የሀዘን ግጣም ናት ፣ ትለኛለህ አሉ ገል ነው ሰውነቷ ፣ ወዲያው ይጠፋል ውሉ ሊቅ ደቂቅ አታውቅም ፣… — Mihret Zenebe (mercy) — TG.ME

የሀዘን ግጣም ናት ፣ ትለኛለህ አሉ
ገል ነው ሰውነቷ ፣ ወዲያው ይጠፋል ውሉ
ሊቅ ደቂቅ አታውቅም ፣ የማይንጣት የለም
ትለኛለህ አሉ ፣ ልምዷ ነው መቆዘም ።

ወለምታ ነው የሚቀናት
ትንሹ ነው የሚያበግናት
ሀሳበ ውስን ነች  አታይም አርቃ
ሀዘን ይቀናታል
ኢምንቷንም እከል ታያለች አትልቃ ።
ትለኛለህ አሉ

አልከኝ አሉ ጠና ያለ ወግ አያምርባት
ቆፍጠን ማለት አይሄድባት
አታውቅበት
መከራከር ምከንያት ሰበብ በረድፍ አርጎ
ከፍ ማለት በስሜት ላይ ፣ ፊትን ከልብ ዘወር አርጎ ።

ባይሳንም ይከብደኛል  ፣  እውነት  አለው ንግግርህ
ማይወርፍህ ይጥለኛል ፣ ጣም የሌለው ይመረኛል
ባየሆን ይሄን አትዘንጋ
በሚታየው ስለምወድቅ ፣ ልብህ መራቅ ስላልቻለ
እንዳይመስልህ ደንዳናነት ፣ ስርቴ ላይ ያልታከለ ።

        ምሕረት ዘነበ
🔥4🥰2
August 12, 2026 112 2