❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣6⃣ ..........ፊት ለፊቴ ቆማለች ። ሳያት ደነገጥኩ ። በሰአቱ እሷ ልትመጣ ትችላለች የሚል ሀሳብ ቀርቶ እሷንም ላለማሰብ እየታገልኩ ነበር ። በመምጣቷ ከመደሰት ይልቅ ምክንያቱን ባላቅም ፊቴን ነው ያዞርኩባት ። ከእጄ የወጣ ነገር ስለሆነ ለራሴ ድጋሜ ተስፋ መስጠት አልፈለኩኝም በዛ ላይ ጭንቅላቴ ውስጥ የሰርጓን ምሽት ከዛ ሀብት ጭንቅላቱን ከደፈነው ሰውዬ ጋ አሳልፋለች የሚለው ሀሳብ ጭንቅላቴን ሞልቶታል ። ከእኔ ነው የምትሸሸው ?? " አለችኝ ። በንዴት ነው እያወራች የነበረው ። በርግጥ እውነቷን ነው ። እኔ ነኝ ተስፋ ሰጥቼ መልሼ የነጠቋት !! ሙሉ በሙሉ የኔ ጥፋት ነው ግን የሰው ባህሪ ነውና ጥፋቴን እሷ ላይ ለማላከክ ስለፈለኩ ብቻ በሰአቱ እኔ ባልኖርም እንቢ ማለት ትችይ ነበር አልኳት ። ንግግሬ የበለጠ አናደዳት መሠለኝበአንዴ ፊቷ ተቀየረ እና " ከዛስ አንተ ስለኔ ምን እንደምታስብም ሳላቅ ምን ልሆን ?? ሰርጉን እንቢ አልኩ ከእናቴ ጋ እንጣላለን አንተ ጭራሽ አፈልገኝም ከዛ እኔ ሜዳ ላይ ቀረሁ !!......" ብላ በንዴት ብዙ ነገር አወራችኝ ። እኔም የሷን ንግግር ተንተርሼ ራሴን ነፃ ለማረግ ብዬ ብቻ እኔስ ያንቺን ስሜት በምን ላውቅ እችላለሁ እኔስ ሰውዬውን ወደሽው ቢሆነስ በምን አውቃለሁኝ ? ብዬ ራሴን ነፃ ለማረግ ሞከርኩ ። ስህተቴን ለመሸፋፈን በሞከርኩ ቁጥር በጣም እያናደድኳት ነው ያለሁት ግን በራሴ እጅ እንዳጣዋት ስለተሰማኝ ላለመቀበል እየሞከርኩ ይመስለኛል !! ከእራሴ ጋር ከበድ ያለ ትግል ላይ ነኝ !!! እንዳሰብኩትም በጣም ተናዳ ወደዃላ እየሸሸች " አንተ እውር ስለሆንክ ነዋ እኔ ምን ላርግ " አለችኝ ። ምን ማለት ነው አልኳት ከተኛውበት ቀና እያልኩ በጣም በብዙ መንገድ ማወቅ ትችል ነበር በብዙ መንገድ ላሳይክ ሞክሪያለሁ ክፍል ውስጥ ሳላይክ ውዬ አላቅም አንተ ግን ቀና ብለህ አይተከኝም አታቅም ከልጅነታችን ጀምሮ እመኝክ ነበር አዎ አልዋሽም ግን አንተ ማየት አትችልም ። ከሴክሽን አንደኛ ወጥቼ ሲጨበጨብለኝ ትኩረት ክጠከኝ ብዬ ስንቴ ተመኝቻለሁ ...." እያለች ብዙ ያላስቸዋልኳቸውን ነገሮች ነገረችኝ ። በዝምታ ሳዳምጣጥ ከቆየሁ ቡሀላ ለምንድነዉ አሁን የምትነግሪኝ ታዲያ ካለፈ ቡሀላ ምን ለመሆን ነው የምትነግሪኝ ቆይ እ እንዲቆጨኝ ከሆነ ተሳክቶልሻል በቃ ተይኝ አልኳት ። ከልቤ እንድትተወኝ ፈልጌ ባይሆንም ራሴን ለመሸወድ እየሞከርኩ ነበር ። !! " አንተ ምልክት እንኳን መች አሳየከኝ እና ነው ቆይ እ የሆነ ሳምንት ልታስቆመኝ ልትቀርበኝ ሞከርክ ከዛ መልሼ ልቀርብ ስሞክር ባላየ ማለፍ ጀመርክ ምንድነው የኔ ጥፋት " አለችኝ ። ቀና ስል ከየት እንደመጣ አላውቅም እንባዋ እንደ ጉድ እየወረደ ነበር ። ደንግጬ እያመመኝም ቢሆን ከተኛውበት ተነስቼ እንባዋን እየጠራረኩ አቀፍኳት ። ምን ያህል እንደተናደደችብኝ የሚያስታውቀው በዛ ልክ መናገሯ ነበር ። ሰው ቀና ብላ አታይም የምላት ልጅ በጣም ነበር የተናገረችኝ ። ለትንሽ ደቂቃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተነካክተን ተቃቀፍን ። ልክ እቅፏ ውስጥ ስገባ ከላይ ላይ የተጫነ ድንጋይ ቀስ በቀስ የተነሳልኝ እስኪመስለኝ ድረስ እየቀለለኝ ነበር ። እቅፏ የሆነ ሰላም አለው !!! የሆነ ፀጥ ያለ ነፋሻማ ቦታ የገባሁ ይምስል ራሴ ሰላም እየተሰማው ቀስ ያለ ንፋስ እየፈሰብኝ መስሎ ተሰማኝ ። ከሷ እቅፍ ላለመውጣት ምንም ላደርግ እንደምችል ይሰማኛል !!!እሷም ከየት እንደለመደች ባላውቅም ፍቅር መስጠት ችላበታለች ቀስ እያለች ለስላሳ ፀጉሬ ውስጥ እጇቿን እያርመሰመሰች እቅፏን እንደወደው አደረገችኝ ። ከረጅም ደቂቃ ዝምታ ከሰፈነበት ሰላምታ ቡሀላ ሀብትሽ ? " አለችኝ ። በቃ ተነስ ልትለኝ ስለመሰለኝ በእናትሽ ትንሽ እንቆይ አልኳት ። " ለምን ትንሽ እ እድሜዬን ሙሉ እንዲህ ብናሳልፍም አይከፋኝም " አለችኝ ። በንግግሯ የተደሰትኩት እኔ ሳላስበው አንገቷ ስር እንደተወሸኩ ሳምኳት ። የሚገርመው ምንም አላለችኝ በአፀፋው መልሳ ሀብትሽ "" አለችኝ ። ወዬ አልኳት እኔም ደግሜ " አንድ ነገር ልንገርህ አትናደድም " አለችኝ ። አትናደድም ተብለው የሚነገሩ ነገሮች እንደሚያናድዱ ግልፅ ነው ግን እሷ ሆናብኝ አልናደድም ኝገሪኝ አልኳት ። " እንዴት እንደምነግርህ አላቅም ቀሌላ አትረዳኝ ላንተ ካለኝ ፍቅር ነው ግን........ " ብላ ዝም አለች ። ግን ምን ንገሪኝ አልናደድብሽም አልኳት ። በቃ አልችልም !!" አለችኝ ። ምንድነው የማትችይው አልኳት ግራ ገብቶኝ በቃ ለሱ ክብሬን መስጠት አልችም !!!! " አለችኝ በሀፍረት ፊቷን ደረቴ ላይ ለጥፋ ። እኔ ግን ደንግጬ አሁንም ወደ ዃላ ገፍትሪያት ከእቅፏ ወጣሁ .......ደንግጣለች !!! ሴት የሚለውን ክብሯን ትታ ሴትነቷን ለመስጠት ጠየቀችኝ ለሷ ምን ያህል ከባድ አመት ንደሆነ ግልፅ ነው !!! እኔ ግን ጭራሽ አስቤውም የማላቀው በጣም የምፈራው ነገር ነው ። በጭራሽ ደግሞ እንደዛ ትላለች ብዬ አስቤውም አላውቅም !!! ከሷ በላይ እኔ ደንግጫለሁኝ !! አፌን እንደከፈትኩ ዝም ብዬ ስመለከታት " አትየኝ እኔ ባለጌ ሆኜ አይደለም ወይም ክብር ሳይኖረኝ ቀርቶ አይደለም በደንብ ታቀኛለህ ሰው ቀና ብዬ ሳላይ ነው ያደኩት !!ግን አንተን ከቁጥጥሬ በላይ እወድሀለሁ ለፍታ ካሳደገችኝ እናቴ እኩል ወይም በላይ ኡፍፍፍ በቃ አላቅም ብቻ አልችልም !!የሆነ ቀን አይተከኝ ወይ በሆነ ተአምር ወደከኝ ተጋብተን ካንተ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደምወልድ እያለምኩ ነው ያደኩት !!!ያኔ እኛ ቤት በከመጣህበት ከአስር አመቴ ጀምሮ ምኞቴ ነበርክ !!እድሉን ባታበላሽ እኮ እናቴ እንደምታዝን እያወኩም ሰርጉን ልተወው ነበር ????..... ለምን ግራ ታጋባኛለህ ቆይ የማትወደኝ ከሆነ ለምን አትነግረኝም ??" ብላ ተመለከተችኝ ። ስሜቱን ከዚህ በፊት ስለማላቀው ለመረዳት ቢከብደኝም ግን ደግሞ ሁኔታዎች ለሷ ያለኝን ፍቅር ግልፅ ያደርጉታል !!!ለሴት ትኩረት የሚባል የማልሰጥ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው ጋ ሳያት ልቤ እንደተሰበረ የተሰማኝ በሷ ነው !! ስትረቀኝ የተከፋሁት የታመምኩትም በሷ ነው !!.ከእናቴ ቀጥሎ እቅፏን የወደድኩት ዪጀመሪያ ሴት ናት ። ልዕልና ስታቅፈኝ የሚሰማኝ ድንጋጤ ለካስ የፍቅር አልነበረም ከሴት ጋር ያለኝ ርቀት እንጂ ....ከህመሜ በእቅፏ የፈወሰችኝ ሴት እሷ ናት !!!ለሊቱን ሙሉ ሳስባት ስጨነቅ ነው ያደርኩት !!ስለዚህ አልወድሽም ብል ውሸት ነው የሚሆንብኝ !!!አቅፊያት ለሊቱ እንዲነጋ አብራኝ እንድትሆን ብፈልግም ግን አስተዳደጌና ራሴን ያሳመንኩበት ማንነት ከለከለኝ !!!.ፍላጎቴን እንድደብቅ አስገደደኝ !!! ....... . . ይቀጥላል ክፍል 2⃣7⃣
ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣6⃣ ..........ፊት ለፊቴ ቆማለች… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME
August 31, 2026 250