ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል3⃣0⃣ ..........ስትመጣ አየዋት ።… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል3⃣0⃣

..........ስትመጣ አየዋት ።
በሰአቱ ሳናስበው ከልዕልና ጋር ተቀራርበን  ነበር ።ከቤቱ ስንወጣ ራሱ እየተሳሳቅን ነበር ። እና ፊት ለፊቴ እሷን ሳያት ያገጠጠው ጥርሴ ባንዴ ሽሽግ አለ ።
ፊት ለፊት ስንገጣጠም የማያ ፊት ላይ ያየሁት ድንጋጤና የመሰበር ስሜት አስተውዬዋለሁ ።

ከእኔ በላይ ደግሞ ልዕልናን በሆነ አስተያየት ተመለከተቻት !!!
ምን ሆና ነው ብዬ ፈራሁ ።
ከዛ በፈጣጣው ወደኛ መጣች ።
ልዕልና ከዚህ በፊት አይታት ስለማታውቅ መታ ፊት ለፊቴ ስትቆም ግራ በተጋባ ፊት ዞራ አየችኝ ።
እኔም ግራ ገብቶኝዐበዝምታ ስመለከት ነበር ። እሷ ናት ልጅቷ ?" አለችኝ ።
ጭራሽ ደግሞ ከኔ መልስ እየጠበቀች ነበር ። ምን ማለት እንዳለብኝ እንኳን የማላቀው እኔ ሁለቱንም በየተራ ተመለከትኳቸው ።
አይናቸውን እኔ ላይ ተክለው ምላሽ ይጠብቃሉ ።

በዝምታዬ መፅናቴን የተመለከተችው ማያ
" ንገረኛ እሷ ናት አይደል እኔን ሳታድነኝ ጥለህ የመሄድህ ምክንያት  ??.
እሷ ናት አይደል በፍቅር የጣለችክ ከእኔ ያራቀችክ ?? እሷ ናት ማለት ነው ክብሬን ማንነቴን ልስጥህ ባልኩኝ እንቢ እንድትል ያደረገችህ ........." የሆነውንም ያልሆነውንም ቀባጠረች ።
የእኔ መልስ አሁንም ዝምታ ቢሆንም ልዕልና ግን በሰማችው ነገር የተደሰተች ይመስል ፍልቅልቅ እያለች ነበር  ወይኔ ማያ !!!!

ከእኔ መልስ አለማግኘቷ ሲገባት ራሷ መልሳ ለነገሩ ልክ ነህ እሷ ከእኔ በላይ ቆንጆ ናት አይደል በዛ ላይ የሚያምር አለባበስ አላት የሀብታም ልጅ መሆኗን እገምታለሁ በዛ ላይ ደግሞ አንተ እንደምትወዳት እሷም  እንደምትወድክ በእይታዋ ያስታውቃል !!!
ግን እምልልሀለሁ አክስቴ ራሱ የእኔን ያህል እንደምትወድህ እጠራጠራለሁ !!!!" ብላኝ አረፈችው ።

አክስቴ የምትለው እናቴን ነው ። ንግግሯ የሆነ ደስ ሚል ነገር ቢኖረውም ግን ልዕልና ትኩረቷንና እምነቷን እኔ ላይ እንድትጥል አድርጓት ነበር ።
እንደምወዳት መተማመን ጀምራለች ።
በጣም የምፈራው ነገር አሁን ባለሁበት ሁኔታ  የምሯን ነው ትወደኛለህ ? የሚል ጥያቄ ከልዕልና አፍ መስማት ብቻ ነው !!!!!
ምክንያቱም እንደዛ አለችኝ ማለት ፈጣሪ የሰጠኝን ዳግመኛ እድል ገደል እንደመክተት ነው ። ብትጠይቀኝ ልክ ማያን እንዳጣዋት እሷንምአጣታለሁ ።
ምክንያቱም እኔ ስሜቴን መግለፅ አልችልምምም!!!!

ወደ ማያ ስመልሳችሁ ግን ሳታስበው እንባዋ አመለጣት ። እሷ ስታለቅስ ማየት አልፈለኩም አንገቴን ደፋሁ ። ተጨማሪ ንግግር ሳታደርግ መልካሙን ሁሉ እመኝልካለሁ እሺ ትገባሀለች ያዝልቅላችሁ " አለችኝ ።
ወዲያው ደግሞ ወደ ልዕልና ዞራ
" አዎ ቆንጆ ነሽ አምናለሁ ግን ፀባይሽም እንደመልክሽ ይሁን እሺ ገባሽ አይደል !!!
ሀብትሼን በምንም ነገር ብታስከፊው አንቺ አትኖሪም ምክንያቱም ሁሌ በቅርብሽ አለሁ " ብላ ዝታ በመሀላችን አልፋ ሄደች ።
ምን ማረግ እንዳለብኝ አላውቅም ልክ ማያን ተከትዬ ልሄድ ስል ልዕልና በሚያሳዝን ፊት እያየችኝ ሚኪ አትወደኝም እኔን ?" አለችኝ ።
ወዲያው ማያ ወደኔ ዞራ ታየኝ ጀመር ።  በሁለቱ ሴቶች መሀል ሆኜ በየተራ አየዋቸው ።

ልክ ልሁን አልሁን ባላውቅም የግድ መወሰን አንዷን አጥብቄ መያዝ ነበረብኝ ግን መወሰን ከብዶኝ መሀል ላይ ቆሜ ስወዛገብ ነበር ።በዛ መሀል ከየት እንደመጣ አላውቅ የማያ አይኖች እንባ አዝለዋል አሳዛኝ የልዕልና ፊት ደግሞ እግሬን እንዳላንቀሳቅስ አስረውኛል ።
አዝናለሁ ሀብትሽ እድልክ አልቋል " አለችኝ ።

ማለት ማያ እስኪ ልትረጂኝ ሞክሪ እያልኩ አይን አይኗን ስመለከታት ፈገግ አለች ።
ምንድነው ብዬ ግራ በተጋባ ፊት እየተመለከትኳት እያለ ችግር አለ ?" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል ቀጥታ ወደ ማያ ሄዶ ግንባሯን ሳማት ።
ሰውዬው ፊቱ አዲስ ሆነብኝና ግራ ገብቶኝ ቆሜ እስክታስረዳኝ መጠበቅ ጀመርኩኝ አረ ምንም ችግር የለም ጓደኞቼ ናቸው ላስተዋውቅህ " ብላ ወደኔ ይዛው መጣችና ሀብታሙ ይባላል እንደ ወንድሜ በለው ጓደኛዬ ነው እሷ ደግሞ የሱ ሚስት ናት ያው አልተጋቡም ግን በቅርቡ ሰርጋቸውን እንበላለን " አለችው ። እሱም እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ በላይ እባላለሁ ባለቤቷ ነኝ " አለ ።

ጭራሽ አልጠበኩኝም የሰርጉ ቀን ትኩረት ሰጥቼም አላየሁትም ከዚ በፊት በሱፍ ምናምን ተወጣጥሮ አይቼው አቃለሁ ግን በኖርማል አለባበስ ሳየው የተለየ ሰው ሆነብኝ ።
እኔ ሳስብ የነበረው የሆነ ከባድ ሰው ትልቅና የሚያስፈራ ሰው አርጌ ነበር ።
በዛ ላይ አባቱን በደንብ ስለማቀው ልክ እንዳባቱ በገንዘብ የሚያምን ጉረኛ እና አፈር አይንካኝ የሚል አይነት ሰው መስሎኝ ነበርጰ። አልዋሽም ማያ በጣም ትበዛበታለች !!!!!!! ማያ እና እሱ አይገናኙም በርግጥ በዛ ላይ በእድሜ ቢያንስ አምስት አመት በላይ እንደሚበልጣት እገምታለሁ ግን እንዳሰብኩት አያስጠላም !!!

" በቃ አሁን እንሂዳ ለፈተና ማረፍ አለብሽ ነገ ትሄጃለሽ እኮ " ብሏት እጇቿን ይዞ መሄድ ጀመረ ። ሲጀመር እኔ ነኝ ጥፋተኛ በሰአቱ አዝኜላት እንጂ አፍቅሪያት አልነበረም ማለት ነው??? ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ !!!!
ከደቂቃዎች በፊት ልትሄድ ስትል ልከተላት እየቃታኝ ነበር የቆየው አሁን ግን አጇን ይዟት ሲሄድ ሳይ ምን አልባት የደስታ እንጂ ሌላ ስሜት አልተሰማኝም ነበር !!!!
አትሂጂ ብዬ ልለምናት ላስቆማትም ሆነ ልከተላት አላሰብኩም ሁላ !!
ለነገሩ ለምን ብዬ ???!!!

ሳስበው ትክክለኛ ነገር እንደሆነ ልቤ ስለሚያቀው ይመስለኛል ያልተከፋሁት !!
በሰአቱ ልጁን ሙሉ በሙሉ በአባቱ አይን ስላየሁት ይጎዳታል ትምህርቷን እንድታቋርጥ ያረጋታል በገንዘብ እንደገዛት ቢሰማውስ ?? እያልኩ እፈራ ስለነበር እንዲሁም ማያ በጣም ቆንጆ እና ጨዋ ምርጥ ባህሪ ያላት ሴት ስለሆነች የማይመጥናት እጅ ላይ ወደቀች ብዬ ስላሰብኩኝ እንዲሁም ደግሞ አሱን ያገባችው በእኔ ጥፋት ነው ብዬ ስላሰብኩ ይመስለኛል ያመመኝና የተጎዳሁት !!!


እንደውም ሳስበው ሴት ልጅ የምትወደውን ብቻ ሳይሆን የሚወዳትን ማግባት በጣም የተሻለ አማራጭ ይመስለኛልም !!!
ቢያንሱ እሱ እንዳየሁት ከሆነ ያከብራታል ያስብላታል ይንከባከባታል በሰው ፊት አያዋርዳትም በዛ ላይ በገንዘብም ቢሆን ሀብታም የሀብታም ልጅ ነው እኔ በስም ብቻ ከተሸከምኩት ይልቅ የተሻለ ነው !!!
ስለዚህ እንኳንም ከሱ ጋር ሆነች እንኳንም አልተሳሳትኩ እንኳንም ስሜት አልኖረኝ ብዬ ፈጣሪዬን አመሰገንኩ ደ
በዛ ሁላ ሀሳብ መሀል ግን ለማያ ብዬ ጥያት ልሄድ የቃጣኝና ማያ ስትሄድ ወደሷ ልመለስ ያሰብኩት ልዕልና ትዝ አለችኝና ወይኔ ጉዴ ብዬ ስዞር በሆነ አይነት አስተያየት እያየችኝ ነበር ።
ይቅርታ ልዕልና ብዬ ወደሷ ስዞር  .......



.......

.
.

ይቀጥላል


ክፍል 3⃣1⃣
❤8🙏4
September 3, 2026 161