የኮምፒውተራችንን Hard Drive እንዴት በቀላሉ ፓርቲሽን(partition) መክፈል እንችላለን? በመጀመሪያ ፓርቲሽን በመክፈላችን ምናገኛቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ብለን ስናስብ እንደየ ፍላጎታችን ሚለያይ ሲሆን ለሁላችንም ሚሰጠን ዋናው ጥቅም ቢኖር ፉይላችንን ከ ሲስተም ፋይል ያሉ ፋይሉችንን ለይተን በማስቀመጥ በተላያዩ ምክንያት ቡት ማረግ ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን መነሳት ሲያቅተው ልናጣ ምንችለውን ፉይል ለመከላከል የምንጠቀምበት መንገድ ነው ለምሳሌ ከፋብሪካው እንደመጣው በ C: partiton ብቻ እየተጠቀምን ቢሆንና በቫይረስ ምክንያት ሲስተም ፋይል ቢጠፋ ሌሎች ፐርሰናል ፉይሎችን አጣን ማለት ነው። ስለዚህ በቀላሉ እዛው ፓርቲሽን በመፍጠር የግል ፉይል ለብቻ C: ፓርቲሽን ለብቻ አድርገን በመጠቀም ፋይላችንን መከላከል እንችላለን ይህን ካልን ስለ ፓርቲሽን እንዴት ዊንዶውስ ባዘጋጀልን disk managment በመጠቀም እንዴት መስራት እንችላለን ሚለውን ላሳያችሁ ወደድኩ በመጀመሪያ ባክአፕ መውሰድ አስፈላጊ ነው ምንም እንኳ ፕሮሰሱ ፋይል ባያጠፋብንም ለጥንቃቄ ሲባል ወስደን መጀመር አለብን በመቀጠል ወደ my computer iconላይ ራይት ክሊክ አርገን manage ሚለውን ክለክ ስናደርግ አዲስ ዊንዶው ይከፈትልናል ማለት ነው። በግራ ባለው ዝርዝር ውስጥ disk managment ሚል በመፈለግ ያንን እንከፍታለን በመቀጠልም በሚከፈተው ዊንዶው ውስጥ መሀል ላይ ሁኖ ከታች ባለው ቦታ ላይ ያልተከፈለው ፓርቲሽን በ ሰማያዊ ይታየናል ስለዚህም ማድረግ የፈለግነውን ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ በሚመጡት ዝርዝሮች ውስጥ shrink volume የሚለውን በመምረጥ በሚከፈትልን ዊንዶው መሰረት እንደምን ፈልገው ሳይዝ በማስገባት ሌላ አዲስ ፓርቲሽን እንፈጥራለን። ⚠️ ማሳሰቢያ የ disk size ስባስገባ ቁጥሩ በ Mega byte(MB) ነው የሚቀመጠው ስለዚህ ለምሳሌ 100 GB ማድረግ ከፈለግኩኝ 1024,000 ብየ ቁጥሩን ማስገባት አለብኝ ማለት ነው ወይም 200GB ማድረግ ብፈልግ 2048,000 ማለት አለብኝ። የ 1 GB ማለት 1024 MB ስለሆነ። ⚠️ ይህንን finish ብለን ከጨረስን በኋላ የከፈትነው ፐርቲሽን እዛው disk managment ውስጥ በጥቁር ከለር ይታየናል ስለዚህ ይህንን ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ የጀመረነውን ፓርቲሽን መፍጠር ለመጨረስ እንጀምራለን። ስለዚህ ራይት ክሊክ ስናደርግ new volume የሚለውን ስንነካ አዲስ ዊንዶ ይመጣል ስለዚህ ምንም ነገር ሳንነካ nextን ብቻ በመጫን መጨረሻም ላይ finish ስንጫን አዲሱ ፓርቲሽን my computer ውስጥ መታየት ይጀምራል ማለት ነው ። ▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ ቻናሉን ሼር አድርጉ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ እውቀት ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎችን ያግኙ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://m.youtube.com/channel/UCCtQ8TSLVzUagfV4LjpQoCQ ▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
Information Technology: post #197 — TG.ME
August 12, 2022 2.2K 6