ድሮሮሮ.. ሆነህ ዩኒቨርስቲ ከገባህ ያመልኩሃል። ያጨበጭቡልሃል። ያደንቁሃል። ጀለስካዎች ይቀኑብሃል። ጸዴ፥… — Mihret Zenebe (mercy) — TG.ME

ድሮሮሮ.. ሆነህ ዩኒቨርስቲ ከገባህ ያመልኩሃል። ያጨበጭቡልሃል። ያደንቁሃል። ጀለስካዎች ይቀኑብሃል። ጸዴ፥ የተማረች፥ ገርል ትጠብሳለህ። ላይፍ ይገባሃል። ራስህን ትችላለህ። ሰው አያነብልህም። በአውራ ጣትህ አትፈርምም! ፈረንጅ ማውራት ትችላለህ። ፖለቲካ ታውቃለህ። የመንግስት ስራ ትይዛለህ። ኮት ትገዛለህ። ቤተሰቦችህ ደረታቸውን ይነፋሉ። እህቶችህ የመጠበሻ ክላሳቸው ከፍ ይላል። ወመኔው ወንድምህ በስምህ ተበድሮ ያጨሳል። የሰፈሩ ቅያስ በስምህ ይጠራል "ያ ዩኒቨርስቲ የገባው ጨዋ ልጅ ቤት ጋ" ምናምን ነገር፥ የሰፈሩ ሼባዎች ያከብሩሃል፥ ወመኔ ጀለሶችህ በሹክሹክታ ያሙሃል፥ የተለየ ወጥ ይሰራልሃል፥ ትኩስ እንጀራ ይቀርብልሃል። ትከበራለህ። የዋለልኝን አርቲክል ታነባለህ። ጥላሁን ግዛው ይናፍቅሃል። መንግስትን ትጠላለህ። ቦርጫም ቢሮክራት ይደብርሃል። ፀጉርህን ታጎፍራለህ። ጺም ይኖርሃል። ፍልስፍና ታሪክ ፖለቲካ ትንሽ ሳይንስ ትለበልባለህ። ትከራከራለህ። በካሴት ሙዚቃ ትሰማለህ። ሲጋራ ታጨሳለህ። ወሬህ ፀዴ ይሆናል። አይዲያሊስት ሆነህ ቁጭ ትላለህ። ምድር ላይ ገነት ትፈልጋለህ። የኢትዮጵያ ህዝብ ባንተ ትግል ነፃ እንደሚወጣ ታምናለህ። ትመረቃለህ። በት'በት ብለህ የመንግስት ስራ ትይዛለህ። ቤት ትከራያለህ። መፃህፍት ይኖሩሃል። መንግስትን በጎሪጥ ታያለህ። እሱም ይገላምጥሃል። ሲመሽ ቢራ ትጠጣለህ። መንግስትን በሹክሹኩታ ታማለህ። መኖር ትጀምራለህ። ለናትህ ሻሽ ትገዛለህ። ለአባትህ የጠጅ መጠጫ ትሸጉጣለህ። ጨረቃን በገመድ ለማውረድ እንደሞከርክ ይገባሃል። ኒያላ ለኩሰህ ከት ብለህ ትስቃለህ። ታገባለህ። እናትህን አያት ታደርጋለህ። ሰፈሩ ለሚያሰራው መንገድ ሊቀመንበር ትሆናለህ።

July 1, 2026 257 3