👉 ሰንበትን ሊያጸናልን
••
የአይሁድ ሰንበት ፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት ። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት ፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ) ፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ
••
👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት
••
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። " ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ " ( ዮሐ20:29 )
••
የተሣተውን ፤ የተረሳው ፤ የተገደፈውን ፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
••
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
2
2April 27, 2025 2.1K 2