ያህዌ-ካንና ፥ እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላክ እያንዳዳችን ሰዎች መለያ ይሆነን ዘንድ ቤተሰቦቻችን ያወጡልን መጠሪያ ስም አለን፡፡ እነርሱም ሲያወጡልን ሁኔታዎችን ክስተቶችን ወይም ደግሞ የሚወዱትን ስም መርጠው ያወጡልናል፡፡ በድሮ ዘመን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰንመለከት አብዛኛው ስም የሚወጣው ከባህል፣ ከክስተቶች ወይም ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ ሲሰይም ሲሆን ለዚህም ማሳያ እንዲሆን የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ የተባለው እግዚአብሔር ራሱ ያወጣለት ሲሆን እንዲሁም ደግሞ በአዲስ ኪዳን ላይ መጥምቁ ዮሃንስን ማንሳት እንችላለን። ከዚህም በላይ ደግሞ ሰዎች ካሉበት ሁኔታ፣ ባህሪ እና ማንነት ሲለወጡ ስማቸውም ጭምር ሲቀየር እናያለን ለምሳሌ ያዕቆብ ወደ እስራኤል እንዲሁም ሳዉል ወደ ጳውሎስ ተቀይሯል። ስምም ማንነትን እና ባህሪን የሚገልጽ ስለነበር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ማንነቱ በስም ለማሳየት ሲል “እኔ… ነኝ” እያለ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲናገር እናገኛለን። ይህም ማለት ደግሞ ባህሪውን እና ማንነቱን እንድናውቅ እና አውቀንም እንድንከተለው ስለሚፈልግ ነው። በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ ማንነቱ በስም የተገለጸው በአብርሃም ጊዜ ነበር። በመፅሐፍ ላይ እንደሚል “ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ ያህዌ ይርኤ፡ እግዚአብሔር ያዘጋጃል ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ዘፍጥረት 22፡14 (አመት) እግዚአብሄር የመስዋቱን በግ ለአብርሃም አዘጋጀቶ ነበርና፤ ያም ቦታ ያህዌ ይርኤ ተበሎ እስካሁን ድረስ እንደሚጠራ መፅሐፍ ይናገራል። በዚህ ጥናት ውስጥ የምንመለከተው ከእግዚአብሔር ባህሪያት እና ስሞች ውስጥ አንዱ የሆነው “ያህዌ ካናና” ነው። ቀጣይ👇👇👇👇
2