Tech Info🌍: post #2309 — TG.ME

Workday የተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት በሀከሮች የመረጃ ስርቆት አጋጠመው። Workday የHuman resource/የሰው ሀብት ማኔጅ ማድረጊያ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚያቀርብ የቴክ ድርጅት ሲሆን ይህ ድርጅት ሀከሮች የተጠቃሚዎችን መረጃ እንደሰረቁት ገልጿል። ስርቆቱ የተፈፀመውም ካሉት third-party customer relationship databases /የደንበኛ ግንኙነት መረጃቋት/ አንዱ ላይ ነው። ይህም ደግሞ እንደ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና ኢሜል አካውንት ያሉ መረጃዎችን የሚያስቀምጥበት ነው። ድርጅቱ እንደገለፀው የተሰረቁት መረጃዎች እንደ social engineering scam ላሉ አገልግሎቶች ሊውሉ ይችላሉ።

August 31, 2025 348