በልብስ ላይ የሚሰሩ ሲህሮች 🖍(በዶ/ር ኡሙ ሚስባህ) ​ክፍል 2፡ ምልክቶቹ ​ 7. #የመፍራት_ባህሪ ድንጉጥ… — 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿 — TG.ME

✉️ በልብስ ላይ የሚሰሩ ሲህሮች
🖍(በዶ/ር ኡሙ ሚስባህ)

ክፍል 2፡ ምልክቶቹ

​ 7. #የመፍራት_ባህሪ
ድንጉጥ መሆን ዋነኛው መለያ ነው። ከእንቅልፍ በርግጎ መነሳት፣ ኮሽ ባለ ቁጥር መደንገጥና በተለይ የአዛን ድምፅ ሲሰማ ውስጣዊ መረበሽ ይፈጠራል። ከሰው ተገልሎ መቀመጥን ምርጫቸው ያደርጋሉ።

​8. #ቀልብን_ማበላሸት_ሰላትን_መጥላት
ሰላት መቆም እንደ ሞት ይከብዳቸዋል። በምንም አይነት አስገዳጅ ሁኔታ እንኳ ለመስገድ ፍቃደኛ አይሆኑም። ሌላ ሰው ሰላት ሲሰግድ ማየት በራሱ ከፍተኛ ጭንቀትና ከዚያ ቦታ የመሸሽ ስሜት ያመጣባቸዋል።

​ 9. #ልብ_የሚረብሽ_የሰላም_እጦት
ነጋ ጠባ በጭንቀትና በጥብብ መኖር፣ ልብ በፍርሃት መሸበርና ሰውን ማየት መጥላት የዘወትር ስሜታቸው ይሆናል። ሰላምን ማጣት እጅግ ትልቅ ቅጣት ነው።

​ 10. #ብርቱ_የማይለቅ_መጥፎ_ሽታ
ከአፍ፣ ከብብት ወይም ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚወጣና በዲዮድራንት የማይጠፋ ሽታ ይፈጠራል። ታማሚው ቢታጠብና ቢታጠን እንኳ ሽታው ስለማይለቅ ሰዎች አጠገቡ መቆም እስኪጠሉ ድረስ ይቸገራል።

​11. #ዶካኪ_ባህሪ_መደበርና_ራስን_ማግለል
እነዚህ ምልክቶች ሲደራረቡ መጨረሻው ተስፋ መቁረጥ ይሆናል። "አልጠቅምም፣ መሞት አለብኝ" ብሎ ማሰብና ሰዎችን መጠርጠር ይጀምራሉ። ሁልጊዜ መቆዘም መገለጫቸው ይሆናል።

​12. #ክፉ_አስፈሪ_ህልሞች
ከከፍታ ቦታ መውደቅ፣ እባቦች ሲነድፉ ወይም አይጦች ሲሮጡ ማየት፣ እንዲሁም ጥቁር አስፈሪ ፍጥረታት ሲያፍኗቸው ማለም የተለመደ ነው።

​13. #ተራነት_የበረካ_እጦት
ታካሚው ስኬታማ ነጋዴ ቢሆን እንኳ ገንዘቡ በረካ አይኖረውም። ገንዘቡ የት እንደሚገባና በምን ላይ እንደሚወጣ ለማሰብ ሲሞክሩ አእምሮአቸው ይታመማል።

​14. #ርሀብ_አለ_በዛም_ላይ_የሆድ_መነፋት
ሆድ እንደ እርጉዝ ሴት ይነፋል፤ ከመነፋቱም በላይ በጣም ይወጠራል። በሆድ ውስጥ የሚገላበጥ ነገር እንዳለ ታካሚው ይሰማዋል።

ህክምናው
✅ #ተዝኪር ጠዋትና ማታ አላህን ማስታወስና ቁርአን መቅራት።
✅ #ልብሱን_ማስወገድ የሚጠረጥሩትን የልብስ አይነት ከቤት ማውጣት።
✅ #ውሃ_መጠጣት በብዛት ውሃ መጠጣት።

✅ #ሱሶችን_ማቆም ቡና፣ ጫት፣ ኮካ፣ ሺሻና መሰል ሱሶችን መተው።

✅ #ሩቅያህ በአፋጣኝ ሩቅያህ መጀመርና ኢማንን ማጠናከር።

✅ #ዳእዋ ጠቃሚ ዳእዋዎችን ዘወትር ማዳመጥ።
ህክምናው በቀልብ ዶክተር ቴሌግራም ቻናል ላይ ይቀጥላል...

​#ሲህር #የልብስ_ሲህር #ሩቅያ #ቀልብ_ዶክተር #ኢስላማዊ_ህክምና #ጤና #ፈውስ #እምነት #ትምህርት

አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው
🔸

💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡

💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇

⭐️ https://t.me/Qallbdoc


ህክምና ለማግኘት👇

✈️https://t.me/freeeeeeeeeeeere

👆

ህክምና ለማግኘት👇

✈️https://t.me/UstazulQallb

👆

ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇

📱 https://qalebdoctor.com
❤4
August 31, 2026 505 3