የመከራው መሲሕ፤ ኢሳይያስ 53 መሲሑ ለመጠላት፣ ለመቍሰልና ለመሞት እንደሚመጣ ከ700 ዓመታት በፊት ተነበየ፤ የመከራውን ጥልቀት ገለጠ፤ "ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን" (ቍ. 5)። እንደ ተጻፈው፣ ስለ እኛ በለበሰው ሰውነት የእኛን ቅጣት በሞላ ተቀበለ፤ ድቀታችንን ደቀቀ፤ ስለ መተላለፋችን ተመታ ስለ ጥፋታችን ቆሰለ፤ ስለ በደላችን ተወጋ። ይህ ሁሉ ሲሆን ደሙን ዘራ። በዚያም አጥቦን ሕይወቱን አካፈለን፤ በእግዚአብሔር እርሻም አለመለመን። #ኢየሱስ😭 sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈sʜᴀʀᴇ ◈telegram Let us praise God by poem! በግጥም እናመስግን! ይቀላቀሉ https://t.me/AsaphTube
July 7, 2026 136