ብልጥ ማለት ለቀጣዩ አለም ቤቱ አሻራውን የሚያኖር ነው! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿الْكَيِّسُ… — የሐቅ መንገድ (the path of truth)የንፅፅር ቤት — TG.ME

ብልጥ ማለት ለቀጣዩ አለም ቤቱ አሻራውን የሚያኖር ነው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿الْكَيِّسُ  مَنْ  دَانَ نَفْسَهُ  وَعَمِلَ لِمَا بَعْدَ الْمَوْتِ، وَالْعَاجِزُ مَنْ أَتْبَعَ نَفْسَهُ هَوَاهَا، وَتَمَنَّى عَلَى اللَّهِ﴾

“ብልጥ ማለት ነፍሱን ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው (ህይወቱ) የሰራ ነው። ሰነፍ ማለት ነፍሱን ዝንባሌዋን እያስከተላት በአላህ ላይ አጉል የተመኘ ነው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 2459
ብልጥ ማለት በዚህች ዓለም ገንዘብን፣ ዝናን፣ ወይም ምቾትን የሰበሰበ ሳይሆን፦ ነፍሱን ገዝቶ፣ ፍላጎቷን ተቆጣጥሮ፣ ከሞት በኋላ ላለው ዘላለማዊ ህይወት የሚሰራ ሰው ነው።

እውነተኛ ብልጠት ቤት፣ መኪና፣ ዲግሪ መሰብሰብ ብቻ አይደለም። እውነተኛ ብልጠት ለቀብራችን ብርሃን፣ ለመዝገባችን መልካም ስራ፣ ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ማስቀደም ነው።

"ሰነፍ ማለት ደግሞ ፦ ሁልጊዜ ነፍሱ የምትለውን እየተከተለ፣ ኃጢአት ውስጥ ሆኖ "አላህ ምህረት ያለው ነው" ብሎ በምኞት ብቻ የሚኖር ነው። ምኞት ያለ ስራ፣ ከንቱ ልፍት ነው።


https://t.me/thepath_of_truth
👍6🔥6❤3
September 3, 2026 362 1 3