@Informations_Technology · 1.3K subscribers
ጠቃሚ የቴክኖሎጂ እውቀት ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎችን ያግኙ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://m.youtube.com/channel/UCCtQ8TSLVzUagfV4LjpQoCQ Facebook link👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿 https://www.facebook.com/Technologynews.M
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/Informations_TechnologyIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created October 9, 2020per Telegram
We have been tracking it since August 24, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
4 advertisers placed 4 creatives in this channel · est. CPM $1–5.
ፌስቡክ👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿👇🏿 https://www.facebook.com/Technologynews.M ዩቱበ፦👇🏼👇🏼👇🏼 https://m.youtube.com/channel/UCCtQ8TSLVzUagfV4LjpQoCQ
ኮምፒዉተራችሁ በጣም slow ነው? እንዴት ማስተካከል ትችላለችሁ? ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የገዛነው ኮምፒውተራችን ፍጥነት በመቀነስ ማለትም ቶሎ ምላሽ ባለመስጠት እና ረጅም ጊዜ load በማድረግ በጣም ቀላል የሆኑ ስራዎችን እንዳንሰራ ሲያደርገን ይስተዋላል። ኮምፒውተራችን ለምን slow እንደሆነ እና ችግሩን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል መረዳት ከባድ ስራ መስሎን ሊታይ ይችላል። ዛሬ አይዲዛየር ኮምፒውተር ቀርፋፋ ፒሲን እንዴት በደቂቃዎች ውስጥ ማስተካከል ሚያስችሉንን ቀላል መንገዶች ይገልጸላችኋል፣ ፈጣን ውጤት ያገኛሉ! ላፕቶፔ ቀርፋፋ የሆነው ለምንድነው? በጣም ብዙ ፕሮግራሞች ከጫኑ ኮምፒውተርዎ መቀዛቀዝ መጀመሩን ሊያስተውሉ ይችላሉ። በርካታ ፕሮግራሞችን ለማሮጥ ብዙ processing ሃይል ይፈልጋል ማለትም speed እና performance ባዛው ልክ ይገደባል። ይህንን ለማስተካከል ሁለት ነገሮችን ማድረግ እንችላለን። 1.የሚሰሩትን ፕሮግራሞች ብዛት መቀነስ እና 2.የኮምፒተርዎን memory እና processing power መጨመር። 1. የኮምፒተርዎን ፍጥነት የሚቀንሱ ፕሮግራሞችን ይለዩ ** 2. ዲስክዎን ያጽዱ ** 3. ጥቅም ላይ ያልዋሉ ፕሮግራሞችን uninstall ያድርጉ ** 4.Start-up programዎችን ማቆም ** ኮምፒውተራችን ስንገዛ በራሳቸው ፍቃድ ከበስተጀርባ automatically የሚሮጡ ፕሮግራሞች ተጭኖበት ሊመጣ ይችላል። እነዚህ የሚፈልጓቸው እና አልፎ አልፎ የሚጠቀሙባቸው ፕሮግራሞች ቢሆኑም automatically መጀመራቸዉ የኮምፒውተራችን ፍጥነት ላይ ተጽዕኖ ሊያመጡ ይችላሉ። ስለዚህ start-up programዎችን ማቆም አስፈላጊ ነዉ። ፕሮግራሞችን automatically እንዳይጀምሩ ለማድረግ ይህንን steps ይከተሉ:- A.taskbar ላይ ሄደው ባዶ ቦታ ላይ Right-click ያድርጉ B.ከተዘረዘሩት ዉስጥ Task Manager የሚለውን ይምረጡ C.Startup የሚለውን tab ይምረጡ D.Automatically መጀመር የሌለባቸውን item ከተዘረዘሩት ፕሮግራሞች መሀል ይምረጡ። የመረጡት ላይ ሄደው Right-click ያድርጉ E.Disable የሚለዉን ይምረጡ Automatically እንዳይጀመሩ ካረጋችሁት ፕሮግራሞች ብዛት ላይ በመመስረት፣ ኮምፒዉተሮ ቶሎ መከፈት አለበት( ፈጣን startup time ማየት አለብዎት።) ከከፈተም በኋላ በbackground የሚሮጡ ፕሮግራሞች የሚጠቀሙት resource ስላነሰ የlaptopዎ ፍጥነት ይጭምራል። 5.Temporary ፋይሎችን ማጥፋት ** Internt ላይ አንድ website በጎበኙ ቁጥር ጊዜያዊ ፋይል ኮምፒውተርዎ ላይ ሊጫን ይችላል። እነዚህ ፋይሎች websiteቱን ለቀው ከወጡ በኋላ አያስፈልጉንም ፤ ስለዚህ እነሱን መሰረዝ storageዎን free ያደርገዋል። ጊዜያዊ ፋይሎችዎን ለመሰረዝ እነዚህን መመሪያዎች ይከተሉ :- A.Task Bar ላይ ካሉት iconዎች መሀከል File Explorer ይምረጡ B.Click This Pc or Computer or My Computer C.Local Drive ይምረጡ፤ አብዛግኛዉን ጊዜ C:Drive ነዉ። D.ከተዘረዘሩት ፎልደሮች መሀከል Windows የሚለዉን ይምረጡ። E.ከዛም ከተዘረዘሩት ፎልደሮች መሀከል Temp የሚለዉን ይምረጡ። F.እዛ ፎልደር ዉስጥ ሚገኙትን ሁሉንም ፋይሎች መርጠው Delete ያድርጉዋቸው። ( ሁሉንም ፋይሎች ለመምረጥ Ctrl + A key መጫን ይችላሉ) ይህንን ማድረግዎ Storage driveዎ በፍጥነት ፋይሎችዎን እንዲያገኝ ያስችለዋል። 6.Solid state drive(SSD) ይጠቀሙ ** ላፕቶፖዎ HDD የሚጠቀም ከሆነ ወደ SSD ይቀይሩት ። ማንኛውንም ስራ SSD እስከ 6 እጥፍ ያፋጥናል። በተጨማሪም ቀላል እና ትንሽ የbattery power ይጠቀማሉ ከHDD አንጻር። 7.RAM ይጨምሩ** በቂ RAM የሌላቸው ላፕቶፖች በጣም ቀላል የሆኑትን ስራዎች እንኳን ለመስራት ሊታገሉ ይችላሉ። 8.ሀርድ ዲስክዎን defragment ያድርጉ ** ላፕቶፕዎ HDD የሚጠቀም ከሆነ ሀርድ ዲስክዎን defragment ማድረግ ሊያስፈልገው ይችላል። HDDዎች መረጃን በቅደም ተከተል ነው ሚያነቡት ። ስለዚህ መረጃን በበርካታ ቁርጥራጭ ቦታዎች ማስቀመጡ መረጃውን ለመግኘት የሚፈጀውን ጊዜ በዚያው ልክ ይጨምራል። የእርስዎን ሃርድ ድራይቭ defragment (defragring) ማድረግ driveዎ ላይ ያለውን መረጃ በሎጂካዊ ፎርሜሽን ያስቀምጠዋል፤ ይህም መረጃዉን በፍጥነት ለማግኘት ያስችለዋል። ሃርድ ድራይቭዎን defragment ለማድረግ ምርጡ መንገድ የMicrosoft® Windows® Disk Defragmenter መገልገያ መጠቀም ያስፈልጋል። ሃርድ ድራይቭዎን defragment ለማድረግ እነዚህን ፈጣን stepዎች ይከተሉ። 1ኛው መንገድ ፦ Disk Defragmenter automatically እንዲሮጥ ማድረግ Disk Defragmenter መች መች automatically እንዲሮጥ መቀየር/መወሰን ከፈለጉ እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ፡- A.Click the Start menu or Windows button B.Defragment your hard drive ብለው ጽፈው የመጣውን ምርጫ click ያድርጉ C.ከመጣው dialog window ላይ change settings የሚለውን button ይጫኑት D.ኮምፒዩተሩ on ሆኖ በተለምዶ ብዙ ስራ ማይሰራበትን ቀን እና ሰዓት ይምረጡ ። sleep ሚሆንበትም ሰዓት መሆን ይችላል። E.Click OK 2ኛው መንገድ ፦ ዲስክዎን እራስዎ manually ዲፍራግመንት እራስዎ manually ዲፍራግመንት ከማድረግዎ በፊት analyze ማድረግ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ ከላይ ከ1 – 2 የተገለጽትን stepዎች ከተከተሉ በኋላ analyze ሚለውን button መጫን ። ይህንን ሲያደርጉ ላፕቶፖዎ ዲስኮ defragment ያስፈልገው እንደሆነ የሚገልጽ report genert ያደርግላችኋል። manually ዲፍራግመንት የሚያስፈልገው ከሆነ Defragment disk የሚለውን button ይጫኑት ። Defragment ከተደረገ በኋላ የኮምፒዩተርዎ performace ለውጥ ሊያሳይዎ ይገባል። 9.Web Browserዎን ወይም Internet connectionዎን check ያድርጉ ** በጣም ብዙ Add-on እና extensions browseraችን ላይ መጫን ፍጥነት ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል። እንዲሁም Latest version መጠቀም አስፈላጊ ነዉ። add-ons or extensions ማጥፊያ መንገዶች በሚጠቀሙት browser ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ሁሉም browserዎች ላይ ይህንን የሚያስችል ሜኑ ማግኘት ከባድ አይደለም። 10.የላፕቶፖዎን fan ያጽዱት ** Fan ውስጥ አቧራ ሲከማች የአየር ፍሰትን ይከለክላል እናም ኮምፒውተርዎ እንዲሞቅ ያደርገዋል ፤ ስለዚህም systemዎ performance በመቀነስ ላፕቶፕዎ እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል። በአጠቃላይ ቀርፋፋ ላፕቶፕን ለማስተካከ ግዙፍ ለውጦችን ማድረግ አያስፈልግዎትም። አፋጣኝ እና ዘላቂ ውጤቶችን የሚያቀርቡ ጥቂት ትናንሽ፣ ሊቆጣጠሩዋቸው የሚችሉ ከላይ የተዘረዘሩትን መፍትሄዎችን ይተግብሩዋቸው።