የሀዘን ግጣም ናት ፣ ትለኛለህ አሉ
ገል ነው ሰውነቷ ፣ ወዲያው ይጠፋል ውሉ
ሊቅ ደቂቅ አታውቅም ፣ የማይንጣት የለም
ትለኛለህ አሉ ፣ ልምዷ ነው መቆዘም ።
ወለምታ ነው የሚቀናት
ትንሹ ነው የሚያበግናት
ሀሳበ ውስን ነች አታይም አርቃ
ሀዘን ይቀናታል
ኢምንቷንም እከል ታያለች አትልቃ ።
ትለኛለህ አሉ
አልከኝ አሉ ጠና ያለ ወግ አያምርባት
ቆፍጠን ማለት አይሄድባት
አታውቅበት
መከራከር ምከንያት ሰበብ በረድፍ አርጎ
ከፍ ማለት በስሜት ላይ ፣ ፊትን ከልብ ዘወር አርጎ ።
ባይሳንም ይከብደኛል ፣ እውነት አለው ንግግርህ
ማይወርፍህ ይጥለኛል ፣ ጣም የሌለው ይመረኛል
ባየሆን ይሄን አትዘንጋ
በሚታየው ስለምወድቅ ፣ ልብህ መራቅ ስላልቻለ
እንዳይመስልህ ደንዳናነት ፣ ስርቴ ላይ ያልታከለ ።
ምሕረት ዘነበ

