ክፍል 11
በማግስቱ ጠዋት እናቴ ወደ መስጂዱ ልትወስደኝ ተዘጋጀች። እኔም ልብሴን ቀይሬ ከቤት ለመውጣት ተዘጋጀሁ። ነገር ግን ወደ ደጃፉ እንደደረስኩ እግሮቼ ከባድ ድንጋይ እንደተጫነባቸው ያህል ሊንቀሳቀሱልኝ አልቻሉም። አካላቴ በሙሉ መንቀጥቀጥ ጀመረ በደረቴ ላይ ከባድ ጫና ስሜት ተሰማኝ።
እናቴ «አይዞሽ ልጄ ተራመጂ» እያለች እጄን ስትስበኝ በድንገት ራሴን ስቼ መሬት ላይ ወደቅኩ። እናቴ በጮኸች ጊዜ አባቴና ወንድሜ ሮጠው ወጡ። አባቴ እኔን ተመልክቶ «ይህች ልጅ ወደ መስጂድ መሄድ አትፈልግም በውስጧ ያለው ነገር እየከለከላት ነው ስለዚህ ሼሁ ጋ ተሸክመንም ቢሆን እንውሰዳት» ሲል በሰመመን ውስጥ ሁኜ እሰማው ነበር፡፡
በዚያ ቅጽበት አእምሮዬ ይሰራ ነበር ነገር ግን ሰውነቴን ማዘዝ አልቻልኩም ነበር። አባቴ እኔን ወደ መስጂድ ከመውሰድ ይልቅ በመንደራችን ያሉ ባህላዊ አዋቂዎችንና ጠንቋዮችን መጠየቅ እንዳለብን ነገራቸው። «ኢማሙ ጋር ብንሄድ ምንም አይሰራም ሌላ መፍትሔ መፈለግ አለብን» አለ።
እናቴ ግን አባቴን ተቃወመች። «አይሆንም! ወደ ጠንቋይ አንሄድም አላህ ያላዘዘውን መንገድ አንከተልም» አለች። በትንሹም ቢሆን ኢማን የገባት ናት፡፡ በወላጆቼ መካከል ያለው ጭቅጭቅ ተጠናከረ። እኔ በመሬት ላይ ተጥዬ በውስጤ የሚቃጠለውን ስቃይ እየታገልኩ ከዚህ ሁሉ መከራ የምገላገልበትን ቀን አላህ እንዲያቀርብልኝ በልቤ እፀልይ ነበር፡፡
ከዚያ አደጋ በኋላ የቤታችን ወሬ ለመንደሩ ሁሉ ተሰራጨ። የቅርብ ጎረቤታችን የሆኑት ሴትዮ ወደ ቤታችን መጡ። እኚህ ጎረቤት በመንደሩ ውስጥ በብዙ ነገሮች ጣልቃ በመግባት የሚታወቁ ሴት ናቸው። እናቴን ለብቻዋ ጠርተው «እህቴ የልጅሽን ሁኔታ እያየሁት ነው ይህ በሽታ ተራ በሽታ አይደለም። በእኔ እምነት ከተማ ወረድ ብሎ የሚገኝ አንድ አዋቂ ሰው አለ እሱ ጋር ካልወሰዳችኋት ልጅቷ ትጠፋባችኋለች» አሏት።
እናቴ በጭንቀት ውስጥ ስለነበረች «ያ አዋቂ ሰው ማን ነው? ምን አይነት ሕክምና ነው የሚያደርገው?» ስትል ጠየቀች። ጎረቤታችንም «የተለያዩ እፅዋቶችንና ሚስጥራዊ ነገሮችን በመጠቀም የተሰረዘውን ነገር የሚፈታ ነው» ብለው መለሱ። እናቴ በኢስላማዊ እምነቷ ላይ በትንሹም ቢሆን ጎበዝ ብትሆንም የልጇ ስቃይ ስለበዛባት አእምሮዋ በጥርጣሬ ተሞላ።
አባቴ የ ጎረቤታችንን ምክር ወዲያውኑ ተቀበለው። «ምንም ቢሆን መፍትሔ ከሆነ እንሞክረው» አለ። እኔ ግን ያን ጥቆማ ስሰማ በውስጤ ታላቅ ፍርሃትና ተቃውሞ ተፈጠረ። አላህ ያላዘዘውንና ያልፈቀደውን መንገድ መከተል መጥፎ ና አጥፊ መሆኑን በውስጤ አውቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የመናገር አቅም አልነበረኝም።
በማግስቱ ጠዋት አባቴ እኔን አስገድዶ ወደዚያ አዋቂ ሰው ለመውሰድ ተዘጋጀ። እኔም እያለቀስኩና እየተንቀጠቀጥኩ ከእነሱ ጋር ለመሄድ ተገደድኩ። ያ ጉዞ ግን ወደ ብርሃን ሳይሆን ወደ ባሰ ጨለማ የሚወስደኝ የመጀመሪያው የተሳሳተ እርምጃ ነበር...
#ፈጥነው_ይታከሙ_በቶሎ_ይዳኑ
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/freeeeeeeeeeeere
👆
ህክምና ለማግኘት👇
https://t.me/UstazulQallb
👆
ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇


