ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣1⃣ ...........ወደ ውስጥ ገባ ።… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣1⃣

...........ወደ ውስጥ ገባ ። አባቴን እወደዋለሁ አከብረዋለሁኝም ጭምር ግን አንዳንዴ ሌሎች አባቶችን አይቼ እሱን ሳይ የምር ከልቤ እከፋለሁ ምንም እንኳን የተደላቀቀ ህይወት ካልሰጠኝ ብዬ ባላማርርም ድህነታችንን እንኳን አጣጥመን እንድንኖራት አልፈቀደልንም ።
ማለት ስሜን ሀብታሙ ብሎ አውጥጦ ሀብታም እስክሆን ከመጠበቅ ውጪ ምንም እያደረገልን አይደለም !!
ቢያንስ እንኳን ለፍቶ በቀን ስራ ምናምን የሚያገኛትን ብር ለኛ የሆነ ነገር ማረግ ባይችል እንኳን እናቴ ልብስ አጥባ የምታመጣውን ብር ለመውሰድ መድፈር አልነበረበትም !!
ቢያንስ እንኳ ሁሉም ቢቀር ሰክሮ እየመጣ በየቦታው እያደረ ክብሯን ባይሰርቅብኝ ደስ ይለኝ ነበር ። አንዳንዴ እናቴ የተሸከመቻቸውን ችግሮችና በሆዷ የያዘቻቸውን ህመሞችና ሚስጥሮችን ሳስብ  በጣም ታሳዝነኛለች !!!
ከድሮ ጀምሮ በሆዷ በርካታ ሀዘንና ሚስጢር አለ ግን ደስተኛ ሰው ይመስል ሁሌ ስትስቅና በእልልታ ስታደምቅ ትታያለች !!
የን ቀንም ቢሆን ምንም እንዳልተፈጠረ ሰው ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ሲመጣ እሱ እየተንገዳገደ ባደፉ ልብሶቹ ተሸፍኖ ወደ ቤት  መጣ !!

ቀን በቀን አባቴ እየተቀየረ ነው የመጣው !! እየባሰበት እንደ ልብሱ ልቡም እያደፈ የመጣ ይመስል ክፉ መናገር አዘውትሯል የዛን ቀንም ሲገባና በዛ ሁኔታ ውስጥ ሲያየን ምንም በማያስቀው ከት ብሎ እየሳቀ እናትና ልጅ ተስማምታችዃል አይደል  እኔ ስወጣ ደስተኛ ሆናችዃል ድሮም እኮ ያራራኳችሁ እኔ ነበርኩ አይደል  ሀ ሀ ሀ  ሀ ሀ ሀ ( ረዘም ያለ የፌዝ ሳቅ ሳቀና)
ሳስበው የድህነት ኑሮ የተስማማችሁ ይመስላል !!" አለን ወደ ውስጥ እየገባ ።
በሰአቱ ከማንም በላይ የእናቴ ቅስም እንደሚሰበር ግልፅ ነው በጣም ከፍቷት እንባዋ እስከማቅረር ቢደርስም ስሜቷን ዋጥ አድርጋ የኔን መከፋት እንዳስተዋለች
" ዛሬ ደግሞ ከነ ጋኑ ነው መሠለኝ የተጋተው " ብላ ያልመጣባትን ከትት ብላ ሳቀች ።

እኔም የሷን ደስታ ለማርዘም ስል ፈገግ ብዬ በይ አሁን ስጦታዬን ተቀበይኝ ብዬ ግንባሯን ስሜ የገዛውላትን በብልጭልጭ የተሸፈኑ ጌጣጌጦች አደረኩላት የኔ እናት አርቴ ሆነ የብር ሆነ ምንም አያሳስባትም ።
በህይወቷ የታደለች አይደለችም ስጦታ ምናምን ተሰቷት ስለማያቅ ይሄ ለሷ ትልቅ ነገር ነው !!እንደውም ልጄ ደረሰልኝ ብላ በደስታ ነው የምትኩራራው ።
በነገራችን ላይ እኔ ሀብታም መሆኑን የምፈልገው ለእኔ አይደለም እኔ እንደ አብዛኞቹ እኩዮቼ ጥሩ ልብስ እለብሳለሁ ግን ለእናትና አባቴ ስል ማድረግ አለብኝ በተለይ ለእናቴ  !!!!

እኔና እናቴ በዛቾ ትንሽ ነገር ስንላቀስና ምን ያል እንደምትወደኝ እየነገረችኝ በሩ ተንኳኳ ።እንባዋን ከአይኗ እያበሰች ሄዳ በሩን ከፈተችው ።
ወደ ውጪ ስመለከት ሰርካለምና ማያ ነበር በወጣሁ ቁጥር መንገድ ለመንገድ የምንገናኘው አልበቃ ብሎ ጭሳሽ ቤቴ ?? ብዬ በጣም ተናደድኩኝ!
በነገራችን ላይ ይሄ የአይምሮዬ ንግግር ነው ልቤ በተቃራኒው ግራ እየተጋባም ቢሆን እንድትቆይ ይፈልጋል ።

ማያ እኔ በሌለው ቀን ካልሆነ በቀር እዛ ቤት ድርሽ ብላ አታውቅም ነበር ግን ቤታችንንም ድህነታችንንም  ስለምታውቀው ያን ያህል አልጨነቀኝም ።
የነሱ ቤት በጣም ከኛ የተሻለ ነው እንደኛ አካባቢ ሀብታም የሆነ ቤተሰብ ነው በተለይ ደስተኛ መሆናቸው ያስቀናኛል ።
እንደሚጠበቀው እናቴ ገና በሩ ከመከፈቱ
" እልልልልል እይማ አየሽ ልጄ ምን እንደሰጠኝ ኑ ግቡ ቆይ ብላ ቶሎ ቶሎ ቡና ማፍላት ጀመረች ።እዛ ቤት ውስጥ የኔና የማያ የአይን ግጥጥሞሽ ሊያሳብደኝ ደርሷል !!!ግን አሁን ላይ የህነ ነገር እርግጠኛ እየሆንኩ ነው!!!
በሁለታችንም መሀል የሆነ ቅርበትና መሣሣብ አለ!!! በስርአት ላወራት ራሴ አስቤ ስጨርስ በመሀል ሠርካለም ዛሬ እኔም ምነግራችሁ ትልቅ ነገር አለ ።
ማያ ቀለበት ልታስር ነው " ስትል ፊቴ ላይ ያለውን ፈገግታ እና የሆነ የስሜት እሳት  ውሀ ደፍታ አጠፋችው....

ላይኩ 100 ከሞላ አንድ ክፍል ይለቀቃል

.
.
.
.

ይቀጥላል


ክፍል 2⃣2⃣
❤21
August 27, 2026 256