The Mountain Is You" የሚል ተወዳጅ መጽሐፍ አለ። የመጽሐፉ ዋና ሃሳብ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከስቃይ ጋር… — yero's reflections/ የየሮ ንጽረቶች — TG.ME

"The Mountain Is You" የሚል ተወዳጅ መጽሐፍ አለ። የመጽሐፉ ዋና ሃሳብ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከስቃይ ጋር ስለመቆራኘት ዝንባሌ ስለማዳበራቸው ነው። ይህ ቁርኝት ደግሞ ስቃይን ከለመደ የስሜት ቁርኝት (emotional attachment) የሚመጣ ነው። እንደ መጽሐፉ አባባል፤ አንዳንድ ሰዎች unconsciously ስቃይን ይመርጣሉ። ለእነርሱ ደስታና ተድላ ባዕድ፤ ስቃይ ደግሞ የተላመደ ቤተኛቸው ነው። አርሰናል ላለፉት 22 ዓመታት የዋንጫ ጥም ውስጥ ኖሯል። በተደጋጋሚ እጁ የገባው ዋንጫ እየተነጠቀ ደጋፊውን ክፉኛ ሲያማርር ከርሟል። የሚገርመው ግን በእነዚህ ዓመታት የአርሰናል ደጋፊ ቁጥር እጅግ ጨምሯል። አብዛኛው አዲሱ ትውልድ ደጋፊ አርሰናል ትላልቅ ዋንጫ ሲያነሳ አይቶ አያውቅም። ጥያቄው ታዲያ እዚህ ጋር ነው፤ እንዴት 22 ዓመት ዋንጫ ያልበላ ክለብ ያን ሁሉ ደጋፊ አፈራ? ምናልባት "The Mountain Is You" መጽሐፍ እንደሚለው፤ ከስቃይ ጋር የመቆራኘት ዝንባሌ ያላቸው ሁነው ይሆን? እንጃ! የሆነ ሁኖ አሁን አርሰናል ከዋንጫ እጦቱ ተፈውሷል... 🏆 እንግዲህ የደጋፊው ቁጥር ይጨምር ይሆን የምናየው ይሆናል? 😂 ለማንኛውም አርሴዎች እንኳን ደስ አላችሁ

May 20, 2026 239 1