ፖሊ ግቢ ጉባኤ: post #4632 — TG.ME

ለምን የአብነት ተማሪዎች የደብረታቦር ዕለት ይዘክራሉ ? 🤔

በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፩-፱ ያለው የእግዚአብሔር ቃል :-

     ከስድስት ቀንም በኋላ ÷ ጌታችን ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሓይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እንሆም ሙሴና ኤልያስ ከርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ታዩዋቸው።

ጴጥሮስም መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መኾን ለእኛ መልካም ነው ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

እርሱም ገና ይህን ሲናገር እንሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እንሆም ከደመናው ውስጥም ''በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ርሱን ስሙት'' የሚል ድምፅ መጣ።

ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ጌታችን ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዐይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከጌታችን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። በማለት ይነግረናል።

ይህ ዕለት ከተሰዓቱ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በዚህ ወቅት ለሐዋርያት የክርስቶስ የባህርይ ልጅነት ከባህርይ አባቱ ተገልጧልና፣ እንዲሁም የባህርይ አምላክነቱን በመግለጥ በልባቸው የነበረውን ጥርጣሬ አስወግዶላቸዋልና፣ በተጨማሪም ነገረ ሥጋዌውን እንዲሁም ምስጢረ ሥላሴን ገልጦላቸዋልና።

የአብነት ተማሪዎችም አቤቱ በዚህ ዘመን ላለን ሐዋርያትን በመምሰል አርድዕተ ሊቃውንት ለሆንን ለእኛም ትምህርታችንን ግለጥልን፣ የራቀውን አቅርብልን የቀረበውንም አራቅልን በማለት በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ የደብረታቦር ዕለት ዝክር ይዘክራሉ።

ይህ ዕለትም በፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች በደመቀ እና በአማረ መልኩ ይከበራል ።

ለበዓሉ ማዘጋጃ ድጋፍ ለምታደርጉ :-
ንግድ ባንክ :-1000358173199
ተስፋሁን ገድፍ እሸቴ

እመሰ ረሳይኩኪ ቤተ ጉባዔ ለትርስዓኒ የማንየ
ወይጥጋዕ ልሳንየ በጉርዔየ   መዝ 136÷8

ትርጉም:-
  የአብነት ቤተ ጉባዔ ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣
ባላስብሽም ጉረሮየ ከተናጋየ ትጣበቅ።

እርስዎም ድጋፍ በማድረግ ፣ በዕለቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ❗️

ሰዓት:- ምሽት 11:00
📆ቀን:- ነሃሴ 13/12/2018 ዓ.ም
🏛ቦታ:- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ

አዘጋጅ :- ፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤‍🔥7❤5⚡1👍1🥰1🙏1🕊1
August 12, 2026 1.3K 1