ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል3⃣1⃣ ....... ወደሷ ስዞር በዝምታ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️ ✍ፊደል                         ክፍል3⃣1⃣ ....... ወደሷ ስዞር በዝምታ ተመለከተችኝ ይቅርታ እንደምታስቢው አይደለም አልኳት ወደሷ እየቀረብኩ ። ሂዳ ተከተላት " አለችኝ አንድ እርምጃ ወደዃላ እየሸሸች ። ይቅርታ የራሴ ጥፋት ነው እንድትጎዳ ስለማልፈልግ ብቻ ነው ብዬ ላስረዳት ሞከርኩ ። ለምን ትጎዳለች ራሱን የሚጠብቅ ኩል የሆነ ባል የሚያከብራት ሰው አላት ለምን ትጎዳለች ??" አለችኝ ። መጀመሪያ እንደዛ አልመሰለኝም ብዬ ላስረዳት እየሞከርኩኝ እያለ " ትወዳታለህ ?" የሚል ድርቅ ያለ ጥያቄ ጠየቀችኝ ።ማያ ማለት ከልጅነት የማቃት ግን የማላቃት ልጅ ናት ሽለሷ ሁሉንም ነግርሻለሁ ከፈለግሽ ግን እወዳታለሁ እንጂ በፍቅር አይደለም እምልልሻለሁ አስብላታለሁ ግን ላፈቅራት አልቻልኩኝም እሷ ጋር ያለው ስሜት ቀስ በቀስ እንደሚጠፋ እርግጠኛ ነኝ አልኳት ። ያን ያህል የተዋጠላት አትመስልም ። እውነት ለመናገር ከሆነ ከልቤ ነው ያወራሁት በዛ ላይ በራስ በመተማመን ስሜቴን መግለፄ የሆነ ደስ የሚል አይነት ስሜት አለው የሆነ ነገር ከላዬ ላይ እንደወረደ እየተሰማኝ ነው  !!! እዛ ጋር የነበረውን ድባብ መቀየር ፈልጊያለሁኝ ። ልዕልና ያን ያህል የምትጨክንብኝ አይመስለኝም ግን አላውቅም ። በሰአቱ ስሜቷን ለማስተካከል ስለፈለኩኝ ወደሷ ቀረብኩኝና አይን አይኗን መመልከት ጀመርኩኝ ።በሰአቱ  በጣም በራስ መተማመን ላይ ነበርኩኝ ። በልበ ሙሉንት አታምኚኝም እኔ ልሙት በፍቅር አላስባትም አልኳት። ከዛም ትንሽ የፍቅር ሰው ለመሆን ስለፈለኩኝ ግን አንቺስ ? አልኳት ፈገግ ብዬ በጣም እየቀረብኳት። እኔ ምን ? " አለችኝ ። ምንም ሳልናገር በሆነ መንገድ አየዋት ተግባብተናል ግን ላለማመን እየሞከረች ይመስለኛል ። ደግሞ ለምንድነው እንደሱ የምታየኝ " አለችኝ አይኖቿን ወደ መሬት እየተከለች ። ደስ የሚለው ቦታው ብዙም ሰው የማይተላለፍበት ስለነበረ እንጂ እንደዛ ከሴት ጋ ተቀራርቤ ሰው ቢያየኝ ኖሮ ......!!!ብቻ ግን ወደ ፍቅራችን ስመለስ  የሌለኝ ባህሪያትን እያወጣሁ ነው ። ከሷ ጋ ስሆን የሆኑ ስሜቶች አሉ ። ላቅፋት እንድታቅፈኝ እንድስማት እንድትስመኝ እጆቿን መያዝ ብቻ ብዙ ነገሮችን እመኛለሁ ። መቼም ሀብትሽ እንደዛ አያረግም ማያን የተዋወቃት ሚኪ የፍቅር ሰው መሆኑ ተዋቶለታል ። በእጆቼ አገጯ አካባቢ ይዤ ቀና እያደረኳት አይኔን እያየሽ ተመልከቺኝ እንጂ ምን ሆነሻል ? አልኳት ። አንተ እንደሱ አትመልከተኝ አትቀረበኝም " ብላ ድጋሜ አንድ እርምጃ ከኔ ራቀች ። ሚኪ ግን ከራሱ ጋ አልነበረም  የበለጠ  ወደሷ ቀረበና ለምን አላት ። ውስጤ ያለው ሌላኛው ማንነት ማለቴ ሚኪ በዛ ሰአት አልተቻለም እሷ ደግሞ ስቀርባት ትደነግጣለች ምክንያቱም ውስጤ እንድሳሳት ይገፋፋኛል ልቤ ይመታል እና እንደምትወደኝ ማሰብ እንድጀምር ያረገኛል እረፍ !!" አለችኝ ። ምን አልባት ልክ ብትሆኚስ እ አስቢ ምን ችግር አለው ደግሞ ለምንድነው ልብሽ የሚመታው እ ታፈቅሪኛለሽ እንዴ ??  አልኳት ጉፍጥጥ ብዬ ። " ሚኪ ዛሬ ምን ሆነሀል ቅድም አሞክ የነበረው ራስክን ነበር አበድክ እንዴ በዛው ?" አለችኝ ። አይ አሁን ላይ ከበፊቱ የተሻለ ጤነኛ ሆኛለሁ እሺ ብዬ ፈገግ አልኩኝ ። ትንሽ ዝም አለችና እንደማፈር እያለች " ታውቃለህ ሚኪ በቅርብ ስትታይ የበለጠ ቆንጆ ነክ እንድጎዳ ካልፈለክ አንድ እርምጃ ከእኔ ራቅ " አለችኝ ። ማለት ለምን ትጎጃለሽ እ እኔ ቆንጆ መሆኔ አንቺን ይጓዳል ? ብዬ ተመለከትኳት ። አዎ ምክንያቱም ልቤ በጣም እየመታ ነው " አለችኝ ። ከዛ ምን እንደሆንኩ አላውቅም ሊከተሉኝ የሚችሉትን  ጥፊ ጥሎ መሄድ  መጣላት ስድብ ሁሉንም ሳላስብ ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩኝም ቀና አድርጌ በእጆቼ ጉንጮቿን አቅፌ በማይሆን መንገድ ሳምኳት ከዛ ግን ደስ የሚለው እኔ ከጠበኩትና ከፈራሁት የተሻለ ነበር ። ጥፊ የለውም ትንሽ የስስት ግፍተራ አለ ከዛ እጆቿን አፏ ላይ አድርጋ ዞር ዞር ብላ አየችና ምን ሆነሀል ሰው ቢያየንስ ደግሞ ድገመውና ገድልሀለሁ እሺ " የሚሉ የደስታ ቃላቶችን ተናገረች ። በጣም ሳቋን ለመቆጣጠር እየሞከረች ነበር ቢያን በሰአቱ ፊቷ ላይ ቁጣና የመዘግነን ስሜት አለመኖሩ ሰላም ሰቶኛል ። ሲጀመርም ግልፅ የሆነ ነገር ነበር ዝምታዋ መልስ ሰጠኝ ። እውነት ለመናገር ያንን ነገር ከየት እንዳሰብኩትም አላቅም ለመጀመሪያ ጊዜ የወንድ ልጅ ስሜት ያየሁባት ሴት እሷ ናት !!!ባለፈው ማያ በዛ ልክ አውርታኝ ራሱ ምንም ፍላጎትና ስሜት አልነበረኝም ለማያ ሲሆን ግን አመለጠኝ !!!! አሁን ላይ ሳስበው የዛኔ እንኳንም ተሳሳትኩ እላለሁኝ!!! በሰአቱ የሆነ አይነት ንዝረትና ከልብ የመነጨ የደስታ ስሜት በየተራ እየተመላለሱብኝ ነበር ። ለምን እንደሆነም አላውቅም በርግጥ ግን የምር ኩራት ተሰምቶኛል የዛኔ የምርም ወንድ የሆንኩ መሰለኝ ።!! ከዛም ወደሷ ቤት መሄድ ጀመርን ። እንደስከዛሬው አልነበረችም። አታየኝም አታወራኝም ቅብጥ ቅብጥ አትልም እጅ በደረት አርጋ ቀስ እያለች መሄድ ጀመረች ። ሳወራትም በጣም በርጋታ መመለሷ ግራ ቢገባኝ ደህና ነሽ ልዕልና ችግር አለ አስከፋሁሽ እንዴ ?? አልኳት ። እንዴ ማለት ምንም አልሆንኩም አረ " አለችኝ  ።እና ምንድነው በአንዴ የተቀየርሽው ? አልኳት ። ሳቋ አመለጣት ነገር ግን በነዛ የሚያምሩ እጆቿ ሳቋን ከፊቷ ላይ ተቆጣጠረችና " አይገባህም እንዴ እንደነገሮች እየተቀየርኩ ነዋ " አለችኝ ። ንግግሯ የበለጠ ግራ አጋባኝ ። ማለት እንዴት ብዬ መልሷን መጠበቅ  ጀመርኩ " ካሁን ቡሀላ ኩል መሆን አለብኝ ነገሮች ተቀይረዋል ጓደኝነት እና ፍቅር ላይ አንድ አንነት ሰው አልሆንም አንተም የፍቅር ሰው ሁን እስኪ አሁንም ልዕልና ነው የምትለኝ እኮ ???" አለችኝ ። የኔ አናት  ሁኔታዋ በጣም ደስ እንዳላት ፊቷ ላይ ይናገራል !!!! አልፎ አልፎ ለስላሳ እጇቿን እየያስኩ ወደቤት ሄድን ። ስንደርስ ሳሚ ምሳ የሚበላበት ጠረንጴዛ ላይ ቁጭ ብሎ በሀሳበ ተውጦ ነበር ደ ቀበጧ  ልጅ ደህና ነህ አባዬ እንዴት ዋልክ ችግር አለ? " አለችው ። ሳሚም በአፀፋው ፈገግታ እያሳየ ደህና ነኝ ልጄ ምነው ? አለ እሺ ታጥቤ መጣሁ " ብላ ወጣች ። ከዛም ሶስታችንም አንድ ላይ ተቀምጠን ማውራት ጀመርን !!! ከዛ ከሰአታት በፊት ሰላም ታማ እንደነበርና በስንት መከራ እንደተረጋጋች ነገረን ። ከዛም ቁጭ ብለን ልክ እንደ ጓደኛ ስናወራ ነበር። ሳሚን ባየሁት ቁጥር ትዝ የሚለኝ አባቴ ነው ። ረዝሜ ብልም ሰበር ብዬ ማቀፍ የልብን ማውራት እኛ ቤት እንደ ጎጂ ባህል ነው የሚታየው ። በሰአቱም ሰላም  ድብር ብሏት ወደኛ መጣች ። ምን እንደነካት አላውቅም ገና ስታየኝ እሪ ማለት ጀመረች ከስከዛሬው ተለየችብኝ እና በጣም መጮህ እና መሣደብ ጀመረች ???? ....... . . ይቀጥላል ክፍል 3⃣2⃣

September 4, 2026 126