@Yeroreflect · 298 subscribers
ይህ ቻናል በተለየዩ ጉዳዮች ላይ የራሴን ምልከታ የማሰፍርበት ነው። በጽሑፎቹ መንፈሳዊ፣ ሃገራዊና ማህበራዊ ነክ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ። መልካም የሆነ ተጽዕኖ መፍጠር ከቻለ ብዕሬ ለምን ይለጎም?
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/YeroreflectIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created August 29, 2019per Telegram
We have been tracking it since September 8, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
ለስራ በሄድኩበት ከተማ እራት በልቼ ብቻዬን ወደ ማደሪያዬ ስፍራ ሳዘግም አንድ ሃሳብ ውልብ አለብኝ። "ዛሬ ያለሁት 'እኔ' ከአስር ዓመት በፊት ሁኜ ቢሆን ምን ይፈጠር ይሆን?" የሚል። አወጣሁ፣ አወረድኩ። ብዙ "ሊሆኑ ይችሎችን" አሰብኩ። በመጨረሻም አንድ ነገር ገባኝ ዛሬ ያለሁት 'እኔ' ያኔ ኑሬ ቢሆን ዛሬ ያለሁትን 'እኔ' እንደማላገኘው። ዛሬ ላይ ምን አይነት 'እኔ' እሆን ነበር? አላውቅም፤ ግን የተለየ 'እኔ' ለመሆኔ አያጠራጥርም። አውቃለሁ፤ ብቻ መሆን ብዙ ያፈ…
"The Mountain Is You" የሚል ተወዳጅ መጽሐፍ አለ። የመጽሐፉ ዋና ሃሳብ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከስቃይ ጋር ስለመቆራኘት ዝንባሌ ስለማዳበራቸው ነው። ይህ ቁርኝት ደግሞ ስቃይን ከለመደ የስሜት ቁርኝት (emotional attachment) የሚመጣ ነው። እንደ መጽሐፉ አባባል፤ አንዳንድ ሰዎች unconsciously ስቃይን ይመርጣሉ። ለእነርሱ ደስታና ተድላ ባዕድ፤ ስቃይ ደግሞ የተላመደ ቤተኛቸው ነው። አርሰናል ላለፉት 22 ዓመታት የዋንጫ ጥም ውስጥ ኖሯል። በተደጋጋሚ …
ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት ከካህናት አለቆች መካከል አንዱ ብትሆኑ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ መሆኑን ብትረዱ፣ ነገር ግን መምጣቱ በሞቱ ሰውን ለማዳን እንደሆነ ቢገለጥላችሁ የፋሲካው ሰሞን በነበረው ሁነት ምን አይነት ሚና ይኖራችሁ ነበር? አለጥፋቱ ወደ መስቀል ከመላክ የዘለለ ሌላ አማራጭ ይኖራችኋል? እርሱ አይሙት እኔን ጨምሮ መላው የሰው ልጆች ወደ ጥፋት ይሂዱ ብላችሁ ትበይኑ ነበር? ወይንስ ጻድቁን ወደ መስቀል እንዲሄድ ትፈቅዳላችሁ? በጊዜው የነበሩት የካህናት አለቆች ስላላወቁትና ስላልተቀበሉት በቅናት አሊያም ለሕጋቸው ወግነው ለሞት አሳልፈው እንደሰጡት ሁሉ እኛም ክርስቶስ መሆኑ አውቀነው እንኳን ቢሆን እንዳይሞት የመተው ድፍረት እናገኝ ይሆን? ምናልባት እንደ ጲላጦስ እጃችንን ከመታጠብ የዘለለ ለፍትህ የሚያቆም ጥሩነት የሚገኝብን አይመስልም። በኢየሱስ መሞት በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ማናችንም በእነርሱ ወንበር ብንሆን ከተጠያቂነት የምንድን አልነበርንም። እንደውም የመሲሑን መሞት አስፈላጊነት አስቀድመን ተረድተን ከሆነ ከፈራጆቹ ግንባር ቀደምነት የሚመልሰን ያለ አይመስልም። እናም የመስቀሉ ሞት በአይናችን ፊት ውልብ ባለ ጊዜ ራሳችንን ንጹህና ምስኪን አድርገን እነኛን የካህናት አለቆችና ሹማምንቶችን ከፉ አድርገን አንመልከታቸው። እኛም ከእነዛ ክፉነት የተለየ ብዙም ደግነት አይኖረንም ነበር። እርሱን ከመግደል ወይም አሳልፎ ከመስጠት የሚመለስ አቅም የለምን። እርሱ ግን ይህን ሁሉ እያወቀ ለእኛ ከመሞት ወደኋላ አላለም። ሁለት የተቃረኑ እውነቶች አሉ፤ እኛ ኢየሱስን ከመግደል የማይመለስ ራስወዳድነት፤ እርሱ ለገዳዮቹ ከመሞት የማይመለስ ፍቅር! ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም! መልካም የትንሣኤ መታሰቢያ በዓል