part 2 “ያህዌ ካናና” የዕብራዊያን ቃል ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላክ ማለት ነው። “ስሙ… — አሳፍ Tube — TG.ME

part 2 “ያህዌ ካናና” የዕብራዊያን ቃል ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላክ ማለት ነው። “ስሙ ቀናተኛ የሆነው እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና ሌላ አምላክ አታምልክ። ” ዘፀአት 34:14 (አመት) የእግዚአብሔር ቀናተኛነት ሰዎች ጋር እንዳለው አይነት ቅንዓት ሳይሆን ከፍቅሩ እና ከባለቤትነት የተነሳ ቅን​ዓት ሲሆን እስራኤላውያኖች ከተደረገላቸው ነገር የተነሳ አምላካቸው እግዚአብሔርን ማምለክ ሲገባችው ለሌላ አማልክት ሲገዙ እና ለእጆቻቸው ስራ ሲሰግዱ ተገኝተው እግዚአብሔር “ከኔ ሌላ አምላክ አታምልኩ እኔ ቅናተኛ አምላክ ነኝና” ይላችዋል። በዚህ ጥናት ውስጥ የእግዚአብሔር ቀናተኛነቱን ፤ ቅናቱስ ከምን የመነጨ እንደሆነ ፤ አሁን ላይስ በህይወታችን ጌታችን የሆነው ማነው የሚለውን እንዲሁም እንዴትስ አድርገን ቀዳሚ እናድርገው የሚሉትን ሃሳቦች በጥልቀት እንመልከታለን። ቀናተኛ አምላክ ማለት “አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ”። ዘፀአት 20፡5 (አመት) “እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።” (ኦሪት ዘፍጥረት 1፡31 አመት) የእግዚአብሔር ቀናተኛነት በገላትያ 5፡20 ላይ እንዳለው “ቅናት” አይደለም። በገላትያ “ቅናት” የሚለውን ቃል ስንጠቀመው እኛ እንዲኖረን የምንፈልግው የነበረን ነገር ሌላ ሰው ኖሮት ስናየው የሚሰማን ቅናት ማለት ነው። በዘፀአት 20፡5 ውስጥ እግዚአብሔር የሚቀናው የራሱ የሆን እና ለእርሱ የሚገባውን ነገር ለሌሎች አማልከት ሲሰጥበት ነው፡፡ እንዲህ እንደሚል “በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ካለው ወይም ከምድር በታች ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ ነገሮች በማናቸውም ዐይነት ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ። አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤” ዘፀአት 20፡4-5 (አመት)። ይህ ጥቅስ የሚናገረው ለእግዚአብሔር ብቻ አምልኮ ከማድረግ ይልቅ ለጣዖታት ስለ መስገድ እና ጣዖታትን በማምለክ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ የሆነውን የአምልኮና የአገልግሎት ባለቤት ነው፡፡ እርሱ (እግዚአብሔር በዚህ ትዕዛዝ እንደገለጸው) ከእግዚአብሔር ሌላ ማንኛውንም ነገር ማምለክ ወይም ማገልገል ኃጢአት ነው፡፡ እኛ የሌለንን ነገር ሌላው ሰው ሲኖረው ያንን ስንመኝ እና ስንቀና እርሱ ልክ ያልሆነ ቅንዓት ነው፡፡ ቅንዓት የሚለውን ቃል እግዚአብሔር ቀናተኛ ነኝ ሲል በተለየ መንገድ ነው፡፡ እርሱን የሚቀናው ለእርሱ ብቻ የተገባው አምልኮ እና አገልግሎት ለሌላው ሲሰጥ ነው፡፡

👍2❤1
July 18, 2026 80