የተወዳጁ አዳም ረታ አዲሱ መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ በሁሉም የጃዕፈር መጻሕፍት መደብሮቻችን ለሽያጭ ይቀርባል :: በቅርብ ቀናት ደግሞ ከደራሲ አዳም ረታ ጋር በመነጋገር የፊርማ ስነስርአት ዝግጅት ይኖረናል :: በድጋሚ ለማሳወቅ ያክል በአዲስ አበባ ኤግዝቢሽንና ባዛር ላይ አልተሳተፍንም :: ምክንያቱንም ሌሎች ተሳታፊዎች ከከፈሉት እጥፍ ክፈሉ ስለተባልን ነው :: ይህንንም በተደጋጋሚ የምናሳውቀው ጃዕፈር መጻሕፍትን ብላችሁ ሄዳችሁ ውድ ጊዜያችሁንና ገንዘባችሁን እንዳታባክኑ በማሰብ ነው :: ከመደበኛው ሽያጭ ባለፈ ባሉን ሁሉም ቅርንጫፎቻችን እስከ እሁድ ድረስ ልዩ ቅናሽ አድርገናል ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ከ 30% እስከ 50 % ቅናሽ መጻሕፍትን መሸመት ትችላላችሁ :: እናመሰግናለን !
July 31, 2026 82