ነቢያትን የሚልክ አምላክ
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيم
በማታው ውይይት ላይ ወገናችን ቃሌ የኢየሱስ አምላክነትን ያሳያሉ ብሎ ካነሳቸው አምስት Argumen_ቶች መካከል አራተኛው ነቢያቶችን ልኳል የሚል ነበር።
23. ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና። በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።
ማቴዎስ 21:23 (አማ54)
እዚህ ክፍል ላይ ማስተማር የጀመረው ትምህርት ነው ማቴ 23:39 ድረስ የቀጠለው ፦ ከዚም 23:34 ላይ ይህን ተናገረ
34. ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤
35. ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።
37. ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
ማቴዎስ 23:34-37 (አማ54)
ይህን የተናገረው ሲያስተምር መሆኑን ከተረዳን ታዳ ትምህርቱ ከየት ነው? ሲባል ከላከው ከአብ ነው።
16. ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤
ዮሐንስ 7:16 (አማ54)
ኢየሱስ ከራሱ ምንም አይናገርም አብ እንዲህ በል ያለውን ነው የሚለው፦
49. እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
50. ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
ዮሐንስ 12:49-50 (አማ54)
ኢየሱስ የአብ አፈ ቀላጤ ነው። አብ በቀጥታ ስለማይናገር በኢየሱስ በኩል ይናገራል።
24. የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 14:24 (አማ54)
ስለዚህ "ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤" የሚለው ቃል የአብ እንጂ የኢየሱስ አይደለም። ኢየሱስንም ጨምሮ ሁሉንም የላከው የነቢያት አምላክ አብ ነው። በብሉይ ኪዳን ለአባቶች በነቢያት ተናግሮ በአዲስ ኪዳን ደግሞ በኢየሱስ በኩል መናገር ጀመረ፦
1. እግዚአብሔር በቀድሞ ዘመናት በተለያዩ መንገዶች፥ በነቢያት አማካይነት ለአባቶቻችን ብዙ ጊዜ ተናግሮ ነበር፤
2. አሁን ግን በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ሁሉን ነገር ወራሽ ባደረገው በልጁ አማካይነት ለእኛ ተናገረን፤
ዕብራውያን 1:1-2 (አማ05)
"ለምኖ ነው የላከው" የሚለው መልስ እንደእኔ ተቀባይነት የለውም!
✍ወንድም ሷቢር
https://t.me/thepath_of_truth
4
2August 26, 2026 630 6 3