ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣9⃣ ..........ያሳየችው ፊት ደስ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣9⃣

..........ያሳየችው ፊት ደስ አይልም ነበር!!!
ደስ የሚለው እኔም አፀፋውን እየመለስኩ ፊቴን ከሷ በላይ ከስክሼ
ምነው ልዕልና ? አልኳት ።
ዞር ብላ አባቷን ተመለከተችና
" አይ ገርሞኝ ነው " ብላ በቅጡም ሳትጨርስ ለምን ? ብዬ ቆሌዋን ገፍፈኳት !!!አይይይይ....." ብላ ነገሩን አረዘመችው ።

በጣም ንዴት  ላይ መሆኔን የተመለከተው ሳሚ ልዕልናን በአይኑ ዝም እንድትል እየነገራት ነበር ። እኔ ትክክል መሆኔን ስለሚያውቅ ምንም ለማለት አልደፈረም ነበር !!


ለደቂቃዎች ያህል በመሀላችን ዝምታ ከሰፈነ ቡሀላ ልዕልና ቀልጠፍ ብላ እየተቁለጨለጨች ይቅርታ አንዴ ላውራ ?" ብላ ሁለታችንንም ተመለከተችን
በሰአቱ ሳሚ ምንም እንድታወራ የሚፈልግ አይመስልም !! ሳስበዎ ነገሮችን እንዳታበላሽ  ፈርቶ ይመስለኛል !!!
እኔ ደግሞ በተቃራኒው መጥፎ ንግግር ተናግራኝ እሷን መጥላት እፈልጋለው !!!
ምክንያቱም ልጅቷ በጣም ቆንጅዬና የምታሳሳ ናት !!!የምጎዳው የምታመመው ለማያ ቢሆንም ሳስበው ግን ልዕልና ለእኔ የማትገባ አይነት የሆነች ልዕልት ትመስለኛለች !!!!

ራሴን በደንብ አረጋግቼ አውሪ ምንም ችግር የለውም አልኳት ቀለል ካላት ብዬ ፊቴን ፈታ እያረኩኝ ።
" ይቅርታ ሚኪ ..."ብላ ወሬዋን ስጀምር ቶሎ ጣልቃ ገብቼ ሀብተትሽ በይኝ ሀብታሙ ነው ስሜ አልኳት ቶሎ ጣልቃ ገብቼ ።በስሜ እንደማንኛውም ሰው ፈገግ ብላለች !!!ደስ የሚለው ቅልል ያለች ልጅ ስለሆነች አይ እኔ ሚኪ ብልክ ይሻለኛል " አለችኝ ! ሳልፈልግና ሳላስበው ፈገግታዬ አመለጠኝ ። ስኮሳተር ተጨንቆ የነበረው ሳሚም አብሮኝ ፈገግ እያለ ነበር !!!
" ደሞ አንተን የመሰለ ውብ ልጅ ሀብታሙ የሚል ስም አብሮ አይሄድም እሺ በስመአብ " አለች ቀልድ መሆኑን ለማሳወቅ እየሳቀች !!!
እኔም እኮ እሱን አስቤ ነው የቀየርኩት አልኳት ፈገግ ብዬ ። እሺ ወደ ሀሳቤ ልመለስና እኔ አንተ ምንም ብትሆን አይጨንቀኝም !! ካስቀየምኩህ ይቅርታ ግን እኔ አንተን የሳልኩበትና ያገኘውክ ቦታ ስላልተገጣጠመልኝ ብቻ ነው !!!
እንጂ አንተን የወደድኩህ ማለቴ ( ክው ብላ እጆቿን እያወራጨች )የወደድንህ  አንተነትህን ነው !! እኔ አንተ ስለምትኖርበት ቤት ሰፈር መንደር ምንም አይጨንቀኝም !!!
ሲጀመር ማንም ተንደላቆ የኖረ የለም አባዬ አንተ ካለህበት ሁኔታ የከፋ ቦታ ላይ አድጎ አሁን ላይ ....አንተ ደግሞ ፈጣሪ ሁሉን አሟልቶ ነው የሰጠቅ እኮ በጣም ውብ ነህ ፀባይክ ለመስራት ፍላጎት አለህ ቋንቋ ትችላለህ ቁመትና አለባበስህ ......." ብላ ዝም አለች
ቋንቋ ያለችው እንግሊዝኛ ቋንቋን ቀለል አድርጌ መጠቀም እንደምችል አስታውላ ይመስልኛል !አለባበስ ቁመት ስትል ሞዴሊንግ እንድማር እየነገረችኝ ይመስለኛል !!!
ግን በጣም ውብ ነህ ሁሉን አሟልቶ የሰጠህ እንዲሁም የወደድኩህ የሚሉት ቃላቶች እኔና ሳሚ ፈገግ ብለን እንድናያት ያደረገው ንግግር ይመስለኛል!!!!

ሳላስበው በንግግሯ ተስቤ ነበር !!!
ህመሜን የምርም ሙሉ በሙሉ የለቀቀኝ ይመስለኛል!!!!! ደስ እያለኝ ነበር !!!በተለይ ደግሞ እኔ ትለኛለች ብዬ የጠበኩት ነገር እና እሷ ላይ ያየሁት ነገር ምንም ስላልተገጣጠመ ደስ ብሎኛል !!!
ሀብታሞች እንደዛ ያስባሉ ብዬ ስላላሰብኩኝ ተገርሜ ነበር ።
ሳናስበው ሶስታችንም በፈገግተታ ተሞልተን ሳለ የሳሚ ስልክ ጠራ ......ሳሚም ቶሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ለማውራት ሄደ ።
ንዴቴ በአንዴ ቀለል ብሎ በፈገግታ ስመለከታት አይኖተቿ እኔን ላለማየት ማማተር ጀመሩ !ለኔ ያለሽ ፍቅር አባትሽ ፊት እስከመናዘዝ ነው ማለት ነው ? አልኳት በፈገግታ ተሞልቼ  !! እ አረ እንደዛ  አይደለም " እያለች እያለ ሳሚ ወደኛ መጣ ።

" ልጆች እንግዲህ ይቅርታ በጣም አስፈላጊ ስብስባ ረስቼ ነው መሄድ አለብኝ
ስጨርሱ ደውሉልኝና መኪና እልክላይዋለሁ ወደቤት ሂዱ " ብሎን እየተቻኮለ ከኪሱ የሆነ ያህል ብር አውጥቶ ለእኔ ሰጠኝና የተጠቀምነውን ክፈሉ ካነሰ ደግሞ ደውሉ " ብሎን እየፈጠነ ሄደ ።

ይሄ ማለት ደግሞ እኔና ልዕልና ብቻችንን አንድ ደስ የሚል አየር ያለው ካፌ ነግር ውስጥ ተቀምጠን እየተፋጠጥን ነው ።
ታውቃላችሁ አንዳንዴ በጣም ራሴን እስከመጥላት የሚያደርስ በራስ አለመተማመን ውስጥ ከቶኛል !!!
ልክ ከማያ ጋር ስሆን ሙሉ በሙሉ ማያን እንደምወዳት ይሰማኛል በማግባቷም ተከፍቻለሁ ግን ልክ ልዕልናን ሳገኛት ሁሉንም ነገር ጥርጣሬ ውስጥ ትከተዋለች !!!!

ሁለታችንም ፋንታችንንም ጨርሰን ቁጭ ብለን ስንፋጠጥ የተመለከተን አስተናጋጅ ወደኛ መቶ የሚጨመር ነገር አለ ? " አለን ። ምንም አያስፈልግም ለማለት ገና ላወራ ስል ቀድም ብላ ለእኔ ማኪያቶ አምጣልኝ " አለችው ።
በነገራችን ላይ ያን ያህል ውድ እንዳልሆነ ባውቅም ግን ቀምሼ የማላቀው እኔ እድሌን ለመጠቀም ያህል ለእኔም አልኩት ። ከትኝሽ ቆይታዎች ቡሀላ ይዞልን መጣና መልካም ጊዜ ብሎን ሄደ ።

ሙሉ ሰአቱን ልዕልና አይኖቿን ከእኔ ለማራቅ  የምታረገውን ትግል እየተመለከትኩ ምስጥ ብያለሁ ።
ሴት  ልጅ  የወደደችውን ወንድ ልጅ አይን በጣም ትፈራለች !!
ሴት ልጅ ከወደደችክ ያንተን አይን ላለማየት አይኖቿን ገደልም ልትከት ትችላለለች !!!!
በመሀላችን ያለውን ዝምታ ቀልድ ለማረግ ያህል እና ስለ ባልሽ ትንሽ ንገሪኛ ? አልኳት ። እ የምን ባል ነው ሚኪ " አለችኝ አሁንም እጆቿን የማኪያቶ ሚንኪያ ላይ አድርጋ ።ባል አለኝ ብለሽኝ ነበር እኮ አልኳት እኔም ለማወጣጣት ስለፈለኩኝ
"አረ እኔ እየደዛ አይነት ነገሮች ላይ የለሁበትም እኮ " አለችኝ ።

የዛን ቀን ምን እይደነካኝም አላውቅም በጣም ቀልደኜ ሆኜ ነበር ከቤት ስወጣ የበረኩበት ሙዶ እና እዛ እያሳየሁት ያለሁት ሙድ አይገናኝም ሁላ !!!!
ጭራሽ ብሶብኝ እና እኔ የመጀመሪያሽ ነኛ እ !!! አልኳት እየሳኩኝ ።

ማኪያቶው ጠረንጴዛ ላይ እንደተቀመጠ በመሆኑ ምንም ባጠጣም ምራቋ ያነቃት ይመስል ትን ብሏት ውሀ ጠጥታ የው የለቀቃት ሁላ !!! እንዴ ምየው ችግር አለ ?  አልኳት እሷም ቶሎ ብላ አረ የምን ችግር ጠጣና ቶሎ እንውጣ በቃ አለችኝ ። እሷ እንዳደረገችው አማሰልኩና ቀመስኩት ። ሀለት የምወዳቸው ነገሮች ድብልቅ ነው በጣም ይጣፍጣል !!!!

ቶሎ መውጣት የፈለገች ትመስላለች ቶሎ  ቶሎ መጠጣት ጀመረች እኔም ቶሎ ጨርስኩና ሂሳብ መጣ ።
የመጣው ብር ሳሚ  ከሰጠኝ አንፃር ትንሽ ነበር !!! በእኔ በኩል እናቴ በቀን ለአንድ ጊዜ ምግብ የወር ወጪዋን እንዳወጣን ብሰማ እንደማታናግረኝም አቃለሉ ከሳሚ ብር ላይ ብዙ መትረፉ ግን ደስ አላለኝም ።


ከዛ ቲፕ ኘስቀምጠን ወጣንና በር ላይ እንኪ ለሳሚ ስጪው እሺ ብዬ ብሩን ስሰጣት ልትቀበለኝ ፍቃደኛ እየሆነች አልነበረም !!!!
" አያገባኝም ራስክ ስጥ ሲቀጥል ደግሞ ገና ግብዛው መች አለቀ ትጋብዘኛለህ " ብላኝ አረፈች ። አስቡት በአባቷ  ብር  እኔ ስጋብዝ !!!! መኪና ጥሩ ብሎን ቢሄድም እኔ በየቀኑ በእግሬ የምመላለስበት መንገድ ነውና ቅርብ ነው በዛውም እያወራን እንሄዳለን ብያት መንገድ ጀመርን ።
ልክ የሰፈራችን መተጣጠፊያ መንገድ ላይ ስንደርስ ከሷ ጋ እያወራን ከት ብዬ ስቄ ቀና ስል ማያን ከፊት ለፊቴ ወደኔ ስትመጣ አየዋት .........

.......

.
.

ይቀጥላል
❤2🥰1
September 3, 2026 144