ክፍል 13
እናቴ ቁርአኑን ካቆመች በኋላ እኔ በከባድ ትንፋሽ መሬት ላይ ተደፋሁ። እናቴ በእንባ ተሞልታ «ልጄ የአላህ ቃል እንዴት ያምሻል? በውስጥሽ ያለው ነገር ምንድን ነው?» ስትል ጠየቀችኝ። እኔ ግን መመለስ አልቻልኩም ምክንያቱም እኔ ራሴ ቁርአን መስማት ለምን እንደከበደኝ አልገባኝም ነበር።
ቀደም ሲል አባቴና እናቴ ቁርአን ሲቀሩ ወይም ከመስጂድ የአዛን ድምፅ ሲሰማ ልቤ በታላቅ ሰላም ይሞላ ነበር። አሁን ግን የቁርአን ድምፅ ሲሰማ በውስጤ እንደ እሳት የሚቃጠል ስሜት ይፈጠር ነበር። ይህ ሁኔታ እኔን በከፍተኛ ሁኔታ አሰቃየኝ። «እኔ ካፊር ሆኛለሁ ወይስ እምነቴ ጠፋ?» ብዬ ራሴን እወቅስ ነበር።
በዚያ ሰሞን የአእምሮ ጫናዬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ። ራሴን የማጥፋትና ከዚህ ስቃይ የመገላገል ሀሳቦች በአእምሮዬ ውስጥ ይመላለሱ ጀመር። «ከዚህ ሁሉ ስቃይ መሞት ይሻላል» ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። ነገር ግን አላህን መፍራቴና የእናት እና አባቴ ሀዘን ያን እንዳላደርግ ከለከለኝ።
አንድ ቀን ማለዳ ታናሽ ወንድሜ ወደ ክፍሌ ገብቶ «እህቴ... እባክሽን ወደ ቀድሞው ሁኔታሽ ተመለሺ ለሊት ለሊት ጥርስሽን ትበያለሽ ታስፈራሪኛለሽ ትጮሂያለሽ አባታችን ደሞ ባንቺ ነጋ ጠባ ሁልጊዜ ያለቅሳል» አለኝ። የወንድሜ ንግግር ልቤን ነካው። ተነስቼ ልታቀፈው ስሞክር በድንገት አእምሮዬ ተዛባና ወንድሜን ገፍትሬ ጣልኩት፡፡ እውነትም አውሬ ሁኛለሁ፡፡
ወንድሜ መሬት ላይ ወድቆ በቅስፈት እያለቀሰ ከክፍሌ ወጥቶ ሮጠ። እኔ እጆቼን ተመልክቼ በፍርሃት ተንቀጠቀጥኩ። «እኔ ምን አደረግኩ? ለምን ወንድሜን ገፈተርኩት?» ብዬ ራሴን ጠየቅኩ። እጆቼን ለመቆጣጠር አቅም አጥቼ ነበር አእምሮዬና አካላቴ ተለያይተው ነበር።
ከዚያ ቀን በኋላ ወንድሜ ወደ ክፍሌ ጨርሶ አልመጣም። አባቴም እኔን በክፍሌ ውስጥ ዘግቶ እንድቀመጥ አዘዘ። «ለሌሎች አደጋ እየሆነች ነው ከክፍሏ መውጣት የለባትም» አለ። በዚህ ሁኔታ በክፍሌ ውስጥ እንደ እስረኛ መኖር ጀመርኩ።
በዚያች ትንሽና ጨለማ ክፍል ውስጥ ቀናትና ሳምንታት አለፉ። የምግብ ሳህን በበሩ ስር ይገባልኝ ነበር ልክ እንደ እስረኛ፡፡ እኔ ግን አብዛኛውን ጊዜ አልነካውም ነበር። የብቸኝነት የፍርሃትና የመመሰቃቀል ስቃይ አእምሮዬን ሊያሳብደው ተቃረበ። በየሌሊቱ በርካታ ጥቁር ምስሎች በክፍሌ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ አያለሁ።
አንድ ምሽት ከመስኮቴ ውጭ ባለው ጨለማ ውስጥ ሁለት የሚያበሩ ጥቁር ዓይኖችን አየሁ። ያይን ምስል ወደ መስኮቱ ቀርቦ «ማንም ሊረዳሽ አይችልም አንቺ የእኛ ነሽ!» የሚል አስፈሪ ድምፅ አሰማ። በፍርሃት ተንቀጠቀጥኩ ድምፄን አውጥቼ መጮህ ፈለግኩ ነገር ግን ጉሮሮዬ ተዘጋ...
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇






