እግዚአብሔር በዚህ ጾም አልወጣ ፤ አልላቀቅ ያለልን አመላችንን ይንቀልልኔ
••
ክብር ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሰይጣንን ወግቶ ድል የነሣው በቆሮንቶስ በረሃ ነበር። እንደ አይሁድ ትውፊት ከሆነ ሰይጣንና የክፋት መናፍስቱ ከእጽዋት የተራቆተ በረሃማን ስፍራ ለማደሪያነት ይመርጣሉ። በርግጥም ሕያዋን የሆኑ ጻድቃንን፣ ከውኃ ዳር እንደ ተተከለ ዛፍ የለመለሙ እና ፍሬያማ የሆኑ ቅዱሳንን የማይወድ ሰይጣን፣ ለማደሪያነት የውኃ ምንጭ እና ልምላሜ የሌለበትን በረሃ ይመርጣል ቢባል የሚደንቅ ነገር አይደለም። ይህም በመሆኑ መድኃኒታችን ሰይጣንን አጎሳቁሎ እና አዋርዶ ያሸሸው ሰልጥኖ ከሚኖርበት በረሃ ገብቶ ነው። ዛሬም የቅድስና ምንጭ የደረቀበት፣ ከበጎ ምግባር ተራቁቶ ገላጣ መሬት በመሆን ለሰይጣን ምቹ ማደሪያ የሆነ ሌላ በረሃ በዚህ አለ። ይህም በረሃ ሃይማኖት የሰለለበት፣ የመልካምነት ፍሬም ደርቆ የረገፈበት የእኛ ሰውነት ነው። በቆሮንቶስ በረሃ የነበረውን ፈታኝ ድል የነሣ ጌታ፣ በእያንዳንዳችን ሰውነት መሽገው የተቀመጡትን መናፍስት "ከኋላቸው ሂዱ" ብሎ ገስጾ ከእኛ ያርቅልን።
••
መልካም የጾም ጊዜ ይሁንልን!
••
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ዘወረደ 2018 ዓ.ም.
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinosy
8February 16, 2026 1.6K 1