ልጅ እያለሁ፤ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ክረምት ላይ ይመስለኛል። የዳንኤል ዓምደሚካኤል ቁጥር ሶስት አልበም ቤታቸን በብዙት ይደመጥ ነበረ...ታዲያ በእነዛ የክረምት ጊዜያት ግቢያችን ውስጥ እየተጫወትኩ ከዛ አልበም የሳበኝን አንዱን መዝሙር ደጋግሜ መዘመርን አዘወትር ነበር። አዘማመሬም ሆነ እየዘመርኩ የተጫወትኳቸውን ጫወታዎች አሁን ድረስ ፊቴ ድቅን ይላሉ። "መች ረሳው መች ዘነጋው ሁሉንም አስታውሳለሁ ከህጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቼለሁ....." እያልኩ አንጎራጉራለሁ። አሁን ላይ ሳስበው የሚያስቀኝ ጥያቄ ወደ አእምሮዬ ይመጣል "ከህጻንነቴ ጀምሮ ያልኩት ግን ዬትኛውን ህጻንነት ነው?" ያኔ እኮ ገና ህጻን ነበርኩ። ብቻ በእነዛ የልጅነት ወራት የእኔ ተወዳጅና ተመራጭ ዝማሬ ይሄ ነበር። ይህ ያስታወሰኝ ከሰሞኑ አንድ ወጣት በአንድ መድረክ ላይ ይህንን ዝማሬ ስትዘምር መስማቴ ነው። ዳግም እንደ ልጅነቴ ያንን ዝማሬ ጠዋት ማታ ማዳመጥና ማንጎራጎር ሲቀናኝ። የአሁነኛው ግን ከዛን ጊዜ የሚለየው ከህጻንነቴ ጀምሮ የመራኝን የእግዚአብሔር እረኝነት በትክክል እያሰላሰልኩ መሆኑ ነው። መዝሙሩ ደስ ስላለኝ ብቻ ሳይሆን፤ በእያንዳንዱ የሕይወቴ ምዕራፍ ውስጥ የእግዚአብሔር የመልካምነቱ፣ የምህረቱ፣ የቸርነቱና የፍቅሩ አሻራ ደምቆ ስለሚታየኝ ነው። ከብዙ ውድቀትና ጥፋት እንደ ጠበቀኝ፣ ከአያሌ መሳቶች እንደመለሰኝ ስለማውቅ ነው። ለሞኝነቴና ለአላዋቂነቴ አሳልፎ አልሰጠኝም፤ ለፈቃዴ አልተወኝም። ከልጀነት ወራት ጀምሮ ያለፍኩበትን ጎዳና መልስ ብዬ ስመለከት እዚህ ለመድረሴ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ ምክንያት እንደሌለ ሲገባኝ ማንጎራጎሬን እቀጥላለሁ "የራራልኝ በድካሜ ሃይል የሆነልኝ አቅሜ ጎኔ ቁሞ ያበረታኝ ማን ነበረ ከአንተ በላይ . . . ሁሉም አልፎ እዚህ መድረሴ በአንተ እንጂ መች በራሴ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ ሁልጊዜ ዘምራለሁ መች ረሳሁ መች ዘነጋሁ ሁሉንም አስታውሳለሁ ከህጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ..... https://youtu.be/Ff4xG3kFyfw?si=vPMW1vvWgLkVJh6u
YouTubeLidia Anteneh @ Dink Sitota Worship Night 2023 "Meche Resahu" Original Song by Daniel A/MichaelLidia Anteneh @ Dink Sitota Worship Night 2023 "Meche Resahu" Original Song by Daniel A/Michael & "Alresawum" By Tekeste Getnetልጅ እያለሁ፤ ሁለተኛ ክፍል ጨርሼ ክረምት ላይ ይመስለኛል። የዳንኤል ዓምደሚካኤል ቁጥር ሶስት አልበም ቤታቸን… — yero's reflections/ የየሮ ንጽረቶች — TG.ME
March 8, 2024 1K