አንዳንድ ሰዎች ማግባት እንዳለብኝ ሊያሳምኑኝ ሲሞኮሩ....
"ምን መሰለህ ካገባህ በተለይ ከወለድክ በኋላ የምትኖርለትን አላማ ታገኛለህ።"
ሳላገበ 3,467 የምኖርበት ምክንያቶች ያሉኝ ወንድማችሁ በውስጤ ሳቅ እያልኩ መካሪዎቼን ላለማስቀየም አንገቴን "አሁን ገባኝ" በሚል መልኩ እነቀንቅላቸዋለሁ።
በእርግጥ ልፉ ቢላቸው እንጂ እኔ እንደሆንኩ ማግባት ምንም ጥቅም የለውም ቢሉኝም እንኳን ማግባቴን አልተውም። ኧረ እንደውም ጋብቻን የሚከለክል ሕግ ቢወጣ ራሱ ሕጉን ጥሼ አገባለሁ።
እና ምን ለማለት ነው፤ ወዳጆቼ እኔን ለማሳመን ጉልበታችሁን አታባክኑ።
11
4August 17, 2025 428 2