ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣8⃣ እኔ ግን እንቅልፍ ሊወስደኝ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣8⃣



እኔ ግን እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም !!!
ይልቁንም መድሀኒት ያጣ እብድ መሠልኩ
እሷ ገና ከኔ ከመራቋ መታመም ጀመርኩኝ ። ቀኑም እየመሸ ነበር !!
አልዋሻችሁም ከየት እንደሚመጣ እንኳን ሳላውቀው እንባዬ ዝም ብሎ መፍሰስ ጀምሯል ለሊቱን ሙሉ ሳለቅስ አደርኩ እናቴም ከእኔ እኩል ስታለቅስና ስትጨነቅ አደረች ሰካራሙ አባቴ ብሩ አላለቀችበትም መሠለኝ ቤት መቶም አያቅ የፈረደባት እናቴ ብቻዋን ስታስታምመኝ አደረች ።
እናቴ ተስላልኝ ነው መሠለኝ ሲነጋጋ እንቅልፍ ወሰደኝ ።የነቃሁት ቀን ላይ ቢሆንም ስነቃ ተሽሎኝ ነበር !!!

ማያ ሳትመጣ ሶስት ቀናት ያህል ቆየች ። ማትሪክ ፈተና አራት ቀን ቀርቶታል ።

የተለያየ  ትምህርት ቤት ተልከን  ነው የምንፈተነው እና እኔና እሷ አንድ ላይ ቢደርሰን ደስ ይለኝ ነበር !!! ደግሞ ሶስቱንም ቀን ሳስበው የነበረው ከዛ ሰውዬ ጋር ተኝታ የሚለውን ሀሳብ እያሰብኩ መቀበል እስኪከብደኝ ድረስ ሳስበው ነበር !!ግን ሁለቴ አሳልፌ ሰጥቻታለሁ የሷ ጥፋት አይደለም !!ቀኑ ቀጥሎ ቅዳሜ ቀን ትምህርት ቤት እንድንመጣ አርብ ጠዋት ተነግሮ በወሬ በወሬ እኔም ሰማሁኝ ። ቁጭ ብዬ ስለዛ እያሰብኩኝ እናቴ መጣራች ጀመረች አቤት እማ ስላት

" ሰው ይፈልግሀል " አለችኝ ። ማያ መጣች ብዬ ባንዴ ፊቴ በርቶ ነበር !!
ለማየት የናቴን ጀሳሳ ጎጆ አጎንብሼ ስወጣ ግን ከተበኩት በተቃራኒ ያልተጠበቀ እንግዳ ነበር ያየሁት !!ለምን እና እንዴት እንደሆነ ባላቅም ቀበጧ ሞልቃቃዋ የልጥጥ ልጅ ሰላምና አባቷ ሳሚ በር ላይ ቆመዋል !!!ልዕልና በሆነ አይነት አስተያየት ስታየኝ ነበረ ።
እኔም ደንግጫለሁ !! በሆነ መንገድ ግን ትኩረቴ ማያ ጋር ስለሆነ ምን አገባኝ አይነት ስሜት አበረታኝና ጠጋ ብዬ
ሰላም ሳሚ እንዴት ነህ ሰላም ደህና ናት ? አልኩት ።
ከእሱ መልስ በፊት ግን ልዕልና  ቀደም ብላ ሚኪ እዚህ ምን ታደርጋለህ  ?? " ብላ አየችኝ ። ማለት ? አልኳት እንዳልገባሁ ሆኜ እዚህ ቦታ ላይ ምን ትሰራለህ በዛ ላይ አንተን ለማግኘት ስንት እንደለፋን ታውቃለህ ?? " አለችኝ ። በሰአቱ ለመመለስ ፍቃደኛ ባለመሆኔ በዝምታዬ ፀናሁ ሳሚም ጣልቃ ገባና ልጄ በሰላም ነው አይደል ሳትናገር የጠፋከው በዛ ላይ ፊትህ ልክ አይደለም አሞካል እንዴ ችግር አለ ? " አለኝ ።

ልዕልና ከምጠይቃቸው ጥያቄዎች በተቃራኒው ነው የሱ ሀሳብ ለዛም ነው ምርጥ ሰው ነው የምለው !!!!
እኔም እዛ ቤት መቆየታችንን ስላልወደድኩት በሰላም ነው ሳሚ እየሄድን እናውራ አልኳቸው ።

ሰው ግቡና እናውራ ይላል እኔ......
ግን ውጪውን  አይታ እንደዛ ካለች መቼም ውስጥ ስትገባ ራሷን እንዳትስት ፈርቼ ነው !!!! ሳሚ ስለኔ በትንሹም ቢሆን ስለነገርኩት ቶሎ የተረዳኝ ይመስላል
" አዎ ደስ ይለኛል እናወራለን በሉ ኑ " ብሎ ቀድሞን ወጣ ። ልዕልና ግን ጉዳዩን ለመረዳት የከበዳት ትመስላለች !!
የኔ ቤት መሆኑን ለመቀበል የከበዳት ይመስል ሚኪ  ምን  ሆነህ ነው እ እዚህ ጊቢ ምን ታደርጋለህ ከቤተሰብ ተጣላህ እንዴ ደግሞ ለምንድነው እየራከኝ ያለከው ??
ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ ።

እንደሁሌው መመለስ የማልፈልገው ጥያቄ ነውና በዝምታ አቀረቀርኩ ።
" እኔና ሚኪ የምንወዳት ቤት አለች እዛ እንሂድና ቁጭ ብለን እናወራበታለን " አለ ሳሚ አይ እኔ ይቅርብኝ ወደቤት ልመለስ ትንሽ አሞኛል አልኩት ! ወደ ቤት ?" አለች ልዕልና ነገሩን ለመረዳት እየሞከረች ያለች ትመስላለች ።
" ቆይ ቆይ ከእኛማ እንዲህ በአንዴ መራቅ አትችልም ሁሉ ንም ነገር እናውራው ይቀልሀል ካስፈለገም ሆስፒታል ደርሰን እንመጣለን በሉ ግቡ " ብሎ መኪናው ውስጥ ገባ ። እኔም ጋቢናውን ከፍቼ እስክትገባ ቆሜ ጠበኳትና ከዃላ ገብቼ ቁጭ አልኩኝ ።
እንደነ ሳሚ አይነት የለጠጡ ሰዎች የኛ መንደር ብዙም ስላልተለመደ መንደርተኛው ብቅ ብቅ እያለ እያዩኝ ነበረ

እንዲሁም ከኔ ችግር አለባቸው አሁንማ ስርቆት ጀመረ እንዳይሉ ፈራሁ ።
በዝምታና በጨዋነት  ቢያምኑብኝም  ስኮሳተርና ስለምደባደብ እንደዛ እንዳያስቡ ፈራለሁ !! ብቻ ግን ከዚ በፊት ወደወሰደኝ ቦታ ይዞን  ሄደና መጀመሪያ ምግብ ጋበዘን ! ከዛም ለእኔና ለሷ ፋንታ አናናስ አዘዘና ማውራት ጀመርን ።

ልዕልና ለመስማት ቸኩላለች ።
" ድንገት ስጠፋ እኮ ተጨንቀን ነው በስንት ፍለጋ ነው ያገኘንክ ተጨንቀን አለኝ " ይቅራ አርጉልኝ ሰሞኑን ትንሽ ችግሮች ተደራርበውብኝ ነው አልኳቸው ።
" እሺ እዛ ቦታ ምን ታረጋለህ ሚኪ " አለችኝ ልዕልና ፊቷን አጨማዳ ።
ከዛ በላይ መታገስም መደበቅም ዝም ማለትም አልቻልኩኝም አየር በደንብ ሳብኩና ያ ቦታ የምትይውና የተፀየፍሽው ቦታ የእናቴ ቤት ነው የእኔም ቤት ማለት ነው !!
እኔን እንድጠራልኝ የጠየቅሻት ሴት እናቴ ናት !! እኔ ማለት የአንዲት ምስኪን የደሀ ልጅ ነኝ እኔ ስለኔ ምንም ሳልላችሁ ራሳችሁ ናችሁ የካባችሁኝ !!!
ሰውን በአለባበሱ ስለምትፈርጁ አይደለ !??? ብዬ ግንባሬን ቋጥሬ እንባ እየተናነቀኝ ተመለከትኳት ።
ምክንያቱም ፊቷ በጣም ያስጠላ ነበር ስለዛ ቤት ስታወራ ያሳየችው ፊት ልክ አልነበረም !!!........


.......

.
.

ይቀጥላል


ክፍል 2⃣9⃣


@share @share
❤14👏2🤔1🙏1
September 1, 2026 244 3