ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር የእውነት እንሁን! እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም!… — አሳፍ Tube — TG.ME

ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር የእውነት እንሁን! እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም! በልባችን እንለወጥ! ያልተኖረ የታይታ ገፅታ ምን በሰው ዘንድ ጎሽ ቢያሰኝና ቢገነባ ጊዜ ቆጥሮ ባዶነቱ ይገለጣል ከትወና ህይወት አያልፍም! ብልህ እንጂ ብልጣብልጥ አንሁን! እርሱ ጎሽ ይበለን ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው! ከተገለጠው ድርጊታችን በላይ የልብ አካሄዳችን የነገ ፍሬያችንን ይወስናል! የተገለጠው ድርጊታችን ለሰው ይታያል። ልባችን ግን በእግዚአብሄር ዘንድ ታይቶ ይመዘናል። ምንም ነገር ስናደርግ የምናደርግበት መንፈስ ከድርጊታችን በላይ በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ አለው ያልተኖረ የታይታ ብቻ ገፅታ ምን በሰው ዘንድ ጎሽ ቢያሰኝና ቢገነባ ጊዜ ቆጥሮ ባዶነቱ ይገለጣል ከትወና ህይወት አያልፍም! እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም። በልባችን እንለወጥ! ብልህ እንጂ ብልጣብልጥ አንሁን! ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር የእውነት እንሁን! የእውነት እንኑር! አንሸነጋገል! የእውነት ልብና ቅንነት ገፅታችን ይሁን! እርሱ ጎሽ ይበለን ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው። በእውነት መንፈስ ተባረኩ! ©Hanna Tekle sʜᴀʀᴇ   ◈sʜᴀʀᴇ  ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram    Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube

❤4
July 11, 2026 113 2