በዚህ ጊዜ Internet ተጠቃሚ ሆኖ ሌላው ቢቀር ስለ 2G , 3G , እና 4G ማያቅ ሰው ሚኖር አይመስለኝም፣ ዛሬ እነዚን በስም ብቻ ምናቃቸውን ግን አብዛኞቻችን ምን እንደሆኑ ማናውቀውን ነገር ይዤላችሁ ቀርብያለው
ከዛሬ 40 አመታት ጀምሮ 5 የተለያዩ የስልክ ኔትዎርክ Generation ኖረው ለማየት በቅተናል፣ እናም እነዚህ ኔትዎርኮች ምን እንደሆኑ እና እንዴት እንደነበሩ እንደሚከተለው ቀርቦላችዋል
1G
1G ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በ1980ዎቹ ነበር: ይህ ፈር ቀዳጅ የሆነው ኔትዎርክ Analogue Technology ነው የሚጠቀመው። ያኔ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሰራ ለድምፅ አገልግሎት ብቻ ታስቦ ነበር የተሰራው ፣ ትልቁ እና በጣም ከፍተኛ ፍጥነቱ 2.5kbps ነበር
2G
ስልኮች ትልቅ ለውጥ ያመጡት የምንጠቀመው ኔትዎርክ ከ 1G ወደ 2G ባደግንበት ሰአት ነበር : የሁለቱ ማለትም የ 1G እና 2G ትልቁ ልዩነት ለ Radio Signal 1G Analogue ሲጠቀም 2G ደሞ Digital ነው የሚጠቀመው። ይህ በ1990ዎቹ ይፋ የሆነው ኔትዎርክ ከመጣ በዋላ ትንንሽ ዳታ የሚጠቀሙትን እንደ SMS እና MMS ተጠቃሚዎች ሆነናል : ኔትዎርካችን ከ1G ወደ 2G መቀየሩ ከያኔ ጀምሮ እዝከዛሬ ምንጠቀማቸውን እንደ call hold, Conference call, እንድንጀምር አርጎናል። ትልቁ እና በጣም ፈጣን ፍጥነቱ እስከ 64 kbps ነበር።
በመሃል 3G ከመምጣቱ በፊት እንደ 2.5G እና 2.75G ኔትዎርኮች መጥተው ነበር
3G
3G ኔትዎርክ በዚህ ሰአት ምድራችን ላይ ያሉትን ትላልቅ wireless ቴክኖሎጂዎች እንድናውቅ እና እንድንወዳቸው ምክንያት ሆኖናል : እንደ web browsing, email, video downloading......የመጡት በአብዛኛው በ smart ቀፎዎች አማካኝነት 3Gን ከተዋወቅም በዋላ ነው ፤ በ3G በጣም ብዙ በ2G ልናረግ ማንችላቸውን ነገሮች ማድረግ እንችላለን። 3G ይፋ የሆነው በ2001(g.c) ነው እናም ይህ ብዙ ነገር የቀየረው ኔትዎርክ ይፋ ከሆነ በዋላ በ ሜድያው ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር በብዙ ቦታ ትልቅ ለዋት መለወጥ ችልዋል : 3G እስከ 2mbps ሚያህል ፍጥነት አለው።
ልክ እንደ 2G, 3G ኔትዎርክም ወደ 4G ከማደጉ በፊት ወደ በመሃል 3.5G እና 3.75G ሆኖ ነበር
4G
ልክ ከላይ ሁለቱን ኔትዎርኮች እንዳነፃፀርነው 4Gም ከ 3G በጣም ይለያል : በጣም ለየት ያለ ፍጥነት በጣም ምርጥ የሆነ ጥራት አለው : በ4G ማይቻል ነገር የለም ።
ለ4G ከፍተኛ ፍጥነት ምንጠቀምበት ነገር እይተንቀሳቀሰ ከሆነ እስከ 100mbps ሲሆን ብዙም ሳንንቀሳቀስ ደግም እስከ 1Gbps ሊደርስ ይችላል
5G
5G በዚህ ሰአት በጣም ፈጣኑ እና በጥራት ማንም ማይወዳደረው ኔትዎርክ ነው : 5G ከ 4G እስከ 35 እጥፍ ፍጥነት አለው ያም ማለት 35Gbps ማለት ነው እንግዲ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Tech_Infoss