በእርግጥ ፤ አለፍ አለፍ ብሎ ፥ ስም ለግብር ያዋጣል ያመኑትም ሀሳብ ፥ ሥጋ ለብሶ ይመጣል ቅድመ ክንውኖች ፥… — Mihret Zenebe (mercy) — TG.ME

በእርግጥ ፤
አለፍ አለፍ ብሎ ፥ ስም ለግብር ያዋጣል
ያመኑትም  ሀሳብ ፥ ሥጋ ለብሶ ይመጣል
ቅድመ ክንውኖች ፥ መንገድ ይጠርጋሉ
ግን ሁሌ ዋስ ሆነው መች ያስፈጽመሉ ?

ብዙ እየታዘቡ ፥
ለሀሳብ ለፍላጎት ምክንያት ሰቶ መላፍ
ማታ ህርሜን ብሎ ፥ ቀን አብሮ መሰለፍ
የዛሬ ሰቀቀን ፥ የነገ ኪሳራ
የፈረሰ ሁሉ ፥ ዳግም ላይሰራ
አንዳንዱ አይለወጥ ፥ ይቅር እንደ ከፋ
ላልሆነልን  ሁሉ ፥ አይገባም ጸጸት
አይገባም ተስፋ ።

ምሕረት ዘነበ
❤6⚡3👏2
June 27, 2026 213 1