ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣7⃣ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ ብላ በራሷ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣7⃣


አልጋው ጫፍ  ላይ ቁጭ ብላ በራሷ እየተናደደች ነበር ። የኔ ምላሽ አለመስጠት አናዷታል !!እንደዛ ሳያት የምር ከፍቷትና ተደብራ ስላየዋት እግሯ ስር በርከክ ብዬ እኔን ቀደንብ ታውቂኛለሽ ብዬ አስባለሁኝ ለማንም ሴት ተሰምቶኝ የማያቀው ስሜት እየተሰማኝ ነው ያለው !!!ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ ሳለቅስ ነው ያደርኩት !?! ግን አሁን ከእጄ አምልጠሻል ምን አልባት በራሴ ጥፋት ቢሆንም አጣሁሽ !!!በቃ አሁን የሰው  ነሽ አለቀ !!!አልኳት ። በርግጥ ከልቤ አይደለም !!! እዚሁ አጠገቤ እንድትሆን ብፈልግም ግን እንድትሄድ እየነገርኳት ነበር ። አሁንም እኮ አንተ ጋ ነኝ እየለመንኩህ ነው እኮ አንዴ አጠፋህ እሺ አትድገመው " አለችኝ እያለቀሰች ።
በቃ አይሆንም አልችልም ስላት ተነስታ አቀፈችኝ ። ሁለታችንም ከልብ ተቃቅፈን የራሳችን አለም ውስጥ እያለን በሩ ክፍት አለ ። ጥፋት እየሰራሁ እንደነበር ስለማውቅ መሠለኝ ክው ነው ያልኩት !!!
እኔ ድርቅ ብዬ መዞርም ሲከብደኝ ማያ ዞር ብላ አየቻት ። ሰላም ዋልሽ ልጄ ምነው ችግር አለ እንዴ ?  " አለች ። ድምጿን ስሰማ ኡፍፍፍፍፍፍ ነው ያልኩት ምክንያቱም  የእናቴን ድምፅ በደንብ ነው የማቀው።እሷ ማየቷም ችግር ቢኖረውም ግን የተሻለ ነው ።

እናቴ ወደ ውስጥ ገብታ በሩን ዘግታው በተደናገጠ ፊት ሁለታችንንም በየተራ ማየት ጀመረች ።ከድንጋጤያችን ብዛት ሁለታችንም ቃላት አጥሮን አፈጠጥንባት ።የበለጠ ግራ የተጋባችው የኔ የዋህ እናት
" ልጆች ምን ሆናችዋል ማያ ስርካለም ምን ሆነች ባለቤትሽ ሊጎዳሽ ሞከረ እንዴ ...??" ብዙ ነገር እያለች ጭንቅላቷ ላይ የመጡትን ጥያቄዎች አወረደችብን ።

ለትንሽ ደቂቃዎች ዝም ብለን የቆየን ቢሆንም ከደቂቃዎች ቡሀላ ግን  ማያ ራሷን ሰብስባም ቢሆን ተረጋጊ አረ ምንም አልተፈጠረም አለቻት ። እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ታዲያ ልጄ አስደነገጥሽኝ እኮ በዛ ላይ ሁለታችሁ ምን እያወራችሁ ነበር ?" ብላ ተመለከተችን ።

ማውራታችንን ብቻ ከተመለከተችም ተመስገን ነው !!!!ምንም አረ  ሀብትሽን ፈልጌው ነው " ብላ ነገሩን አቡካካችው ።
ደግሞ አመት ኮ ከላይ መለጣጥ ቡሀላ ቀና ብላ አይታኝ ማለቴ........" ብላ ታየኛለች ። ሁኔታዋ ትንሽ ፈገግ አስባለኝ ።
" ለምን ልጄ በሰላም ነው ወይስ ?" አለቻት አይ አክስቴ በቃ ችግር የለውም በቃ አውርተናል ልሂድ " ብላ ተሸፍናበት የመጣችውን ሻርፕ አነሳች ።

የኔ ልብ አሁንም ግራ እንደተጋባ ነው ! የሆነ ልቤ ቶሎ ከዚህ ቤት ወታ እንድትርቀኝ ይፈልጋል የሆነ ልቤ ደግሞ አጠገቤ ቁጭ እንድትል ይፈልጋል !!!! እዚህ ድረስ መተሽማ ዝም ብለሽ አቴጂም ተቀመጪ ልጄንን አሞብኝ እኮ መድሀኒት ላመጣለት ሄጄ መቶ ይመርመር አሉኝ እሱ ደግሞ ደረቀ ቡና ጠጥተሽ ትሄጃለሽ ቁጭ በይ "  ብላ ጎትታ ጠርዙ ላይ አስቀመጠቻትና
" ለምን  ተነሳህ ልጄ " ብላ አጠገቧ አስተኛችኝና አልብሳኝ ከሰል ለማያያዝ ወደ ውጪ ወጣች ። ገና እሷ ከመውጣቷ ፀጉሬን እየደባበሰች እኔን እሺ አይዞክ አሁን ይሻልሀል " ብላ አይኔን ሳመችኝ ።

ልቤ ደስ ሳይለው አይቀርም !!! ደስታውን በመውጋት እያሳየኝ ይመስላል የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው !!!
እናቴ አስር ጊዜ ወጣ ገባ ተፍ ተፍ እያለች ነው ። ማያ ጭራሽ የማላቃት ሰው ሆናለች
ያቺ ባየችኝ ቁጥር አንገቷን የምትደፋው ቀና  ብላ ለማየት የምትፈራው ማያ አሁን ላይ ጭራሽ የለችም ።ሳስበው ፍቅር ይቀይራል ሁሉንም ያስረሳል መሠለኝ ሴት እንድትነካኝ የማልፈልግ ልጅ ስትነካካኝ ፊቴን በየተራ ስትስመኝ ደስታ እንጂ ንዴት አልተፈጠረብኝም !!!


ሳትናገር ይሄን ሁላ አመት ስሜቷን ይዛ መኖሯ ገራሚ ሆኖ ሳለ ያልተነገረ ፍቅሯን ምን አልባትም ቀደም ብላ ነግራኝ ቢሆን ነገሮች ይቀያየሩ ነበር !!!!!
ለነገሩ ምንድነው የማወራው አንድም ቀን ቼክ አርጊያት የማላቃት ልጅ በምን ድፍረት መታ ትንገረኝ !!!ያልተነገረው ፍቅር ያመጣው ጣጣና ችግር ሁሉ በእኔ ጥፋት ነው !እናቴ..... ወጣገባ ማለቷን እንደቀጠለች ነው !!
ቡና አቀራርባ ለእኔ ሰርታ አልበላም ያልኳትን በሌላት ብር የገዛቻትን አይነት ምግብ አሟሙቃ ስታቀራርብ ማያ ቶሎ ተነስታ የእጅ ውሀ ይዛ መጣች ።
ምንም የመብላት ፍላጎት የሚባል የለኝም አልኳት ። ተው ልጄ እባክህ መብላት አለብህ " አለችኝ እማዬ ። ማያ ደግሞ በተቃራኒው በፊቷ እየተቆጣች ታጠብ ቶሎ በል እኔ እርቦኛል ብላ አስታጠበችኝ በግድ ። ከዛ እናቴ ምግቡን ስታቀርብ አንድ ላይ ሆነን እኔ መብላት ከብዶኝ ሳላውስ ማያ ቶሎ ቶሎ እያለች እያጎረሰችኝ እንድበላ አደረገችኝ !!!


ዘለአለም እሷ እያጎረሰችኝ ብኖር ብዬ ተመኘው ። የምር የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው !! እናቴ ጉዷን አላወቀች እንዴት እንዲ ተቀራረቡ በሚል አስተያየት እያየችን ነበር ።
እናቴ ስትለምነኝ ያልበላውትን በማያ ጉርሻ ጥንቅቅ አርጌ በላሁኝ ።
እናቴ ማያ እንደወጣች የምታወርድብኝን የጥያቄ ናዳ ለመቀበል ራሴን በደንብ ማዘጋጀት ጀመርኩኝ !!!
ቡና ጠጣን እማዬና ማያ ብዙ ነገር አወሩ
በመሀል በመሀል ፈልጋ እንዳላገባችና ህይወቷን የምትሰጠው የምትወደው ሰው እንያለ ለእኔም ለእናቴም እያሳወቀችን ነበር ከልጅነቴ የምመኘውን ሰው ማግባት እፈልጋለሁ !!!ምናምን ብቻ በጣም ብዙ ነገር ነገረችን


የዛኔ የምር ፀፀተኝ !!!! ምን አለ ቀድሜ ባወኩ ብዬ ቸመኘሁኝ !!እሷን የኔ ለማረግ መሞከርም ፈለኩኝ ። ግን ብዙ አልቆየችም ሰአቱ ፈጠነብኝ ጨርሳ ወደቤቷ ሄደች ማለቴ ወደዛ ሰውዬ!!!እና ተመልሳ ከሄደች ደግሜ

እንደማላገኛት እያወኩ በአይኔ ሸኘዋት ።
እናቴም እሷን ለመሸኘት ወታ ምን እያወሩ እንደሆነ አላውቅም ቆዩልኝ እኔም እድሌን ለመጠቀም ስለፈለኩኝ እንቅልፍ የወሰደኝ ለማስመሰል ሞከርኩኝ እናቴም እየሮጠየች እየመጣች ልጄ ልጅ " እያለች ነበር ። አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም " ነውና ነገሩ የምር እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው ዝም አልኩኝ !የኔ የዋህ አምናኛለች !!! የኔ አባት አትላንት ጀምሮ ሳተኛ " እያለች ግንባሬን ስማ ብርድ ልብሱን አስተካክላ አልብሳኝ ወጣች ።
.......

.
.

ይቀጥላል


ክፍል 2⃣8⃣
❤3🥰2
September 1, 2026 229