ለስራ በሄድኩበት ከተማ እራት በልቼ ብቻዬን ወደ ማደሪያዬ ስፍራ ሳዘግም አንድ ሃሳብ ውልብ አለብኝ። "ዛሬ ያለሁት 'እኔ' ከአስር ዓመት በፊት ሁኜ ቢሆን ምን ይፈጠር ይሆን?" የሚል። አወጣሁ፣ አወረድኩ። ብዙ "ሊሆኑ ይችሎችን" አሰብኩ። በመጨረሻም አንድ ነገር ገባኝ ዛሬ ያለሁት 'እኔ' ያኔ ኑሬ ቢሆን ዛሬ ያለሁትን 'እኔ' እንደማላገኘው። ዛሬ ላይ ምን አይነት 'እኔ' እሆን ነበር? አላውቅም፤ ግን የተለየ 'እኔ' ለመሆኔ አያጠራጥርም። አውቃለሁ፤ ብቻ መሆን ብዙ ያፈላስፋል። 😊
May 25, 2026 177