@wxx466 · 1.4K subscribers
የመኖሪያ ቤቶችን ድልድል በተመለከተ በዚህ ገጽ
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/wxx466Is this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created May 17, 2022per Telegram
We have been tracking it since July 17, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
ለመኖሪያ ቤት አመልካቾች! የምርምር እና ህትመት ውጤቶች አያያዝ ሙሉ በሙሉ በትምህርት ሚኒስቴር በተላከው የእድገት/promotion/ መመሪያ መሰረት ስለሆነ በፊት ከነበረው ውጤት ጋር ልዩነት ሊያመጣ ስለሚችል በተላከው የእድገት መመሪያ መሰረት የምርምር ውጤታችሁን ለኮሚቴዎች እንድታስገቡ ለማሳሰብ ነው። መልካም ቀን!
ሰላም ውድ አመልካቾች! ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት በአንዳንድ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር የስራ ክፍሎች ላይ በተፈጠረው የሲስተመ መቆራረጥ ምክንያት በተገለጸው ጊዜ ማመልከቻችሁን ማስገባት እንዳልቻላችሁ በኮሚቴዎች በኩል ተገልጾልናል። ስለሆነም በዚሁ መሰረት ያለው የስራ ጫና ጭምር ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ 12 የስራ ቀናት የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን። መልካም ቀን!
ማስታወቂያ ለመምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች በሙሉ እንደሚታወቀው የመኖሪያ ቤቶች አስተዳደር በየጊዜው የመኖሪያ ቤቶች የውጤት ድልድል እያደረገ የቤት ምደባ አገልግሎት ይሰጣል። ስለሆነም የቤት ድልድል አገልግሎት የምትፈልጉ አመልካቾች ማስረጃችሁን ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 26/08/2018 ዓ.ም በየአካዳሚክ ዩኒቶች በተመረጡት ኮሚቴዎች በኩል ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ// 1) ከዚህ በፊት ማለትም በ2017 ዓ.ም ያመለከታችሁ…
ሰላም ለሁላችሁም ይሁን ውድ የድልድል ኮሚቴዎች! ረቡዕ በ07/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ በውጤት አሰራር ዙሪያና ስለሲስተሙ አጠቃቀም ገለጻና ማብራሪያ ስለሚኖር ከአካዳሚክ ዩኒት አንድ ተወካይ እንድትገኙ እናሳስባለን።
አርብ በ06/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ ተ.ቁጥር 360 ያላችሁ አመልካቾች ከላይ በተያያዘው መሰረት ዘንዘልማ ላሉት ባለ 1 መኝታ ቤቶች ብቻ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት ቁልፍ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። እንዲሁም ሰኞ በ09/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ለስቱዲዮ አመልካቾች እስከ ተ.ቁጥር 510 ያላችሁ አመልካቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመገኘት የቤት ቁልፍ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።