ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣5⃣ ..........እጇን ያዘኳት ።… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣5⃣


..........እጇን ያዘኳት ። በሰአቱ የአንዳንድ ሰዎች አይኔ እኛ ላይ መሆኑን ባስተውልም እንድታዳምጠኝ እየጠየኳት ነበር ።
አርፍጄ ሁሉንም አበላሽቼ ስጨርስ
ኤፈደም አሁንም አዳምጪኝ አልኳት ።
የመጨረሻችን ነው በሚል አይነት ፊት እያየችኝ እኔ ጋ ያለው ስሜት አንተ ጋ አለ እ ታፈቅረኛለሁ ትወደኛለህ ከዚህ አውተህ ታገባኛለህ ???" ብላ የጥያቄ ናዳ አወረደችብኝና ፍጥጥ ብላ አየችኝ ።
ህይወት በጭራሽ ሁለተኛ እድል አትሰጥም !!!
ለእኔ ግን ሰታኝ ነበር ለዛውም እንደ ጥፋቴ ያልሆነ በቂ እድል ነገር ግን ደግሜ ፎረሽኩ!!???እድሌን መጠቀም አልቻልኩም !!!
እሷ እንደመልስላት ስትጠብቀኝ እኔ እዛ ጋ ቆሜ በሌለ ደቂቃና ሰአት ቆሜ ገና ሁለቱን ማወዳደር ጀመርኩ ።
የሰጠችኝን ደቂቃ ከመጠቀም ይልቅ ቆሜ የሚሰማኝ ስሜት የትኛው ትክክል እንደሆነ ሳሰላስል ነበረ !!

ባይገባኝም በጣም ለረጅም ደቂቃ ቆማ ምላሼን ጠበቀች !እኔ ግን መወሰን አቅቶኝ እጄን እያንቋቋሁ ቆሜ አሰላስላለሁኝ ። ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት " ትላለች እናቴ ።
ልቤ መወሰን ባለመቻሌ ሁለቱንም እድሌን አባከንኩት !! ይቅር ብላ ደግማ የያዘችኝን እጅ ደግሜ ከዳዋት !!!
ደግሜ ልታመንላት ባለመቻሌ ባሁን እስከመጨረሻው በሚመስል ሁኔታ እጇን አላቃ ጥላኝ ሄደች ።

አጠገቤ ሆና ስትለምነኝ ከሷ ጎን መቆም ያልቻልኩኝ ልጅ  ልክ ከኔ ስትርቅ ልቤን የሆነ ነገር የወጋኝ ይመስል አይነት ስሜት ተሰማኝ !! ከዛ በላይ ከእራሴ ጋር መጣላቴን መቋቋም ስለከበደኝ ከዛ ቦታ በፍጥነት ወጥቼ ወደ ቤት ገብቼ ለጥ አልኩኝ ።
ራሴን በእንቅልፍ ለመሸወድ አስቤ ነበር !!
ነገር ግን ሀሳቦች ጭንቅላቴን ሞልተውት መተኛት ራሱ ከበደኝ ።
የተናደድኩት በልዕልና ቢመስለኝም ዋና ፀብ ከእራሴ ጋር ነበረ ።


ከእራስ ጋር መጣላት ደግሞ ምን ያህል እንደሚከብድና ራስን እስከመጥላት እንደሚያደርስ ልነግራችሁ አልችልም !!!!
በዛ ላይ እናት በጣም አመሸች ።
ጭንቅላቴ " እሄኔ እኮ ተጋብተው ጨርሰዋል ... አቅፏት ይሆናል ....እየጨፈሩ ይሆናል .....  " ይለኛል ልቤ ደግሞ በተራው " አዎ ብለህ ወስደሀት ቢሆን ኖሮ እሄኔ ለሷ ጀግና ወንድ ሆነክ ፍቅርህን አምነህ ተቀብለህ ከሷ ጋር አንድ ላይ ነበርክ ....ልብህ በደስታ እየመታ ነበር .....ከሀዘን ይልቅ ደስታ ላይ ነበርክ ..." እያለ ይሟገተኛል ።
በጭንቅላቴና ልቤ የተለያየ ሀሳብ እኔ ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም !!!
ሳስበው እናቶቻችን " የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም " ያሉት ለእንደኔ አይነቱ ልበ ቡኩን ሰው ይመስለኛል !!!!!


ጭንቅላቴ ከመፈንዳቱ ትንሽ ቀደም ብላ እናቴ ወደቤት መጣች ።
ብቸኝነቱ ስለተነሳልኝ ትንሽ ቀለል ብሎኝ ነበረ ነገር ግን ውስጤ ሰላም ሊሆንልኝ አልቻለም !!እናቴም እንደመጣች ፊቴን አይታ ልጄ ምን ሆንክብኝ እ ከሰርጉ ቡሀላ ደህና አደለህም " አለችኝ ።
የኔ እናት ጉዷን አላወቀች !!!
ደህና እንደሆንኩ አሳምኛት በሯን ዘጋግታ አጠገቤ መታ ተኛች ።
እኔ ግን እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ይልቁንም በጣም አመመኝ ።
ውስጤ ጭንቀቱ ሰውነቴ ግሏል ያንዘፈዝፈኛል ብርድ ብርድ ይለኛል ራስ ምታት .... አንድ ላይ ተደማምረው በህይወቴ አሞኝ የማያቅ ልጅ ልሞት እስኪመስለኝ ድረስ  ታመምኩኝ !!
ለሊት ላይ እናቴ ግለትክ ቀሰቀሰኝ ብላ ብድግ አለች ።

የኔ እናት  ማታ ላይ እንደደከማት እየነገችኝ ነበር ግን እኔን ስታይ ሁሉንም ረስታ ብድግ ብላ የቻለችውን ሁሉ አጀረገችልኝ ። ኀለሊቱን ሙሉ ጉልበቷ ላይ አስተኝታኝ ስትጨነቅ አደረች ።
ጠዋት ሲነጋጋ ደማከሴው ምናምን በቡና አጠጣችኝ ጭንቅላቴን አሻሸችኝ  ትንሽ ራስ ምታቱ ቀነሰ እንጂ ጤንነት ሊሰማኝ አልቻለም ። ሆስፒታል እንድሄድ ስትለኝ እንቢ ስላት መጣሁ ብላኝ ከብር ማጠራቀሚያዋ ውስጥ አውጥታ ከቤት ወጣች ።
ምን ሆኜ እንደሆነ አላቅም ከህየወቴ ከባዶቹ ህመሞች ውስጥ አንዱ ነው !!!
እናቴ ጥላኝ ስትወጣ ደግሞ የበለጠ አመመኝ ። እንቅልፌን ለማምጣት ለረጅም ሰአት ስገላበጥ ቆየሁ ግን ወፍ የለም !!!???
ፊቴን አዙሬ ተኝቼ ሳለ በሩ ሲከፈት ሰማሁና እናቴ መጣች ብዬ በደስታ ዞር ስል ማያ ፊት ለፊቴ ቆማለች ???......

.
.

ይቀጥላል


ክፍል 2⃣6⃣


Share share share
❤9🥰3👍1
August 29, 2026 306