ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል3⃣2⃣ .................. መጮህና… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል3⃣2⃣

.................. መጮህና መሳደብ ጀመረች ። በጣም ደንግጫለሁ በጣም !!!!
ያ ሁላ ፍቅር ሳቅ መግባባት የት ሄዶ ነው አልኩ ፈርቼ ።
ማለት ከቀናቶች በፊት እኮ በጣም ተግባብተን ተመሰጋግነን ነበር የተለያየነው !!
ግራ ገብቶኝ ሳሚን መመልከት ጀመርኩኝ እሱ ደግሞ በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ሊያረጋጋት እየሞከረ አይደለም ???
እኔ እንደማስበው ከሆነ ደግሞ ሴት ልጅን ከሚያረጋጉ ነገሮች አንዱ የምትወደው ሰው እቅፍ ውስጥ መቆየት ነው ።
ሳሚ ግራ በመጋባት ስሜት ይመለከተኝ ጀመር ከዛ እጆቼን እያጣመርኩ አቅፎ እንዲያባብላት ነገርኩት።

ሳሚ በዛ ላይ ጎበዝ አልሆነም !!! በስራ በባህሪ በሌሎቹ ነገሮች ላይ ጎበዝ ቢሆንም ግን ፍቅር መስጠት ላይ ደካማ ነው !!!
ስሜቱን መግለፅና ማሳየት ላይ የለበትም !
እንዴት እንደተጋቡ አላቅም በርግጠኝነት በሰላም የፍቅር ሰውነት ይመስለኛል !!!
ለምን እኔን ስታይ እንደተናደደች ሊገባኝ አልቻለም !!
ሳሚን ለማስረዳት ስለረቃኝ አጠገቤ ቆማ የለበስኩትን ጃኬት አጨማዳ ወደያዘችው ልዕልና ዞሬ
እቅፍ ናፍቋታል ቶሎ በይ እሷን ማቀፍ አለብሽ አልኳት ።
ነቄ ነገር ናት ቀልጠፍ ብላ ወደ ሰላም ሄደችና እናቴ እማ የኔ ቆንጆ እያለች እንደ ልጅ ፀጉሯን እየደባበሰች አቀፈቻት ።


እውነትም ናፍቋታል መሰለኝ ተረጋጋች። ስድቡን መግታቷን የተመለከተው ሳሜም ከሰላም እቅፍ ተቀብሎ ያባብላት ጀመር ።
ልዕልና ደግሞ ለአባቷ ካስረከበች ቡሀላ ወደኔ መታ ደረቴ ላይ ልጥፍ አለች ።
በሰአቱ ደስታም ድንጋጤም ነበር በርግጥ ግን ሌላ አማራጭ የለኝም አቅፌ ላባብላት ግድ ነው !!!!
ከስንት ቆይታዎች ቡሀላ ሰላም ተረጋጋችልን ።
ሳሎን ተሰብስበን ቁጭ አልን ብዙም ሳትቆይ ወደራሷ መመለሷ ደስ  ይላል ግን ውስጧ እንደቸረበሸ ነው ።
የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ እንዴ ?  አልኩኝ መልሳ ልትሰድበኝ እንደምትችል እያሰብኩኝ !
" የለም ግን ግን አልቻልኩኝም !!!" አለች ፊቷን ላይ ኮምጣጤ እንደጠጣ ሰው ጉምዝዝ አድርጋ ።
ለምን ?? አልኳት መልሼ
" መንፈሴን አስጨነቀቻት ቅርብ ናት አዎ ይሰማኛል እሷ ቅርቤ ናት ጨርቄን አስጥላኝም አረካችም መሠለኝ ቅርቤ ናት !!!!! ..........????" ማለት ጀመረች።



ሁለቱም ግራ ገብቷቸዋል ደንግጠዋል !!
ችግሩ ግን ምንም ልላቸው አልችልም እኔም ግራ ገብቶኛል ለምን እነዚህ ስሜቶች እንደተፈጠረ ማወቅ እፈልጋለሁ ።
አሁን ላይ የማረገው ነገርና የምሰጠው መፍትሄ ስላልነበረኝ እና ነገ የጊቢ ጉዞ ስላለ ወጣሁ !!!
በዛ ሰአት ላይ ጊብ እንደምንሄድ ሳስብ ወደቤት መሄድ ነበረብኝ ።
በጨዋታ መሀል ለምን እንደተናደደችብኝም ነግራኛለች ።
እ ኔም በቻልኩት አውርቻት ተነስቼ ወጣሁ ።
ወደ ቤት ስመለስ ስጠብቀኝ የነበረችው እናቴን ጠርቻት መቅሰስ  በላን !!
በቀጣዩ ቀን የት እንደምንላክ  እጣ ወጣና ለማየት ሁላችንም ወደ ትምህርት ቤት ሄድን ።
የዛኔ ደግሞ የመንግስትና የግል አንድ ላይ ስለምንፈተን የምንላክበት ቀንና ቦታ ከነስም ተዘርዝረ።
!!
ከሁሉም የሚያስጠላው  ነገር ግን ስም ሳነብ የሶስት ሰው ስም ማንበቤ አስደነገጠኝ ። ምክንያቱም እንዴት እንዴት እንደተገጣጠምን እንጃ ሶስታችንም አንድ ጊቢ ለመፈተን ተመድበናል ።
የሆነ ጎኔ ምን አገባህ ቢለኝሞ የሆነ ልቤ ግን አንድ ላይ መሆናችንን አልወደደውም!!!!
በቀጣይ ቀን ያለምንም አማራጭ ለመሄድ መዘጋጀት ጀመርኩኝ ።
ከእናቴ ተለይቼ አድሬ የማላቀው እኔ ገና ሳልሄድ እስከዘላለሙ የተለየዋት ይመስል ሆዴ እየባባ ነው ።
ግን ደግሞ ከእኔ በላይ እናቴ እንደሚከብዳት አውቃለሁ ።
ብቻዋን ነው የምታድረው ማንም የላትም አባቴ እንደሆነ አንዴ የተበላ እቁብ ሆኑዋል !!!

እኔ የሚያሳዝኑኝ እናቴ እንደ ሚስት ወግ ሳታይ አባቴ የአባትነት ክብር ሳያገኝ እድሚያቸውን መጨረሳቸው ነው ።
ብቻ ግን ለእናቴ ለአንድ ሳምንት ብቻ እንደምሄድ እየነገርኩ ላባብላት ሞከርኩኝ ።
ከዛም ሳምንቱን ሙሉ በሰራቻት ብር ዳቦ ቆሎ እና ኩኪስ ገዝታልኝ መጣች ።
አንዳንዴ የሷን ውለታ ሳልከፍል እሞት ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ !!
ከሌላት ላይ ሳትቀንስ እንደሰጠችኝ ያለኝን ሙሉ ልሰጣት እመኛለሁ !
እንደሌሎቹ እናቶች ልብስ ላለብሳት ሀበሻ ቀሚስ ልገዛላት እፈልጋለሁ!!!!!

አንዳንዴ የምር ራሴን አልወደውም ሁሌም ብር ሳገኝ ከራሴ ውጪ ለሷ ካልሲ እንኳን ገዝቼ አላቅም ። ???
ክብሯን ጥላ ሰርታ አስተምራኝ እኔ በማንም መንገደኛ ለመከበር ዘንጬ ለመውጣት ዋጋ እከፍላለሁ !!!"
እውነት ለመናገር ድህነት የሚያኮራ ነገር የለውም ግን በእኔ ልክ ሊታፈርበትም አይገባም እላለሁ አንዳንዴ ሳስበው ግን ማንኛውንም ነገር ስንጠላው ነው ከሱ ለመራቅና ቆርጦ ለመጣል የምንነሳሳው !!!

እኔም ድህነትን ለመቁረጥ ራሴን እያዘጋጀው ይመስለኛል ፈጣሪን የተደገፈዐአይወድቅም የምትል መርህ እየተከተልኩ ነበር ።
ለማትሪክ ፈተና ትኩረት አልሰጠሁኝም አላነበብኩም የማለፍ ፍላጎትም የለኝም !!!!
ወደኩም አለፍኩም ከእናቴ ስር ሆኜ ባገኘዋት እያገዝኳት መኖርን ነው የምፈልገው !!
መጥፎ ውጤት ላለማምጣት በሚል ብቻ ማታ ማታ ትንሽ አንብቤ እየተኛሁ አው የቆየሁት ።

እንግዲህ እኔ ለአንድ ሳምንት ስለሆነ ብዬ ሶስት ልብስ ያዝኩኝ ከዛ አንድ ነጠላ ጫማና አንድ ሽፍን ጫማ እና እናቴ የገዛችልኝን ቆሎና ዳቦቆሎ በጥቁሯ ቦርሳዬ ውስጥ ከትቼ እቃዬን አዘገጃጀሁ ።
" የትራንስፖርት ስንት ነው የሚያስፈልግህ ልጄ ተቀብዬ ልመጣ ነው ንገረኝ " አለችኝ እናቴ ።
ለኔ ሞራል እኮ ነው እንጂ እመልሳለሁ ብላ በአርባ አራቱ ታቦት ምላ ወይም ደግሞ እነዛን ጎረቤቶቿን ግማሽ ግማሽ ለምናልኝ ነው  የምታመጣው !!!
እሄኔ እኮ በልቧ መጀመሪያ ማንን ልጠይቅ ? እያለች ይሆናል
ፈጣሪ ግን ደግ ነው !!!!
በዛው ሰአት በዛው ቅፅበት የውጪው ቆርቆሮ ተንኳኳ ።
ከዛም እሷ በዛው ልትሄድ ሁለታችንም አብረን ወጣን።

ሳሚና ልዕልና  ነበሩ ።
በሰአቱ ግራ ገብቶኝ እዚህ ምን ታረጋላችሁ አልኳቸው ?
" ሰላምታ አይቀድምም እንዴ ልጅ ማይክ " አለና እኔንም እናቴንም ሰላም አለን ።
የኔ ቀበጥ  የዛኔ ጎብዛለች
" ደህና አደሩ የሚኪ እናት ልቀፎት " አለች እጇን እየዘረጋች ።
የኔ እናት ደስ ብሏት እቅፍ አረገቻት ።
እሷ ከመምጣቷ ፈገግታን ጫረችብኝ የሆነ የደስታ ምንጭ ነገር አላት !!!
" እንግዲህ ከፈቀዱልን ልጆትን ልንወስድ ነው የመጣነው " አለ ሳሚ በታላቅ አክብሮት ።
እንዴ ሳሚ እሜይ እኮ ኑሮ አጎሳቆላት እንጂ ከሰላም ታንሳለች ገና ወጣት ናት !! አልኩት አንቱታው የክብር እንደሆነ ባቅም ..
እናቴ ትንሽ ነገሩ አልገባትም መሠለኝ ቀና ብላ አየችኝ ።
እማ ልዕልና ማለት እሷ ናት እሱ ደግሞ ሳሚ አባቷ እኔና እሷ አንድ ጊቤ ነው የምንፈተነው እና የትራንስፖርት ከምናባክን በመኪናው አድርሶን ሊመጣ ነው  ብዬ በአጭሩ አስረዳዋት።
" ይሻላል ልጄ ?" አለችኝ ።
የሆነ ደስ የማይል ፊት አሳየችኝ አላመነቻቸው ይሆናል ብዬ ቀለል አረኩትና አዎ እማ ችግር የለውም በቃ ብዬ ከቤት ቦርሳዬን ይዤ ወጣሁና እናቴን ቻው ብያት እንደምትናፍቀኝና ራሷን እንድጠብቅ ነግሪያት ከጊቢ ወጣሁ ።


Share share
❤5🥰1
September 5, 2026 62