••
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት ፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።
••
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ••
👉 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት እንዲሁም
••
👉 ከምሽቱ 1ሰዓት ፣ 3ሰዓት ፣ 6ሰዓት ፣ 9ሰዓት ፣ 11ሰዓት ናቸው::
••
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::••
👉 #አለመሳሳም አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም።
••
👉 #መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም።
••
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
••
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
••
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው።
••
📌 የጌታችን ሕማማት የምናስብበት ሳምንት ይሁንልን••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
👉🏻 https://t.me/Terbinos
👉🏻 https://www.facebook.com/terbinos
