❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️
✍ፊደል
ክፍል 2⃣3⃣
..........ጊዜ የለኝም አንድ ሚስጥር ነግሬህ እሄዳለሁ አለችኝ ለኔ ምን ልትነግረኝ እንደምትችል አልገባኝም ??
በዛ ሰአት ተሸፋፍና ወደኔ ስትመጣ ደንግጫለሁኝ ። ምክንያቱም እኔ እዛ የሞት ድግስ ላይም የታደምኩት እናቴን ላለማስከፋትና ከሰው ላለማጋጨት አስቤ ነው ።
ምንድነው ?? አልኳት አይን አይኗን እየተመለከትኩኝ ። እኔና እሷ በዛ ልክ ተቀራርበን ስናወራ የመጀመሪያችን ነበር ።ማያ ቀና ብላ አይኔን አይታኝ አታውቅም ነበር የዛን ቀን ግን ወደላይ አንጋጣ እያየችኝ ነበር ።አይኖቿን ሳይ ምንም ነገር መናገር አልቻልኩኝም ነበረ ምላሼ በዝምታ ማየት ነበር ። የዛ ቀን ገና አስተውዬ ውበቷን መመልከት ቻልኩኝ!!!
አይኖቿ ቡኒ ሆነው ከረጅም ሽፋሽፍቷና ከብዙ ቅንድቧ ጋር ተደምሮ በጣም ውብ እይታ አላት ። በሰአቱ እሷን እያየው አይምሮዬ ውስጥ ልዕልና እያለች ሁለቱን እያነፃፀርኩ ይሁን ምን ይሁን በማላቀው ሁኔታ በየተራ እያሰብኳቸው ነበር ??
ግራ ተጋብቼ ሁሉንም ነገር እያደበላለኩት ነው !!!ግራ ቢገባኝ አይኔን ጨፍኜ መግለጥ ስጀምር አሁን በምነግርክ ነገር እንዳትጠላኝ ለኔ ያለክ አመለካከት እንዳይቀየር " አለችኝ
እንደዛ ስትል የበለጠ ጉዳዩን ለማወቅ እንድጓጓ አደረገኝ ።
እሺ ምንድነው ችግር አለ ?? አልኳት
ለመናገር ቃላት ያጠሯት ይመስላል እ እ እያለች መርበትበት ጀመረች ።
እሷ ለመናገር ድፍረት እስክታገኝ ብዬ አስቤ በእናትሽ አታድርጊው እሱን አታግቢው እንዳታረጊው አሁንም ጊዜ አለሽ !! አልኳት በልመና ንግግር ።
" አልችልማ !!! " አለችኝ ። እሺ ለምን ??? በምን ምክንያት ነው ንገሪኝ መቼም ሰውዬውን እወደዋለሁ ልትይኝ አትችይማ !! አልኳት ምክንያቱም እንኳን እሷ በወንድምነትም ለመውደድ የሚከብድ በጣም ክፉና ተንኮለኛ ሰውዬ ነው ። አልችልማ ለእናቴ ስል አደርገዋለሁ በቃ አለቀ ያለ አባት ለፍታ ነው ያሳደገችኝ እሱን ታውቃለህ እኮ " አለችኝ ። እሱን አውቃለሁ ግን ሰርካለምን ለማውራት እንሞክር እሺ እኔ ልጠይቃት አልኳት አይይ አይሆንም መልሷን እያወክ ምንድነው የምትለኝ አሁን አዳምጠኝ በዚህ ሰአትና በዚህ ድፍረት ብቻ ነው እውነታውን ልነግርህ የምችለው " አለችኝ ።
እሺ ንገሪኝ ብያት እስክታወራ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። ነገሮችን አይተህ ባላየ አልፈህ ይሆን ባላውቅም ግን ከልጅነታችን ጀምሮ ግልፅ ነገር ነበር " አለችኝ ምኑ አልኳት ግራ ገብቶኝ ሀብትሽ እኔ ..." ብላ ንግግሩን ሳትጨርስ እናቴ እየተጣራች ወደኔ መጣች ።
" ሀብቴ ሀብትሽ ሀብትዬ " ትላለች
ምንድነው እማ አልኳት ቀስ ብዬ
" ስልክ ይፈልግሀል በጣም ብዙ ጊዜ ተደውሎልካል " አለችኝ ።
ከልዕልና ውጪ ሌላ የሚደውልልኝ ሰው የለም ስለዚህ እሷ ፊት ቆሜ ስልክ ማውራት አልፈለኩኝም ግን የምትነግረኝ እንዳይጠፋባት ብዬ ፈርቼ ትንሺ ፊቴን አዙሬ አቤት ? አልኩኝ
" ሚኪ እባክህ ታስፈልገናለህ " አለችኝ ።
እያለቀሰች ነበር ክው ነው ያልኩት
ምንድነው ?? ችግር አለ ምን ሆነሽ ነው ?? አልኩ እየተንተባተብኩ
" እማ አሟታል ዶክተር ብንጠራም ምንም ጥቅም የለውም ከማደንዘዣ ውጪ አንተ ለኛ መልአክ ነክ አሁኑኑ ና እባክህ ሚኪ ፍጠን " አለችኝ ። ልዕልና ስትመጣ ደግሞ ሁሉንም ረስቼ በሷ ቁጥጥር ስር እሆናለሁ ። እሷን እንቢ ማለትም ሆነ እያለቀሰች መስማት ስላላስቻለኝ ለእናቴ ስልኳን ሰጥቻት ለመሄድ ሩጫ ስጀምር
" ሀብታሙ !" አለች ማያ በጩኸች ።
እንደዛ ስታወራ ሰምቻት ስለማላቅ ደንግጫለሁኝ !!!
በሰአቱ ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ ተመልሼ እመጣለሁ ብያት መሄድ ስጀምር ከዛሬ ውጭ ልነግርክ አልችልም እባክህ " አለችኝ ።
እኔ ግን ምን እንደሆንኩ ባላውቅ ሀሳቤ ሁሉ ልዕልና ጋር ሆኖ ምን አልባትም የህይወቴን ትልቁ ስህተት እንደሰራሁ የሰማኛል !!!!
አሁን እመለሳለሁ እሺ አልኳትና ዞር ብዬ እየሮጥኩ ወደ ልዕልና ቤት ሄድኩኝ !
የሚያስከፋው ደግሞ እዛ ስደርስ ..........
.
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 2⃣4⃣
9
1
1August 28, 2026 280