Last part እግዚአብሔርን ቀዳሚ ማረግ አንድን ሰው ባወቅነው መጠን የበለጠ እንደምንወደው እና ያ ሰው… — አሳፍ Tube — TG.ME

Last part እግዚአብሔርን ቀዳሚ ማረግ አንድን ሰው ባወቅነው መጠን የበለጠ እንደምንወደው እና ያ ሰው የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ እንደምንተጋ ሁሉ፤ እግዚአብሔርን በባህሪውና በማንነቱ ይበልጥ እያወቅነው ስንመጣ በህይወታችን የሚገባውን ቀዳሚነት እንገነዘባለን፡፡ እግዚአብሔርን በህይወታችን ቀዳሚ ማድረግ ማለት ፦እራስን ለእርሱ ማስገዛት እና በእያንዳንዱ ሁኔታዎች ውሰጥ እንደ ሃሳቡ እና እንደ ፈቃዱ መኖር ማለት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ እና እንደ አባትነቱ ማወቅ ያስፈልጋል። እግዚአብሔርን ማወቅ እርሱን እንድናስቀድም እና እርሱን በመፍራት እንድንኖር ይረዳናል። እስራኤላውያን ነፃ ያወጣቸው ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሆነ ሳያስተውሉ በሙሴ አለመኖር ወደ ሃጢያት አዘነበሉ፡፡ መፅሐፍ እንደሚል “እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም….” ሮሜ 1፡ 21 (አመት)”። የመኖራችን ወይም ዛሬን የማየታችን ምክንያት በህይወታችን ቀዳሚ ያደረግናቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ ስራ፣ ትምህርት፣ ቤተሰብ፣ ትዳር፣ ጓደኛ፣ አገልገሎት ቢሆን ቀዳሚ ሊሆን የሚገባው እራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳንሆን የሚከለክሉን ከሆነ እና ለእርሱ የሚገባውን ጊዜ እንዳንሰጥ እንቅፋት ከሆኑ ለእነዚህ ነገሮች እየተገዛን ነው ማለት ነውና ንስሃ ገብተን ወደ እርሱ እንመለስ፤ እግዚአብሔር በህይወታችን ካሉት ነገሮችህ ይልቅ ቀዳሚ እና ዋነኛ እናድርገው።

❤3
July 18, 2026 150