ፊደል አበድሩኝ ያንተ ጥግ ይቅርና ዳርዳርታህ ገመና ከሊቁ ልቅልቅ ከሙንጭርጭር ጠሊቅ ከትንትኑ ትንትን ግሉፀ… — አሳፍ Tube — TG.ME

ፊደል አበድሩኝ ያንተ ጥግ ይቅርና ዳርዳርታህ ገመና ከሊቁ ልቅልቅ ከሙንጭርጭር ጠሊቅ ከትንትኑ ትንትን ግሉፀ እንትን ቀኝህ ግራ:ግራህ ደግሞ ቀኝ ከቃሌ ብትረዝም ፊደል እያጠረኝ አወኩህ ያልኩህን እንኳ መች አውቄ እንትኔ ብልህም አልገባኝ ጠልቄ ከባህር ተጨልፎ ብልቃጥ ተመዝኖ ልክህ ነው አይባል መልክህ ተተንትኖ እንኳን አንተን እራስህን መች ገልጬው የገባኝን ወይ ቋንቋው ቃል የለው ያንተን ልክ ሊገልፀው ወይ እኔ አላውቀው ቋንቋዬን ጠንቅቄ ወይ አይግሩኝ አበው ብጠይቅ አጥብቄ ጥቂት ብታሳየኝ ወየው ብዬ ግርም ሌላ መልክ የለህም ብዬም ብደመድም አንተ ግን እልፍ ነህ አንድ አይቋጭህም የእስከዛሬው ግልጠት ጭራሽ አይለካህም ምንጭ ከtelegram sʜᴀʀᴇ   ◈sʜᴀʀᴇ  ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram    Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube

❤2
July 18, 2026 95