ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣4⃣ ........ የሚያናደው ደግሞ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣4⃣

........  የሚያናደው ደግሞ ስደርስ ቀላል ነገር ነበር !
እንደውም ከጠበኩት በተቃራኒው አንድ ላይ ውጪ ቁጭ ብለው አየር እየተቀበሉ ነበር ።ሰላም ደህና ነሽ ? አልኩኝ እየተመለከትኳት አዎ የኔ ልጅ በጣም ደህና እየሆንኩ ነው ከፈጣሪ ቀጥሎ እድሜ ለአንተ " አለችኝ ።
ከዛም ልዕልናን በመጥፎ አይን እየተመለከትኩኝ
ታዲያ ለምን እንደዛ አልሽኝ አልኳት ንዴቴን ለመቆጣጠር እየሞከርኩኝ ።
ልቤ እዛው መሆን ቢፈልግም እግሬ ጭንቅላቴን እያዳመጠ በሱ ተመርቶ ባዶ እግሬ ሲሮጥ ወደሷ መጣ ???
ገና እዛው ቆሜ እየፀፀተኝ ነበረ ።
ልዕልና ግን ምንም እንዳልተፈጠረ
" እንድትመጣ ስለፈለኩ ነዋ ግን ሙሉ በሙሉ ውሸት አይደለም ቅድም ትንሽ አሟት ነበር " አለችኝ ነገሩኖ ቀለል አድርጋ???


አስታውሰዋለሁ በሰአቱ በጣም ተናድጄ በህይወቴ ሴት ልጅ ለመንካትም አስቤ የማላውቅ ልጅ ልመታት አቃቶኝም ነበር ።
በሰአቱ በራሴ ላይ ችግሮችን ላለመደራረብ ብዬ ፊቴን አዙሬ ሳሚ ይቅርታ አሁን መሄድ አለብኝ በጣም ከአስፈላጊ ነገር ላይ ነው አሟታል ሰጡት ትለኝ አቋርጬ የመጣውት ደህና ዋሉ !
ብዬ ምላሽም ሴልጠብቅ እየሮጥኩ ከዛ ጊቢ ወጣሁ ።


እስከዛሬ ከወጣሁ ብዙም ሳልቆይ ሳላስበው ቤቴ የምደርስ ልጅ ከነሱ ቤት ጀምሮ ብሮጥም መንገዱ እንደ መንግስተ ሰማያት ነበር የራቀኝ !!!
በጣም ከመጨነቄ የተነሳ ሀምሳ ኪሎ ባነሳ የማያልበኝን የላብ ውሀ ሳዘንብ ነበረ !!!መንገዱን ጠላሁት ከዛ ቀን ቡሀላ በዛ መንገድ ላላፍ ቃል መግባት እያማረኝ ልቤን እስክተፋት ድረስ እየሮጥኩ ወደ ሰርጉ ቤት ሄድኩኝ ።

አረፈድኩ !!!!! ማርፈድ ዋጋ ያስከፍላል ሲሉ አላምንበትም ነበር ነገር ግን ለኔ የህይወቴን ትልቁን ዋጋ አስከፈለኝ !!!.
ሰርጉ ተደርጎ ጋብቻው ፀድቆ ሰው መብላት መጠጣት ሲጀምሩ ኘበር የደረስኩት ።
በሰአቱ ባገኘውት ነገር ራሴን ብደበድበው ደስታዬ ነበር ። ከሰዎቹ መሀል ሹልክ ሹልክ እያልኩኝ ወደ ማያ ደረስኩኝ ። ፊት ለፊቷ ሆኜ አንዴ ነይ እያልኩ በሚስጥር ለመንኳት !!ነገር ግን እኔ ጊዚያዊ ስሜቴን አዳምጬ እየሮጥኩ ስሄድ የሷን ልብ ሰብሬ ነው የሄድኩት ለካ !!!!.


ብቻዬን ሄጄ ባናግራት ችግር ነው ብዬ ስለፈራሁኝ  ቆሜ ሳስብ እናቴ ወደነ ማያ ስጦታዋን ይዛ ስትሄድ ቸመለከትኩኝ !
የእኔ እናት ጉዷን አላወቀች ለልጇ ሀዘን ሰርግ አዘጋጅታለች ።
በሰአቱ በርካታ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ላይ እየተመላለሱ ነበሮ ግን ቅድሚያ እሷን ማውራት ስለነበረብኞዥዠኝ ሹልክ ብዬ ከእናቴ ጋር ወደሷ ቀረብኩኝ።
እንደምንም ጠጋ ብዬ  አንዴ  ላወራሽ እፈልጋለሁ  አልኳት ።
ግንባሯን እየነቀነቀች አይሆንም አለችኝ ።
እኔም ቶሎ ብዬ ቃል እገባለሁ ምንም ችግር አይፈጠርም አንዴ እናውራ አልኳት ።

አጎንብሳበት የነበረው አይኗ  ቀና ስትል በእንባ ተሞልቶ ልውጣ አልውጣ እየታገሉ ይመስል ነበረ !!
እሷም ላለማልቀስ እየሞከረች በፍጥነት
" አረፈድክ የአንተንም የእኔንም እድል አባከንክ ለአንድ ደቂቃ ጠብቀከኝ ቢሆን ኖሮ እኔም እንቢ የማለት ድፍረት አገኝ ነበር !!!
አንተን እያየሁ መብቴን ለማስከበር እደፍር ነበር ምን አልባትም ሮጬ መጥቼ እቅፍህ ውስጥ እደበቅ ነበር !!!
ከልጅነቴ ጀምሮ እኔ አንተን ሳይ አንድም ቀን ትኩረት ሰተከኝ አታቅም !!ህይወቴን በሙሉ አንተ የሆነ ቀን አይተክ ወደከኝ እንደምታጠባኝ እያሰብኩ ነው የኖርኩት ።
ታችኛውን መንደር ትምህርት ቤቱንና ክፍላችንን አንድ ላይ አስታውስ እስኪ ምን አልባት ያኔ ምን ያህል እመኝክ እንደነበር ይገባህ ይሆናል !!!! ልታድነኝ አልቻልክም መቃብር ውስጥ እንደወረወርከኝ ቆጥረዋለሁ ምክንያቱም ምሽቱን ሙሉ የኔ ጀግና መልከአክ አድርጌህ እንደምታድነኝ ተማምኜ ነበረ !! "  አለችኝ እንባዋ እየወረደ ግን ፊቷን ቶሎ ቶሎ እየጠረገች ።


አታርፍድ !! ለሚለው ቃል ትኩረት ሰጥቼው ባላውቅም የዛኔ ገና ትርጉሙ ገባኝ !!!.ማርፈድ የኔ የሆነውን ሰው ነጠቀኝ !!!ማርፈድ አንድን ሰው ወደስቃይ ከተተብኝ ......በሰአቱ ቃላት ማውጣት እስኪከብደኝ ነው የተረበሽኩት ዝምታዬ የበለጠ መልስ የሆነ መስሏት እሷም
" መልካም ህይወት እመኝልሀለሁ !! ላንተ ምርጧ ነው የምትገባህ !
ዪጀመሪያዬም የመጨረሻዬም ነህ እወድሀለሁ !!!" ብላኝ ፊቷን አዙራ ወደነማዬ ልትቀላቀል ስትል ቶሎ ብዬ እጇን ያዝኳት ........
.
.
.

ይቀጥላል


ክፍል 2⃣5⃣
❤4🥰2
August 29, 2026 281