ከአስማእ (ረድየሏሁ ዐንሃ) ተዘግቧል፦
አንዲት ሴት እንዲህ አለች፦
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ባለቤቴ ሌላ ሚስት (ድርራ) አላት። ባለቤቴ ያልሰጠኝን ነገር እንደሰጠኝ በማስመሰል ብናገር ኃጢአት አለብኝን?"
ነቢዩ (ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
"ያልተሰጠውን እንደተሰጠው የሚያስመስል ሰው፣ የሐሰት ሁለት ልብስ እንደለበሰ ሰው ነው።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)
አጭር ትምህርት: ሰው ያልተሰጠውን ነገር እንዳለው መናገር፣ በሀብት፣ በእውቀት ወይም በሌላ ነገር ራሱን ማጋነን እና ማስመሰል የተከለከለ ነው። ሙስሊም እውነተኛ መሆን አለበት።
⭐️ https://t.me/Qallbdoc
✨https://t.me/dr_of_heart


