አንዳንዴ በሆኑ አጋጣሚዎች በንባብም ይሁን በደርስ ጊዜ ያወቅሁት አንዳንድ ነገሮች ላጋራችሁ አስብና ግን ሁላችሁም የምታውቁት እየመሰለኝ እተዋቸዋለሁ ግን ከሆነ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችሁ የምታውቁት እውነታውን ሳይሆን እውቀቱን ያገኛችሁበት ሰውዬ የርሱ እውቀትና አቋም ቢቻ ነው።
ይህም የገባኝ ከአንዳንድ የንጽጽር ወንድሞች ምንም አያቁም ብለው ከሀቁ ያፈነገጣ መልስ በሚመልሱበት ጊዜ እንዲሁም ሰነድ አልባ የሆኑ ሀዲሶችን እንደማስረጃ ሲጠቀሙ እና ለወገኖች መልስ ሲሰጡ አንጀታችሁ ርሶ ስታመሰግናቸው ያየሁኝ ጊዜ ነው አብዛኛው አድማጭ ጃሂል ነው የሚለውን የተረዳሁት።
በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ በሌላ ጊዜ ያንኑ ጥያቄ ተጠይቄ ትክክለኛውን መልስ ስሰጥ ተሳስተሃል ያሉኝ እኔ የማውቀውን ያውቃሉ ብዬ ያልኳቸው አድማጮች ነበሩ። ቁርአኑን ከፍቼ ያሳየኋቸውና ያስነበብኳቸው ጊዜ ኮመንቱ ላይ ተሳስተሃል በሚለው ጽሑፍ ሲያጨናንቁት የነበሩ ታዳሚያን በሕብረት ነበር ዝም ያሉት። ግን ሀቅ ያለው ኪታብ ላይ ነው! ነቃ ደንገጥ እንበል እንማር እስከመቼ የማንም ጃሂል መቀለጃ የምነንሆነው።
https://t.me/thepath_of_truth




