ነግረሀኝ ነበር ስሜ በአንተ አፍ ሆኖ እንደማያውቅ መጠሪያ ብቻ ከሚያውቀኝ ሁሉ ቃሉም ትረጉም እንዳይደል አቻ… — Mihret Zenebe (mercy) — TG.ME

ነግረሀኝ ነበር ስሜ በአንተ አፍ ሆኖ እንደማያውቅ መጠሪያ ብቻ
ከሚያውቀኝ ሁሉ ቃሉም ትረጉም እንዳይደል አቻ
የሚተነተን መልክት እንዳለው ከልብህ ሰፈር
እንደሰየምከኝ አንድ ቃል አርገህ ልክ እንደ ሀገር ።

ነግረሀኝ ነበር እኔም አምኜ
በአጠራርህ ከብዙ ድኜ ።

ቆም እስኪያረገኝ አንድ አጋጣሚ
እየጠራሀኝ አቤት ሚል ሳስ ልክ እንደ ሰሚ
አፍታ  እስኪበቃህ  ሌላ ለመጫር
በእንቅፋቴ ሹመቴ እስኪሻር።

ያቺው ብሆንም
ቀጥ ያለ አይደለም ዛሬ አቋቋሜ
ለካ ወትሮውም ተግባሬ ነበር የእኔ ስያሜ ።

ምሕረት ዘነበ
👏3❤1
July 29, 2026 125