❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️
✍ፊደል
ክፍል 2⃣2⃣
......... በጣም ፈርቼና ደንግጬ ነበር ።
ለምን እንደደነገጥኩም አላውቅም እኔ ብቻ ግን የሆ በህይወቴ ውስጥ የቆየ እና የኔ የሆነ ነገር እንደተነጠኩኝ አይነት ስሜት ተሰማኝ በሰአቱ ሳላስበውም ቢሆን
ምን ምን ማለት ነው አይሆንም ብዬ ጮኩኝ ምክንያቱም ፊቷን በደንብ አይቼዋለሁኝ !!
ማያ አይኗ ውስጥ የሆነ ከባድ ህመም ነገር ይታያል !!.ያለመፈለጓን ከፍራቻ ጋር ተደምሮ በደንብ ያስታውቅባታል !!
ሰርካለም ትንሽ ከበድ ያለች እናት ናት እኔ ብቻ ልደመጦ እና ልከበር አይነት ነገር ያጠቃታል በዛ ሰአትም ያለ ፍላጎቷ ልትድራት አስባ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ችዬ ነበር !!!
ማለት ልጄ ለምነሰ አይሆንም ?" አለችኝ መስከረም የሆነ አይነት አስተያየት እያየችኝ ። በሰአቱ ተናድጄ ስለነበር እየጮኩኝ ስለማይሆን ነዋ አይሆንም ! አልኩኝ ። የሆነ ታላቅ ወንድሟ ወይም የረጅም አመት ፍቅረኛዋ ነበር የምመስለው !
እናቴ ጮኬ በማውራቴ ተናዳ እየገላመጠችኝ ነበር !ግን ነገሩ ልክ እንዳልሆነ ስለማውቅ ነበር እንደዛ የተናገርኩት " ቆይ እሺ ማንን ነው የምታገባው ? " አለች እናቴ በተረጋጋ አነጋገር ! በላይሁንን አለች ወ/ሮ" መስከረም ፈገግ እያለች በላይሁን ? " አለች እናቴ ሰውዬውን ለማወቅ ስሙን እየደጋገመች ።በላይሁን ነዋ የጋሽ ጥበበ ልጅ " አለች እማዬ ክው ብላ
" አታረጊውም " አለቻት ።
እናቴ ቀስ በቀስ እኔን መደገፍ መቻሏ ቢያስደስተኝም መደንገጧ የበለጠ አስገረመኝ ምክንያቱም እኔ ሰውዬውን ማስታወስ ከብዶኝ ነበረ ከዛ ግን በድንገት ጋሽ ጥበበ የሚባሉት የወዳኛው ሰፈር ታዋቂ ባለሀብት ሰውዬ እና ወፍራሙና ግዙፉ አስፈሪው ሰውዬ በላይሁንን አስታወስኩት !!!
እሱ ማለት እንኳንስ ለቆንጅዬዋና ትንሿ የዋህና ዝምተኛዋ ማያ ቀርቶ ለማንም ሴት ማይመጥን ክፉና የማይረባ በገንዘብ ልግዛ የሚል ባለሀብት ሰው ነው !!
ከዛ የበለጠ ባሰብኝና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ በጭራሽ እሱን ማግባት አትችልም ያንን አልፈቅድም አይሆንም ለገንዘብ ብለሽ ልጅሽን ልትሸጪ ነው ?
ብዬ ጮኩባት ።
ከዛ ግን ሰርካለምም ከተቀመጠችበት ተነስታ ያንተን ፍቃድ ማን ጠየቀህ ጎረምሳው እኔኮ ምንም ቢሆን ክፉ ደግ አሳልፈናል ብዬ ለልጄ የደስታ ቀን እንድትገኙ ልነግራችሁ ነበር ። ወዲያው ቀለበት አርገው እዛው ሊጋቡ ነው ብዬ
ጭራሽ አድገህ እኔን ማዘዝ አማረክ እንዴ ሆ ጉድ እኮ ነው ....." እያለች እያጉረመረመች የማያን እጅ እየጎተተች ይዛት ሄደች ።
በሰአቱ የሆነ ስልጣን ቢኖረኝና እጇን ይዜ ከምትገባበት ፈተና ባወጣት ደስ ባለኝ ግን ምንም እንደማላመጣ ስለማውቅ አፌን ዘግቼ ዝም አልኩኝ ።ነገር ግን ፊቷ ላይ ያየሁትን ሀዘንና መከፋት ልረሳው አልቻልኩኝም የዛ ቀን ምሽቱንም ለሊቱን ሙሉም ሳስብና ስጨነቅ አደርኩኝ !!!!
በቀጣዩ ቀን ከመቸው እንደተስፋፋ አላቅም ከዛኛው መንደር ያለው ድግስና ወከባ እዚህ ድረስ ይሰማ ነበር !!!
በሰአቱ ጭንቅላቴ ማሰብ አቁሞ ነበር ምን ማረግ እንዳለብኝም ማወቅ አቃተኝ !!!
ምንም ነገር ሳላደርግ የሰርግ ጥሪ ????....
" አቶ በላይነህ ጥበበ
ወ/ሪት ማያ ደረጄ 💍💍 "
የሚል በፎቶዎች የደመቀ የሚያስጠላ ወረቀት ተበተነ ።
ለሷ ያለኝን ነገር ባላውቅም ያንን ነገር ማየት ሰላም ነስቶኝ ነበረ ።
የማይደርስ የለም የተባለው ሰአት ሲደርስ ቁጭ ብዬ ሳይ ነበረ ።
ድንገት እናቴ ስልክ ሲጠራ ደንግጬ ባነን አልኩኝ ። እናቴ ማውራት ጀመረች
" ሄሎ ...አቤት ..... እግዚሀር ይመስገነሰ ....አይደለም ልጄ ተሳስተሻል ... አረ ምን እስዋሸሽ ሙች ስልሽ ተሳስተሻል ...እሺ " የእናቴ በየዋህነት የምታወራው ንግግሯ ።
ስልኩ ሲዘጋ ማነው ? አልኳት ግራ ገብቶኝ ።
" ተሳስታ ነው ልጄ ሚኪ የለም ወይ ትለኛለች " አለች ።
የኔ እናት ስሜን ማስቀየሬን ረስታው ይመስላል !!
እማ አንዴ ስልኩን ስጭኝ አልኳትና ወደ ውጪ ወጥቼ ስልክ ደወልኩ ።
ልዕልና እንደሆነች ስላወኩ ነው እንደዛ ያረኩት ።
ሄሎ አልኩ
" ሄሎ ሚኪ እንዴት ነህ ናፈከኝ እኮ ጠፋክ ዛሬ ና በእናትህ እናቴም ትፈልግሀለች " አለችኝ ።
ይቅርታ ልዕልና ዛሬ መምጣት አልችልም ነገ ጠዋት መጣለሁ ብዬ አውርቻት ዘጋውት ።
ከዛ እናቴ ለባብሳ ስትወጣ ወዳጁን እንደሚቀብር ሰው ፊቴን ጥዬ ሄድኩ ።
ፈተናውስ የልጅነት ውበቷስ አርግዛ እዚህ የማንም መጫወቻ ልትሆን ነው ?? እያልኩ መብሰልሰል ጀመርኩኝ ።
ልክ ወደ ሰርጉ ቦታ እንደጀረስኩ ከእናቴ ተለይቼ ወደዃላ ቀረሁ ።
ከዃላዬ የሆነ ሰው ሲነካኝ ደንገጥ ብዬ ዞርኩኝ ። ተሸፋፍናለች ማያ ነበረች ።
" ጊዜ የለኝም አንድ ሚስጢር ነግሬህ እሄዳለሁ " አለችኝ ......
.
.
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 2⃣3⃣
5
2
1August 28, 2026 280