቅ እንጂ እውነቱን የሚፈጥር ወይም የሚቆጣጠር ሊሆን አይገባም። እያንዳንዱ የእምነታችን መሠረት ሕያው ሆኖ የሚቀጥለው በሥላሴ ምስጢር ውስጥ ሲሰረጽ ነው። ስለዚህ፣ ይህን ጥልቅ ምስጢር እንደ መነሻ በማድረግ፣ 'ለማወቅ አምናለሁ' የሚለውን መርህ በመከተል ወደ በሳል መረዳት የሚያሸጋግር እምነት ሊኖረን ይገባል። "ሥላሴን ለመረዳት የምትሞክር ከሆነ አእምሮህን ታጣለህ፤ ሥላሴን ከካድክ ግን ነፍስህን ታጣለህ።" ቅዱስ አውግስጢኖስ "የሥላሴ ምስጢር በሰው ልጅ ምክንያታዊነት(Reason) ሊደረስበት የሚቻል የፍልስፍና ጥያቄ ሳይሆን፣ በእምነት ብቻ የሚገኝ መለኮታዊ መገለጥ ነው።" ቶማስ አኩዊናስ "ወደ ሥላሴ ምስጢር ስንቀርብ ጫማችንን አውልቀን ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም የምንቆምበት ስፍራ የተቀደሰ ነው። አእምሮአችን ሊረዳው ባይችልም፣ ልባችን ግን በፍቅር ሊያመልከው ይገባል።" ቻርለስ ስፐርጀን ይቀጥላል....... sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
3